16/10/2025
ደም መለገሶ ለእርሶም ጤና ጥቅም እንዳለው ያውቃሉ?
ደም መለገስ ከስጦታዎች ሁሉ የበለጠ ስጦታ ሲሆን በመለገሳችን የሚወልዱ እናቶችን፣ አደጋ የደረሰባቸው ሰዎችን፣ ካንሰር እና ሌላ የረጅም ጊዜ የጤና ችግር ያለባቸው እህት ወንድሞቻችን በቂ ደም ወይም የተወሰኑ የደም ሴሎች ሳያገኙ ከመሞት እንታደጋለን
ደም መለገስ ታዲያ ከጤና አንፃር ለሚለገስላቸው ብቻ ሳይሆን ለለጋሾቹም ከፍተኛ የጤና ጠቀሜታ አለው፡፡ እንደ አሜሪካ ቀይ መስቀል ማህበር መረጃ መሰረት አዘውትሮ ደም በመለገስ የሚያገኟቸውን የጤና ጠቀሚታዎች የሚከተሉትን ይመስላሉ
✦ ጭንቀትን ይቀንሳል
✦ ክብደትን ለመቀነስ ይረዳዎታል
✦ የደም ሕዋስ ምርት እንዲጨምር ያደርጋል
✦ በደሞ የሚገኘውን ከፍተኛ የብረት ክምችት በመቀነስ የልብ ምቶ የተስተካከል እንዲሆን፣ ጡንቻዎት እንዳደክም፣ ጉበቶና ጣፊያዎ እንዳይጎዳ እንዲሁም ለካንሰር እንዳይጋለጡ ይረዳዎታል
✦ በልብ በሽታ የመጠቃት እድልን ይቀንሳል
✦ የኮሌስትሮል (የደም ቅባት) መጠንን ይቀንሳል
✦ በሰውነቶ ያለው ካሎሪ እንዲቃጠል ይረዳል
✦ ነፃ የጤና ምርመራዎች ( የልብ ምት ፣ የደም ግፊት፣ የሰውነቶ የሙቀት እና የሂሞግሎቢን መጠን እንዲሁም የደም አይነቶን ማወቅ ይችላሉ)
✦ የተለያዩ የበሽታ ምርመራዎችን በነፃ (ሂፐታይተስ -ቢ እና ሲ፣ኤች አይቪ፣ዌስት ናይል ቫይረስና የቂጥኝ)
ከእርስዎ የተወሰደው 1 ከረጢት ደም እስከ 3 ሰዎች ያህል ሕይወት በመታደጉ የደስታ ስሜትን ይጎናፀፋሉ
አብዛኞቻችን ደም በመለገሳችን ለችግር ተጋላጭ እንሆን ይሆን ብለን እናስባለን እውነታው ግን ደም መለገስ የሚያመጣው ምንም ችግር የለም፤ ለእያንዳንዱ ለጋሽ አዲስና ጤንነቱ የተጠበቀ ዕቃዎች ስለሚጠቀሙ ደም በመለገስዎ በደምና በደም ንኪኪ ሊተላለፉ የሚችሉ ኢንፌክሽኖች ሊይዝዎ አይችሉም። እርስዎ ጤናማ ከሆኑ ጤንነትዎ ላይ ምንም አይነት ችግር ሳይከተል ደም መለገስ ይችላሉ
ደም ለመለገስ የሚደረጉ ዝግጅቶች :
✦ ሙሉ ጤነኛ መሆን
✦ ቢያንስ 18 አመትና ከዚያ በላይ መሆን
✦ ክብደትዎ ቢያንስ 45 ኪሎግራም መሆን
✦ አካላዊና ሌሎች የጤና ምርመራ ማለፍ የሚችል መሆን አለበት
✦ እርግዝና፣ በቅርቡ የተደረገ ውርጃ እና የቀዶ ህክምና አለመኖሩን ማረጋገጥ
✦ የሚለግሰው ሰው በቅርቡ ክትባቶችንም ሆነ መድሃኒቶችን ያልወሰደ መሆን አለበት
ደም ለመለገስ ካሰቡበት ቀን በፊት ባለው ምሽት በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሚያስፈልግ ሲሆን ከመለገስዎ በፊት ጤናማ ምግብ መመገብ፤ ስብነት ያለቸውን (ለምሳሌ የአሳማ ስጋ) እና እንደ አይስ ክሬም ያሉ ምግቦችን አለመመገብ ይመከራል