ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic መገናኛ- ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር -308 ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ ስልክ-0940103047 -0954999933

የእርሳስ መያዣዎች (Pencil Grip)  ይህ የእርሳስ መያዣዎች መፃፍ ላስቸገሩ ወይም ፍላጎት ለሌላቸው ልጆች የሚጠቅም ነው።  እነዚህ የእርሳስ መያዣዎች በእጁ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ...
06/11/2025

የእርሳስ መያዣዎች (Pencil Grip)

ይህ የእርሳስ መያዣዎች መፃፍ ላስቸገሩ ወይም ፍላጎት ለሌላቸው ልጆች የሚጠቅም ነው። እነዚህ የእርሳስ መያዣዎች በእጁ ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ይረዳሉ፤ ይህም ለህፃናት ረዘም ላለ ሰአት ለመጻፍ ቀላል ያደርግላቸዋል።

ለልጆች የንግግርና ቋንቋ እድገት የሚያገለግሉ ፍላሽካርዶችና እቃዎች
በፈለጉት ትእዛዝ እንሰራለን።

ፍላሽካርዶች እና መጫወቻዎች 🧩

ፍላሽ ካርድ በተለያየ ቋንቋ ይዘዙን

በተለይ ማውራት ለዘገዩ ልጆች እና ቋንቋ ለማስተማር የሚረዱ

ከድምፅ እስከ ማውራት

☎️0978396662
0991239091

ዴሊቨሪ መገናኛ እና መሪ አያት ብቻ አለን

ለልጆች የንግግርና ቋንቋ እድገት የሚያገለግሉ ፍላሽካርዶችና እቃዎች
በፈለጉት ትእዛዝ እንሰራለን።

ለልጆቻችሁ መማርያ ካርዶችና እቃእቃዎች

Flash cards & toys for Your children

💙 ለልጆቻችሁ ንግግርና ቋንቋ ለማዳበር የሚጠቅሙ ካርዶች
⁃ በአማርኛ (Amharic)
⁃ በትግርኛ (Tigrigna)
⁃ በኦሮምኛ (Oromiffa)
⁃ በእንግሊዘኛ (English)


ፍላሽ ካርዶችን ለማግኘት

https://t.me/JoMaFlashcards


ማሕሌት ስፒች ቴራፒስት

አለማቀፍ ስለ ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ቀን  ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ (Occupational Therapy) 👉🏽ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ምንድነው? ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ በሁሉም የዕ...
28/10/2025

አለማቀፍ ስለ ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ቀን

ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ
(Occupational Therapy)

👉🏽ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ምንድነው?

ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያግዝ የቴራፒ ዓይነት ነው።

👉🏽ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ለማን እና ለምን ይሰጣል ?

ለልጆች
• ጥሩ የእጅ ክህሎቶች እንዲኖራቸው (መፃፍ፣ መቁረጥ፣ የጫማ ማሰሪያ ማሰር) የመሳሰሉትን ያካትታል።
• የስሜት ህዋሳት ሂደትን ለመደገፍ (ለድምፅ፣ ለመንካት፣ ለመንቀሳቀስ ስሜታዊ(Sensitive )የሆኑ ልጆችን ለመርዳት
• ራሳቸውን የመቻል ወይም የመንከባከብ ክህሎቶችን እንዲኖራቸው (መልበስ፣ መመገብ፣ ሽንት ቤት መጠቀም)
• የጨዋታ እና ማህበራዊ መስተጋብር ችሎታዎችን ለማሻሻል።

🔹 ለአዋቂዎች
• ሰዎች ​​ከስትሮክ ወይም ከሌላ ህመም ወይም ከጉዳት በኋላ የዕለት ተዕለት ኑሮ ችሎታቸውን እንዲያሻሽሉ ወይም እንዲያገግሙ ለመርዳት (ለምሳሌ ፦ ምግብ ማብሰል፣ መታጠብ፣ እቃ መግዛት፣ መንዳት)
• የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን እና ጭንቀትን ለመቆጣጠር የአእምሮ ጤና ተግዳሮት ያለባቸውን ሰዎች መደገፍ።
• ሥር የሰደዱ የህመም ሁኔታዎችን እንደ አርትራይተስ፣ ህመምና ድካም ለመቆጣጠር ዘዴዎቸ‍ን ያስተምራሉ።
• ለአካል ጉዳተኞች የስራ ቦታ ማስተካከያዎችን ይመክራል።

👉🏽በኢትዮዽያ ኦኮፔሽናል ቴራፒስቶች እነማን ናቸው?

የኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ ባለሙያዎች የዩኒቨርሲቲ ዲግሪ ያላቸው (በባችለር ወይም ማስተርስ ኦኮፔሽናል (የሙያ) ቴራፒ) እንዲሁም የጤና ቢሮ ፈቃድ ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው።

ፎቶ: ከጎንደር ዩንቨርስቲ የተመረቁ OTs ከአስተማሪዎቻቸው ጋር

በማህሌት አዘነ (ስፒች እና ላንጉጅ ቴራፒስት)
ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ

☎️ 0940103047
0954999933

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?  👉🏽 ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት  ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።...
30/09/2025

ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?

👉🏽 ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።

👉🏽 ከሶስት አመት በታች የሆኑ ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት የሚጠቀሙ ልጆች የተለያዩ የባህርይ እክሎች እና የተግባቦት እክሎች ያጋጥማቸዋል።

የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች

🧩 ከፍተኛ እንቅስቃሴ (እረፍት የለሽ መሆን)
🧩ትኩረት ማድረግ አለመቻል
🧩 ጨዋታዎች ላይ ፍላጎት መቀነስ
🧩ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተግባቦት አለመኖር
🧩ተለዋዋጭ ስሜት
🧩 የመረዳት እክል
🧩 የንግግር እና ቋንቋ መዘግየት
🧩 የተገደበ የአይን ግንኙነት እና ማህበራዊ መስተጋብር
🧩ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም የተገደበ ፍላጎት
🧩ስሜትን የማቋቋም እክል
🧩ለነገሮች ስሜታዊነት (sensitive)

የቨርቹዋል ኦቲዝም መንስኤ

👉🏽ቪርቹዋል ኦቲዝም ህፃናት በሞባይሎች፣ በታብሌት፣ በቴሌቭዥን፣ በኮምፒውተሮች እና በላፕቶፕ ስክሪን ላይ የረዘመ ጊዜ ሲያሳልፉ የሚፈጠር ሁኔታ ነው።

የቨርቹዋል ኦቲዝም ቴራፒዎች

👉🏽በዋነኛነት የባህርይ ቴራፒ እና የስፒች ቴራፒ
👉🏽የስክሪን ጊዜን ማቆም ወይም መገደብ
👉🏽የአካል እንቅስቃሴዎችን መጨመር
👉🏽ፊት ለፊት የሚናገሩበትን መንገድ መፍጠርና ማስተዋወቅ
👉🏽 ምቹና ደጋፊ አካባቢ መፍጠር

በማህሌት አዘነ
ስፒች ላንጉጅ ቴራፒስት

ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ

☎️ 0940103047
0954999933

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

ማሕሌት ስፒች ቴራፒስት

23/09/2025
ከኦቲዝም ጋር ያሉ ልጆች  ጥንካሬዎች ✍አንዳንድ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች የተለያዩ ጥንካሬዎች አሏቸው። ከነዚህም ውስጥ:-🔘ሀይፐርሌክሲያ- ብዙዎች ቃላቶችን በልጅነታቸው ማንበብ ይችላሉ።🔘...
21/08/2025

ከኦቲዝም ጋር ያሉ ልጆች ጥንካሬዎች

✍አንዳንድ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች የተለያዩ ጥንካሬዎች አሏቸው። ከነዚህም ውስጥ:-

