Enat Space - የእናቶችና የልጆች ጤና

Enat Space - የእናቶችና የልጆች ጤና Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Enat Space - የእናቶችና የልጆች ጤና, Health & Wellness Website, USA, Washington D.C., DC.

እናት ስፔስ የእናቶችና የልጆች ጤና ገጽ ሳምንታዊ የእርግዝና ክትትሎችን፣ የጽንስ እድገት፤ ምጥ፣ እናትነትን እና የልጆች አካላዊ አእምሮአዊና ስነልቦናዊ እድገትን በተመለከተ መረጃ የሚገኝበት በሳይንስ የተደገፈ፣ ባህልን ማዕከል ያደረገ የኢትዮጵያውያን እናቶችን እና ህጻናት ጤና ላይ ያተኮረ መረጃ የሚገኝበት ነው።

🤰ልጅሽ በዚህ ሳምንት ልጅሽ የአንድ የሾላ ፍሬ መጠን አለው፡፡ ጣቶቹ/ቿም ሙሉ ለሙሉ መከፈት እና መዘጋት ይጀምራሉ፡፡ በድዱ ስር ትናንሽ የጥርስ እምቡጦች እያቆጠቆጠ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ...
02/01/2026

🤰ልጅሽ በዚህ ሳምንት ልጅሽ የአንድ የሾላ ፍሬ መጠን አለው፡፡ ጣቶቹ/ቿም ሙሉ ለሙሉ መከፈት እና መዘጋት ይጀምራሉ፡፡ በድዱ ስር ትናንሽ የጥርስ እምቡጦች እያቆጠቆጠ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ የተሰሩት አንዳንድ አጥንቶቹም እየጠነከሩ ይገኛሉ፡፡ መንጠራራት እና መንቀሳቀስም ይጀምራል፡፡

ዝርዝሩን ከታች ካለው ሊንክ ሰብስክራይብ በማድረግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ የሚለውን ተጭነው ያንብቡ 👇

ልጅሽ በዚህ ሳምንት ልጅሽ የአንድ የሾላ ፍሬ መጠን አለው፡፡ ጣቶቹ/ቿም ሙሉ ለሙሉ መከፈት እና መዘጋት ይጀምራሉ፡፡ በድዱ ስር ትናንሽ የጥርስ እምቡጦች እያቆጠቆጠ ነው፡፡ እስካሁን ድ.....

🤰አስረኛ የእርግዝና ሳምንት ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ጽንሱ መሰረታዊ የሆኑት የሰውነት ክፍሎች ማለትም ኩላሊት፣ አንጀት አእምሮ፣ እና ጉበት በቦታቸው ላይ በመሆን ስራቸውን ጀምረዋል፡፡ በልጅሽ በ...
01/23/2026

🤰አስረኛ የእርግዝና ሳምንት
ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ጽንሱ መሰረታዊ የሆኑት የሰውነት ክፍሎች ማለትም ኩላሊት፣ አንጀት አእምሮ፣ እና ጉበት በቦታቸው ላይ በመሆን ስራቸውን ጀምረዋል፡፡ በልጅሽ በእጅና እግሮቹም ላይ ትናንሽ ጥፍሮች እያበቀለ ይገኛል፡፡
ከማርገዝሽ በፊት ማህጸንሽ የአንድ አነስተኛ ፔር ፍሬ መጠን የነበረው ሲሆን አሁን ግን የአንድ ትልቅ ግሬፕ ፍሩት መጠን ያክል ሰፍቷል። በአሁን ሰዓት የእርግዝና ልብሶችን ለመልበስ ገና ልትሆኚ ትችያለሽ።

ዝርዝሩን ከታች ካለው ሊንክ ሰብስክራይብ በማድረግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ የሚለውን ተጭነው ያንብቡ 👇

Week 10

🤰ሰውነትን ለእርግዝና ምቹ የሚያደርጉ ምግቦችእርግዝና በሚያስቸርበት ጊዜያቶች ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ለውጦች መካከል ከመድሃኒት እና ከህክምና እኩል የሚከተሉትን ምግቦች በመመገብ የመውለድ እድል...
01/20/2026

🤰ሰውነትን ለእርግዝና ምቹ የሚያደርጉ ምግቦች

እርግዝና በሚያስቸርበት ጊዜያቶች ሊያደርጓቸው ከሚገቡ ለውጦች መካከል ከመድሃኒት እና ከህክምና እኩል የሚከተሉትን ምግቦች በመመገብ የመውለድ እድልዎን ከፍ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

ዝርዝሩን ከታች ካለው ሊንክ ሰብስክራይብ በማድረግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ የሚለውን ተጭነው ያንብቡ 👇
https://enatspace.substack.com/p/e92

💋 ጥቂት ስለውበት ለተጎዳ ጸጉር  የእሬት ማስክ እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?ዝርዝሩን ከተያያዘው ሊንክ ሰብስክራብ በማድርግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ 😉የሚለውን በመምረጥ ማንበብ ይችላሉ 👇
01/14/2026

💋 ጥቂት ስለውበት
ለተጎዳ ጸጉር የእሬት ማስክ እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል?

