21/02/2023
ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ ፆም የጤንነት እናት የፍቅር እህት የትህትና ወዳጅ ናት ይላል ሲያስተምር። ቅድስት ቤተክርስቲያንን ጨምሮ በተላያዩ መንፈሳዊ የእምነት ተቋማት ሰለ ፆም አስፈላጊነት እና መንፈሳዊ ጥቅም በብዛት ይሰበካል። ምእመናንንም የፆም ስርአት ተሰርቶላቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲፆሙም ይደረጋል።
ታዲያ የፆም ጥቅምም ሆነ አስፈላጊነት ለመንስፈሳዊ ፍሬ ማስገኛ ብቻ ሳይሆን ለስጋዊ ሰውነታችን መታደስ በጤና የመኖር እንዲሁም ከተላያዪ በሽታዎች ለመከላከል እና ለመዳን ይጨምራል። ለዚህም ነው በአለም ላይ በዚህ ሰአት በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ሰዎች ያለ ሀይማኖታዊ አስገዳጅነት ለተለያዩ የጤና ጥቅሞች እየፆሙ የሚገኙት።
ፆም ዘርፈ ብዙ የጤና ጥቅሞች ሲኖሩት የሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ።
🎯የአእምሮ የመስራት ችሎታን በመጨመር የማስታወስ እና የማሰብ ሀይልን ይጨምራል።
🎯ከውፍረት እና ተያይዘው ከሚመጡ በሽታዎችን ለመከላከል ይረዳል።
🎯በሰውታችን ውስጥ የሚካሄድ ብግነት(inflammation) ይቀንሳል። በዚህም ምክንያት ከሚከሰቱ በሽታዎች ለምሳሌ የመገጣጠሚያ ህመም፣ የቆዳ ህመም፣ የመርሳት ችግር ለመቀነስ ይረዳል።
🎯የስኳር የደምግፊት እንዲሁም ሌሎች የረጅም ግዜ ህመም ከሚሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል እንዲሁም በነዚህ ምክንያት የሚወሰዱ መድኒቶችን ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት ይጠቅማል።
🎯በሰውነት ውስጥ ተከማችተው የሚገኙ መርዛማ ነገሮች እንዲወገዱ ያደርጋል።
🎯የሰውነት በሽታ የመከላከያ አቅምን በማጎልበት ጤንነትን ይጠብቃል።
🎯ሰውነታችንን ለፆም በማስገዛት የምናገኘው መንፈሳዊ ጥቅም ዘረፈ ብዙ ከመሆኑም ባሻገር በኑሮአችን እና በጤናችን ላይ የሚያመጣዉ አውንታዊ ለውጥ መረዳት አስፈላጊ ነው።
🎯 ፆም ለየእያንዳንዱ የሰውነት ክፍል እና ሂደት የሚሰጠውን ጥቅም በየሳምንቱ ለማወቅ ገፆን ይከታተላሉ።መልክቱ ከጠቀመወት ለወዳጅዎ ያጋሩ።ገፁን Like and follow በማድረግ አዳዲስ መረጃዎች ያግኙ።
🎯Join me on Telegram https://t.me/HealthNutritionLifeCoach
Dr. Selamawit Eshetu
MD, Nutritionist
Certified Health and Nutrition Life Coach
Selamawit Z. Eshetu