🔘ሀይፐርሌክሲያ- ብዙዎች ቃላቶችን በልጅነታቸው ማንበብ ይችላሉ።
🔘ጥሩ የማስታወስ ችሎታ አላቸው፤
🔘በሙዚቃ ፣ በሥነ-ጥበባት ፣ በሳይንስ ፣ በሂሳብ ፣ በኮምፒዩተር የላቁ ናቸው፤
🔘ፍላጎቶቻቸው ላይ ትኩረት ይስጣሉ።
🔘ፊደሎችን ፣ ቁጥሮችን ፣ ቅርጾችንና ቀለሞችን ከእኩዮቻቸው በፊት ማወቅ፤
🔘በተወሰኑ አርዕስቶች ላይ ጥልቅ ዕውቀት አላቸው፤
🔘መረጃን በፍጥነት በእይታ መማር ፤
🔘በልዩ ሁኔታ ጥሩ ትውስታ መኖር (ነገሮችን ለረጅም ጊዜ ለማስታወስ መቻል)፤
🔘ትክክለኛው እና ዝርዝር አቅጣጫን መለየት፤
🔘 ልዩ የሆነ ሐቀኝነትና ታማኝነት፤
🔘ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ማድረግ፤
🔘ችግርን የመፍታት ችሎታ፤
🔘ያልተለመደ የመደነቅ ስሜትና የመሳሰሉት አንዳንድ ከኦቲዝም ጋር የሚኖሩ ልጆች የሚያሳዩቸው ጥንካሬዎች ናቸው።

ለስፒች ቴራፒ ይደውሉ

☎️ 0940103047
0954999933



ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

በዚህ ውድ 'ችግር' ላይ ‘መነገድ "ሃጢአትም-ኢሰብዓዊነትም" ነው ! መላኩ ብርሃኑ    | ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም "እጅግ በጣም ውድ" ነው፡፡ ኦቲዝም ወደአንድ ቤት ሲመጣ በወላጅ ላይ ከሚፈ...
31/07/2025

በዚህ ውድ 'ችግር' ላይ ‘መነገድ "ሃጢአትም-ኢሰብዓዊነትም" ነው !

መላኩ ብርሃኑ

| ኢትዮጵያ ውስጥ ኦቲዝም "እጅግ በጣም ውድ" ነው፡፡ ኦቲዝም ወደአንድ ቤት ሲመጣ በወላጅ ላይ ከሚፈጥረው ስነልቦናዊ ጉዳትና ከማህበራዊ ጫና ባሻገር የልጁን/ልጅቷን ህይወት ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የሚደረገው ትግል እልህ አስጨራሽና ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ነው፡፡ ለዚህ ነው አንዳንዶች “ኦቲዝም የደሃ አይደለም” የሚሉት፡፡

ከ' ኦቲዝም ነው አይደለም' ምርመራና ብያኔ እንጀምር !

አንድ ልጅ የሚታዩበት ልዩ ኹኔታዎች የኦቲዝም ወይም ከኦቲዝም ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ሌሎች የዐዕምሮ እድገት መዛባት ጉዳዮች መሆንና አለመሆናቸውን ለመለየት በሃገር ውስጥ የህክምና ማዕከላት የሚደረገው ምርመራ ዋጋው በጣም ውድ ነው፡፡ ከ20 ሺህ ብር ሊበልጥ ይችላል፡፡

በተጨማሪ ሃገር ውስጥ የሌሉ እንደ yeast overgrowth , zinc, lead እና ሌሎችንም ምርመራዎች ለማድረግ የደምና የሽንት ናሙናን ውጪ ሃገር ድረስ መላክን ይጠይቃል፡፡ ጄኔቲክ ምርመራዎችም አሉ፡፡ አቅም ላላቸውና ማሰራት ለሚችሉ ሰዎች እስከ100 ሺህ ብር ድረስ የሚጠይቅ ምርመራ ሊታዘዝ ይችላል፡፡

ምግብስ ቢሆን ?