ዝርዝሩን ከተያያዘው ሊንክ ሰብስክራብ በማድርግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ 😉የሚለውን በመምረጥ ማንበብ ይችላሉ 👇

Aloe vera for Hair treatment

🤰ዘጠነኛው የእርግዝና ሳምንትበዚህ ሳምንቱ ጽንሱ አንድ የወይን ፍሬ የሚያክል መጠን አለው።ዝርዝሩን ከተያያዘው ሊንክ ሰብስክራብ በማድርግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ 😉የሚለውን በመምረጥ ማንበብ ይ...
01/13/2026

🤰ዘጠነኛው የእርግዝና ሳምንት
በዚህ ሳምንቱ ጽንሱ አንድ የወይን ፍሬ የሚያክል መጠን አለው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ሊንክ ሰብስክራብ በማድርግ አሊያም ለዛሬ ይለፈኝ 😉የሚለውን በመምረጥ ማንበብ ይችላሉ 👇

Week Nine

በኦፕሬሽን የወለደች ሴት ህመም ሳይኖራት እንዴት  ከአልጋ ላይ መነሳት ትችላለች?
01/01/2026

በኦፕሬሽን የወለደች ሴት ህመም ሳይኖራት እንዴት ከአልጋ ላይ መነሳት ትችላለች?

🌺🌸🌼ለድህረ ወሊድ ድባቴ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮችከወሊድ በኋላ የሚከተል የድብርት ስሜት በማንኛዋም ሴት ላይ ሊያጋጥም የሚችል ሲሆን በተልይም የገንዘብ ጭንቀት እና ሃሳብ ባለባቸው ላይ ይ...
01/01/2026

🌺🌸🌼ለድህረ ወሊድ ድባቴ ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች

ከወሊድ በኋላ የሚከተል የድብርት ስሜት በማንኛዋም ሴት ላይ ሊያጋጥም የሚችል ሲሆን በተልይም የገንዘብ ጭንቀት እና ሃሳብ ባለባቸው ላይ ይበረታል። ለመሆኑ ይሄንን ስሜት እንዴት ማሸነፍ እንችላለን?

-አመጋገብ፦ ተልባ፣ ቻይ(chia seeds)፣ ሰርዲን የቆርቆሮ ዓሳ፣ አብዝቶ መመገብ ድባቴ የመቀንስ ኃይል እንዳለው ጥናቶች ያመላክታሉ
- የሰውንት ንጽህናን መጠበቅ፣ ንጹህ ልብስ መልበስ፣ ቤትን እና አካባቢን ማጽዳት፣ ንፋስ ወደቤት እንዲገባ በማድረግ የቤቱን ድባብ መቀየር፤
- እንቅልፍ መተኛት፤
- ጸሎት፣ ዱዓ ማድረግ፤ ከመንፈስ አባቶች ጋር መወያየት...

ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ሊንክ ያገኙታል

https://substack.com/home/post/p-182791166

ማር እና እርድ በጸሃይ ለተጎዳ ፊት እንዴት መጠቀም ይቻላል? -አንድ የሻይ ማንኪያ ያልተቀነባበረ ማር ከአንድ የሻይ ማንኪያ የእርድ ዱቄት ጋር ይቀላቅሉ- በንጹህ ቆዳ በስሱ ተቀብቶ ከ10–1...
12/27/2025

ማር እና እርድ በጸሃይ ለተጎዳ ፊት እንዴት መጠቀም ይቻላል?

-አንድ የሻይ ማንኪያ ያልተቀነባበረ ማር ከአንድ የሻይ ማንኪያ የእርድ ዱቄት ጋር ይቀላቅሉ

- በንጹህ ቆዳ በስሱ ተቀብቶ ከ10–15 ደቂቃ ማቆየት እና ለብ ባለ ውሃ መታጠብ(ሳሙና ከመጠቀም ይቆጠቡ)

በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ይጠቀሙ።

ማር እና እርጎ በጸሃይ ለተጎዳ ፊት እንዴት መጠቀም ይቻላል?

