04/12/2025
አስደሳች ዜና
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በሀገራችን መከሰቱን አስከትሎ ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እንዲሁም የህብረተሰባችንን ጤና ለመጠበቅ የጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ከክልል ጤና ቢሮዎች እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን በሽታዉን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤
በዛሬው ዕለት ከአሜሪካ መንግስት በተደረገ ድጋፍ ለበሽታው ተጋላጭነት ላላቸው የማህበረሰባችን ክፍሎች በሽታውን ለመከላከል የሚያግዝ “Sabin single-dose cAd3 Marburg vaccine” የተባለ የማርበርግ ክትባት ተረክበናል።
ይህ የማርበርግ ክትባት በተለያዩ የማርበርግ በሽታ ወረርሽኝ የተከሰተባቸው ሀገራት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዕገዛ እንዳደረገ የተገለፀ ሲሆን ይሄን ተሞክሮ በመውሰድ ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ ባለሙያዎቻችን እና የህብረተሰባችን ክፍሎች ለማቅረብ ዝግጅቶችን ጨርሰናል።