በሌላ በኩል ኦቲዝም ያላቸው ልጆች ብዙውን ጊዜ ከአንጀታቸው ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አለባቸው ተብሎ ይታመናል፡፡ አንጀታቸው አስራጊ (Leaky) ነው፡፡ ብዙ ጥናቶች ‘አንጀትን ማከም ኦቲዝምን ማከም ነው’ የሚል ድምዳሜ ላይ ስለደረሱ ህክምናውን ከአመጋገብ ለውጥ ጋር አስተሳስረውታል፡፡

“አንጀት ትንሹ አንጎል ነው” ይባላል ፡፡ የዶክተር ናታሻ ካምፕቤል የምርምር ውጤት የሆነው GAPS (Gut and Psychology Syndrome) የአመጋገብ ስርዓት (Diet) ለኦቲዝም ልጆች ድርድር የሌለበትና ካሉበት ኹኔታ ለማውጣት የሚጠቅም የአመጋገብ እቅድ የያዘ ነው ተብሎ ይታመንበታል፡፡

ስለሆነም በአብዛኛው ለኦቲዝም ልጆች የሚዘጋጀው ምግብ ኬዚን እና ግሉቲን የሚባሉትን ንጥረነገሮች የያዙና ለኦቲዝም መበየኛዎች (Symptoms) መባባስ ምክንያት የሚሆኑ ንጥረነገሮች በአንጀት ቀዳዳዎች ሾልከው ወደ ልጆቹ የደም ስርዓት ውስጥ እንዳይቀላቀሉ፣ ከዚያም ወደአንጎል ሄደው ስርዓቱን እንዳያቃውሱ ከምግብ ዝርዝር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ማስወገድን ይጠይቃል፡፡

ስለዚህ ወተትና የወተት ውጤቶች፣ እንዲሁም ስንዴና ገብስ እንዲሁም ከአጃ የሚሰሩ ማናቸውም ምግቦች የተከለከሉ ናቸው፡፡ ስኳርና ጣፋጭ ነገር (ከተፈጥሮአዊ ጣፋጮች በቀር) በጭራሽ አይፈቀዱም፡፡

በዚህ ሳቢያ ለልጆቹ አማራጭ ምግብ ለማዘጋጀት በርከት ያሉና እነዚህን ሊተኩ የሚችሉ ምግቦችን ማዘጋጀት ይፈልጋል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ከኦሜጋ 3 እና ከቫይታሚን ዲ በተጨማሪ በቁጥር ብዛት ያላቸው ምግብን የሚተኩ ንጥረነገሮችን (ፉድ ሰፕሊመንት) እንዲወስዱ ሊታዘዝ ይችላል፡፡ የእነዚያ ሰፕሊመንቶች ዋጋ ውድ ከመሆኑ ባሻገር ሁሉን ልተው ቢባል ቢያንስ የአንዱ ዋጋ ብቻ በወር እስከ 4 ሺህ ብር ወጪ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ቋሚ ነው፡፡ ይህንን በ5 እና 6 ሰፕሊመንቶች አብዙት፡፡ በዚህ ሳቢያ ለአንድ ኦቲዝም ላለበት ልጅ የሚወጣው የምግብ ወጪ አነድ ቤት ውስጥ ለመላው ቤተሰብ ቀለብ ከሚወጣው ወጪ ሊበልጥ ሁሉ ይችላል፡፡

ትምህርትስ እንዴት ነው?

ኦቲዝም በሽታ ስላልሆነ መድሃኒት የለውም፡፡ ለኦቲዝም የሚደረገው ህክምና በአብዛኛው ቴራፒ ነው፡፡ የስነባህሪ፣ የቋንቋ፣ የንግግር፣ የተግባቦት፣ የማህበራዊ ክህሎት ወዘተ ቴራፒዎች ናቸው ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች ለመርዳት እንደዋና የድጋፍ መስጫ መንገዶች የሚያገለግሉት፡፡ ኦቲዝምን “ውድ’ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ይህ ነው፡፡

