16/04/2026
ያስረጃል የሚባለው ስጋ በአግባቡ ከተመገብነው እርጅናን እንደሚያዘገይ ያውቃሉ?
ምንም እንኳን በተለምዶ ስጋ ያስረጃል ቢባልም በሳይንስ የተረጋገጠው ግን ተቃራኒው ነው ፣ ስጋ እርጅናን ለማዘግየት የሚያግዙ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል
ስጋ እርጅናን ለማዘግየት የሚያግዝባቸው መንገዶች :-
◈ ቆዳችን እንዳያረጅ ያደርጋል
ስጋ ከፍተኛ ጥራት ያለው ፕሮቲን ስለሚይዝ ማለትም ፕሮሊን እና ግላይሲን የተባሉ አሚኖ አሲዶች ስላሉት ኮላጅንን በደምብ በማምረት ቆዳ እንዳይሸበሸብ እና እንዳያረጅ ያደርጋል
◈ ጡንቻችንን ያስጠብቃል
አንደኛው የእድሜ መግፋት ምልክት የጡንቻ መሳሳት ነው፣ ጡንቻ ደግሞ እድሜያችን በገፋ ቁጥር ጥንካሬያችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስፈልገን ዋነኛው ነገር ነው፤ ስጋ በውስጡ ሉሲን የሚባል አሚኖ አሲድን ይይዛል፤ ይህም ሰውነታችን ጡንቻን እንዲጠግንና እንዲገነባ ትዕዛዝ የሚያስተላልፍ "ኬሚካላዊ ሲግናል" ነው
◈ ጉልበት እንዲኖረን ያደርጋል
እድሜ በገፋ ቁጥር ዋናው የሚያስቸግረን ነገር ጉልበት ማጣት ነው፤ ስጋ ከፍተኛ ሀይል ሰጪ ምግብ ሲሆን ስኳር ከፍ የማያደርግ የማይቋረጥ ሀይል ይለቃል። በተጨማሪም እድሜ ሲገፋ የምግብ ፍላጎት ስለሚቀንስ ትንሽ በልተን ብዙ የምናገኝበት ምግብ ነው
◈ መርሳትና የአዕምሮ መድከምን ይከላከላል
ስጋ ቢ12፣ ካርኖሲን እና ክሬቲንን ስለሚይዝ የማሰብ ፍጥነት፣ ትኩረት እና ንቃት እንዲኖረን ያደርጋል እንዲሁም የማስታወስ ችሎታ መቀነስን ይከላከላል
◈ ሰውነታችን እንዳይዝግ ይከላከላል
ስጋ የካርኖሲን ብቸኛ መገኛ ነው። ይህ ሞለኪውል ስኳር በሰውነታችን ውስጥ ፕሮቲኖችንና ዲ ኤን ኤን እንዳያጠቃ በመከላከል፣ የውስጥ አካላታችን፣ ጡንቻዎች፣ መገጣጠሚያዎች፣ ጭንቅላታችንና ቆዳችን እንዳይዝጉ ይንከባከባል
✅ እንዴት ብንመገበው እነዚህን ጥቅሞች እናገኛለን?
◈ በመጠኑ እና አለፍ እያልን መመገብ (በየቀኑ እና ብዙ መጠን አለመመገብ- በሳምንት ከግማሽ ኪሎ ባይበልጥ ይመከራል)
◈ ከአትክልቶች ጋር አመጣጥኖ መመገብ (አንታይ ኦክሲደንቶችን ከአትክልቶች ለማግኘት እንዲሁም ድርቀት እና የምግብ አለመፈጨት እንዳይኖር ያደርጋል)
◈ ጨው/ቅባት ሳይበዛበት እና ሳያር/በጣም ሳይጠበስ ማብሰል እንዲሁም ጮማ/ስብ የሌለውን ስጋ መብላት
🔴 ስጋ ያስረጃል የሚለው አባባል ከየት እንደመጣ ያውቃሉ?
Hakim Mereja ሀኪም መረጃ
Ethio Hakim