27/10/2025
ድህረ ወሲብ እራስ ምታት
ድንገተኛ ከፍታኛ የውጋት እና ውጥረት የሚይዝ አይነት እራስምታት ሲሆን አንገት እና ማጅራት የሚካትት ሊሆን ይችላል በእርካታ መዳረሻ ና መጨረሻ ላይ ሲከስት ወንዶች በአራት እጥፍ ከሴቶች ይልቅ ተጋላጭ ናቸው
በወሲብ ወቅት በሚፈጠር የደም የግፊት መጨመር ና የጡንቻዎች መወጣጠር እንደ አጋላጭ ምክንያት ቢነሳም እንዲ ነው የሚባል ምክንያት ግን የለውም። ለመጀመሪያ ግዜ ሲከስት በተለይ ከአንጎል ሽፋን ውስጥ ድምፅ መፍሰስ SAH መለይት ያሻል ።
ይህም በተያያዥነት ራስንመሳት ፥ማስመለስ እየጨመረ የሚሄድ እራስምታት አልያም የማጅራት ጅምድዶ የሚይዝ ህመም ፤ የጭንቅላት ሲቲ ስካን አስፈላጊ ይሆናል ከዚ በፊት 3 የተከሰተ ከሆነ ግን ለመለየት ቀላል ይሆናል ።
በፓራስታሞል ብዙ ለውጥ ላይኖር ይችላል ።
እንደ አስፈላጊነቱ ቅድሚያ በየለቱ እና በህመም ወቅት በሀኪም ሊታዘዙ የሚችሉ መድሀኒቶች አሉ።