እያንዳንዱ ቴራፒ ለዚያውም በቀን ከአንድ ሰዓት ያልበለጠ ሆኖ በወር የሚያስከፍለው ገንዘብ ግን አንድ ልጅን ዓመት የሚያስተምር ገንዘብ ነው፡፡ እንዲያም ሆኖ ረጅም ዓመት የሚፈልግ በመሆኑ ልጁንም ቶሎ ከድጋፍ ማላቀቅ አያስችልም፣ ውጤቱም ቶሎ አይታይም፡፡ ወላጆች ያለ የሌላቸውን ጥሪት ማውጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በቁጥር ጥቂት የሆኑት 'የልዩ ፍላጎት አካቶ' ያላቸው ትምህርት ቤቶችም ቢሆኑ በወር ለአንድ ኦቲዝም ላለበት ልጅ የሚያስከፍሉት ገንዘብ ከመካከለኛው ዜጋ ኪስ በላይ ነው፡፡ አንዳንዱ ለማመንም፣ ለመጥራትም ይከብዳል፡፡ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤቶች እንኳን የማያስከፍሉትን አይነት ገንዘብ የሚያስከፍሉ አካቶ ት/ቤቶችና በኦቲዝም ስም የተቋቋሙ ተቋማት ብዙ ናቸው፡፡

በዚህ ላይ ልጁ ትምህርት ቤት ሲሄድም ሆነ ሲመለስ ሰርቪስ የሚጠቀም ከሆነ ወላጆች ለመጓጓዣው ከመደበኞቹ ህጻናት በእጥፍ እንዲከፍሉ ይደረጋል፡፡ በትከሻቸው ይሸከሙት ይመስል፡፡ በጣም ይገርመኛል መቼም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ልዩነትና አድልዎ በጣም ይሰቀጥጣል፡፡

በዚህ ሳያበቃ 'አካቶ' ብለው የሚቀበሉና ልዩ ዋጋ የሚያስከፍሉት ትምህርት ቤቶችም ቢሆኑ ሊያስተምሩ ከተቀበሏቸውና ኦቲዝም ካለባቸው ልጆች ጋር ትምህርት ቤት አብረው የሚውሉ 'አጋዦችን ( Assistant) እንዲቀጥሩ ወላጆችን ያስገድዳሉ፡፡ አንድ አጋዠ በወር 15 ሺህ ብር ድረስ ሊጠይቅ/ልትጠይቅ ትችላለች፡፡

ምንም ማለባበስ ሳያስፈልግ ኦቲዝም ኢትዮጵያ ውስጥ ላለ ወላጅ እንዲህ ተብሎ የማይገለጽ፣ ሌላው ሌላው ጫና ቀርቶ ከወጪ አንጻር ብቻ ህይወትን በጣም የሚያከብድ ውድ ነገር ነው፡፡ 'ለጊዜው አይወራ' ብለን የምንተወው ሌላ ብዙ ጫናም አለው፡፡ እነግዲህ በኢኮኖሚ በደደቀች ሃገር ለሚገኝ አንድ ለመኖርና ቤተሰቡን ለማኖር በሚንገታገት ወላጅ ላይ ኦቲዝም ሲደረብ ምን ያህል ከባድ ጫና መሆኑን ካሰባችሁት ይበቃል፡፡

እጅግ አስከፊው ነገር ግን ይህ ብቻ አይደለም !!

በዚህ 'ውድ' ችግር ላይ አይናቸውን አጥበው ገንዘብ የሚሰሩ ሰዎች መበርከታቸው ነው በጣም የሚያሳዝነው፡፡ አውቀው፣ ተምረው፣ ፍቃድ አግኝተው ልጆቹን መርዳት ችለው ቢሆን መልካም፡፡ ስለኦቲዝም ምንም ሳያውቁ ወይም ከኔ ባልተሻለ ጥቂት ንባብ ብቻ ተነስተው ቤት ተከራይተውና ማዕከል ከፍተው ‘ባለሙያ ነን’ ብለው ነው 'ቢዝነስ' የሚሰሩት ቲክቶኩንና ሶሻል ሚዲያውን አጣብበውታል፡፡

