Decoter sami alemu

Decoter sami alemu Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Decoter sami alemu, Doctor, 文山區興隆路, Taipei.

25/01/2026
እንዲት ነኛ
21/01/2026

እንዲት ነኛ

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ” ማለት ነው፡፡ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣትና ...
28/12/2025

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ፣ ሰው አምላክ ሆነ” ማለት ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል የጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣትና ሰው መሆን ለመናገር ተልኮ የምሥራች ዜናን ያበሠረ፤ በዲያቢሎስ የተንኮል ወጥመድ ገብተው ለተሰናከሉት ፈጥኖ ለመርዳት የሚደርስ፣ በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩት ሁሉ የብርሃን ፋና ያበራ፣ ሰብአ ሰገልን የመራ መልአክ ነው፡፡

ከቀድሞ ጀምሮ ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ተልከው መንፈስ ቅዱስ እንዳናገራቸው ዓለምን ስለማዳን ከጽዮን የሚወጣ ከያዕቆብ በደልን የሚያርቅ ጌታ “ይወርዳል ይወለዳል” በማለት በየወገናቸውና በየዘመናቸው የተናገሩትን የነቢያትን ትንቢት መፈጸሙን የሚያበስረውን የምሥራችን ቃል የተናገረ ነው፡፡ የጨለማ አበጋዝ በሆነ በሰይጣን ተንኮል በሰው ልቦና ውስጥ አድሮ የነበረውን ከእፉኝት መርዝ የከፋ የኀዘን ስሜት ያጠፋ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ከሌሎች መላእክት ተለይቶ ዘወትር በምንጸልያቸው ጸሎቶች ስሙ የሚጠራ መልአክ ነው፡፡ ይኸውም በዘወትር ጸሎቶች በአቡነ ዘበሰማያት፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል፣ በውዳሴ ማርያም፣ በይዌድስዋ መላእክትና በመሳሰሉት ጸሎቶች ዘወትር ስሙ የሚጠራ ነው፡፡ ካህናት አባቶች ቅዱስ ገብርኤል ስእለት ሰሚና ፈጥኖ ደራሽ መልአክ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ይኽም በክርስቲያኖችም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ፈጥኖ ደራሹ መልአክ፣ ስእለት ሰሚው መልአክ ይሉታል፡፡ የአምላክ እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከሌሎች መላእክት ሁሉ በይበልጥ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን እንደምትወደው በድርሳነ ገብርኤል “ወንድሞቻችን ሆይ፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመላእክት ሁሉ ይልቅ ቅዱስ ገብርኤልን በይበልጥ እንደምትወደው ተመልከቱ፤ የልጅዋን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ መወለድ ያበሠራት እርሱ ነውና” የሚል ተጽፎ ይገኛል፡፡

ከሰባቱ ሊቃነ መላእክትም አንዱ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ይህ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ፣ ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካል፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን በዘመኑ ጣኦት የሚያመልከው ንጉስ ናቡከደነፆር በባቢሎን ምርኮ የወሰዳቸውን የእግዚአብሔር ሰዎች አናንያ፤ አዛርያ፤ ሚሣኤል እጅግ ይወዳቸው ነበር፡፡ ከባቢሎናውያን ይልቅ ጠቢባን የነበሩት ሶስቱ ሕጻናት በትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ሦስት ሰፍሮ የምናገኘው ታሪካቸው እንደሚነግረን ንጉሱ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶም ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሳት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር።

ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ፣ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻላል?" ቢላቸውም የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል፣ ባያድነንም ግን አንተ ላቆምከው ጣኦት አንሰግድም" አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሳት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሏቸውን ወታደሮች የእሳቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠለስቱ ደቂቅን ግን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው፣ አጠፋላቸው። ከእሳቱ ላይ ሆነውም እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡

ገዳማውያኑ

Address

文山區興隆路
Taipei

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Decoter sami alemu posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category