ዝርዝሩን ከታች በተቀመጥው ሊክ ያገኙታል
https://enatspace.substack.com/p/af2

አራተኛው የእርግዝና ሳምንት ምን ይመስላል?ከዚህ ሳምንት እስከ አስረኛው ሳምንት ድረስ ማህጸንሽ ውስጥ ያለው ጽንስ ሁሉም የሰውነት ክፍሎች ቅርጽ መያዝ ይባስ ብሎም አንዳንዶቹ እንደውም ስራ ...
12/26/2025

አራተኛው የእርግዝና ሳምንት ምን ይመስላል?

ከዚህ ሳምንት እስከ አስረኛው ሳምንት ድረስ ማህጸንሽ ውስጥ ያለው ጽንስ ሁሉም የሰውነት ክፍሎች ቅርጽ መያዝ ይባስ ብሎም አንዳንዶቹ እንደውም ስራ ይጀምራሉ፡፡

ስለዚህም ከጽንሱ እድገት ጋር ሊፈጠሩ የሚችሉ እንከኖች ለማስቀረት ጤናማ አመጋገብ በተለይም ከፍተኛ የአይረን ንጥረነገር ያላቸው ምግቦች እንደቆስጣ፣ ዘቢብ፣ ጉበት በመመገብ፣ ሺሻም ሆነ ሌሎች አይነት ጭሶችን እንዲሁም የአልክኾል መጠጥ መጠቀም የመሳሰሉ አጉል ልምዶችን በማቆም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሻል፡፡
https://substack.com//p-182582666

12/16/2025

አንዲት ሴት ለመጀመሪያ ጊዜ ስታረግዝ ማወቅ የሚገቧት ነገሮች ምንድናቸው ትላላቹ ?

አምስተኛ ሳምንት በአሁን ሰዓት የጡት ማበጥ፣ ድካም እና ማቅለሽለሽ የመሳሰለ የእርግዝና ስሜቶች ጀምረውሽ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ማርገዝሽን ካንቺ ሌላ ያልተነገረው ሰው በምን ዓነት ሊ...
12/14/2025

አምስተኛ ሳምንት

በአሁን ሰዓት የጡት ማበጥ፣ ድካም እና ማቅለሽለሽ የመሳሰለ የእርግዝና ስሜቶች ጀምረውሽ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ማርገዝሽን ካንቺ ሌላ ያልተነገረው ሰው በምን ዓነት ሊያውቅ አይችልም፡፡ አርግዝናሽንም ሆነ እራስሽን ለመጠበቅ ማድረግ ያሉብሽ ነገሮች ይኖራሉ፡፡

በስራ ቦታ ላየ ለተለያዩ ዓይነት ጥቅም ላይ የሚውሉ ኬሚካሎች(በተለይ ጸጉር ቤት፣ ቀለም ፋብሪካ የምትሰሪ ከሆነ ከኬሚካሎች መራቅ ፣ እንዲሁም በሆስፒታል የምትሰሪ እና ለተለያዩ ጨረሮች ተጋላጭነት ካለሽ እነዚህን ነገሮች በማስተዋል ከአልቃሽ ጋር መነጋገር እና ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብሻል፡፡

በዚህ ወቅት ጽንሱ ከፍተኛ በሆነ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል፡፡ በአሁን ሰዓትም የሰሊጥ ፍሬ ያህል መጠን ሲኖረው እድገቷን ያልጨረሰች እንቁራሪት ቅርጽ አለው፡፡ ሰውነቱም ከሦስት የተለያዩ ሽፋኖች የተሰራ ሲሆን ያላይኛው ሽፋን (ectoderm)ከልጅሽ ጭንቅላት በመነሳትም ህብለ ሰረሰር፣ የጀርባ አጥንት፣ የደምስሮች፣ ቆዳ፣ ጻጉር፣ ጥፍር፣ የጡት እና የላብ እጢዎች ይሰራል፡፡

ሁለተኛው ሽፋን(mesoderm) ደግሞ የልብ እና የደም ዝውውር ሰርዓቶች የሚያኪሄዱበት የሰውነት ክፍሎችን በማሳደግ ላይ ይገኛል፡፡ከጥቂት ሳምንታት በኋላም የልጅሽ ልብ መምታት እና በሰውነቱ ውስጥም ደም መዘዋወር ይጀምራል፡፡

ሦስተኛው ሽፋን(endoderm) ደግሞ እንደ ሳምባ፣ አንጀት፣ ጉበት፣ የታይሮይድ እጢ፣ ጣፊያ፣ ቅድመ የሽንት ስርዓት እና የእንግዴ ልጅ እንዲሰራ ያደርጋል፡፡

Address

USA
Washington D.C., DC
20011

Opening Hours

Monday 9am - 5pm
Tuesday 9am - 5pm
Wednesday 9am - 5pm
Thursday 9am - 5pm
Friday 9am - 5pm
Saturday 9am - 1pm

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Enat Space - የእናቶችና የልጆች ጤና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Featured

Share