ያለሙያቸው 'ምርመራ' እናደርጋለን እያሉ 'ኦቲዝም ነው አይደለም' የሚለውን ከባድ ውጤት የሚበይኑ፣ እንችላለን ብለው የቋንቋና የባህሪ ህክምና ( ቴራፒ) ማዕከላት ከፍተው ብዙ ብር የሚቀበሉ ፣ "የንግግር ክህሎት፣ የባህሪ ማረቅ እና ቋንቋን መረዳት የሚያስተምሩ ፣ በአጠቃላይ የልዩ ፍላጎት ባለሙያዎችን እናሰለጥናለን" እያሉ የሚያስተዋውቁና የሚነግዱ 'ሳይማሩ አስተማሪ' ዎች በዝተዋል፡፡

ስለኦቲዝም ተገቢ ግንዛቤ የያዘ የመንግስት ተቋም በሌለባት፣ በቁጥር ከፍተኛ የሆነ'የኦቲዝም ማህበረሰብ' በምርጫ ማጣት ሳቢያ በግለሰብ አገልግሎት ሰጪዎች እጅ ላይ ብቻ በወደቀባት፣ በአጠቃላይ የኦቲዝም ስርጭትና ምጣኔ መረጃ (ዳታ) በሌላት ሃገር በተለይም በአዲስ አበባ ውስጥ 'ኦቲዝምን ቀላልና አትራፊ የንግድ ዘርፍ ' አድርገው ገንዘብ የሚሰበስቡ ሰዎች ቁጥር በጣም ተበራክቷል፡፡ በየዕለቱም ወደዚህ ዘርፍ 'አይንን በጨው አጥቦ' መግባት በርክቷል፡፡

ተስፋ አልባው ወላጅና አሳዛኞቹ ልጆች ደግሞ ባለማወቅ፣ አማራጭ በማጣትና በጭላንጭል ተስፋ ማስታወቂያ እየተከተሉ ከዚህ እዚያ 'ይሻላል' ብለው ይለፋሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከገንዘቡም በላይ በወላጆችም ሆነ በልጆች ህይወትና የነገ ተስፋ ላይ ከባድና አደገኛ አደጋ ደቅኗል፡፡

ክረምት ወር ላይ ስፒች ቴራፒ ና የባህርይ ቴራፒ📍 ያለን ውስን ቦታ ነው ይደውሉና ይመዝገቡልጆች የትምህርት ቤት እረፍት የሚሆኑበት ሰአት ላይ ለልጅዎ ስፒች ቴራፒና የባህርይ ቴራፒ ይፈልጋሉ?...
09/07/2025

ክረምት ወር ላይ ስፒች ቴራፒ ና የባህርይ ቴራፒ

📍 ያለን ውስን ቦታ ነው ይደውሉና ይመዝገቡ

ልጆች የትምህርት ቤት እረፍት የሚሆኑበት ሰአት ላይ ለልጅዎ ስፒች ቴራፒና የባህርይ ቴራፒ ይፈልጋሉ?

እንግድያውስ ጃዚኤል(ማህሌት) ስፒች ቴራፒ ቴራፒዎችን ለመስጠት ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
ቴራፒያችን አንድ ለአንድ ሲሆን ቴራፒው ለወላጆች ከዛ በኃላ መቀጠል የሚችሉበትን መንገድም አመቻችተናል።

ይደውሉና! ይመዝገቡ!

☎️ 0940103047
0954999933



ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic

አድራሻ :- መገናኛ -ሲቲሞል 3ኛ ፎቅ ስለሺ ስህን ህንፃ አጠገብ

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

የኦቲዝም ምልክቶች
28/06/2025

የኦቲዝም ምልክቶች

ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?  👉🏽 ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት  ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።...
21/05/2025

ቨርቹዋል ኦቲዝም ምንድነው?

👉🏽 ቨርቹዋል ኦቲዝም ከሁለት ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት በብዛት ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት በመጠቀም የሚፈጥረ ሁኔታ ነው።

👉🏽 ከሁለት አመት በታች የሆኑ ስክሪን እንደ ቴሌቪዥን፣ ስልክ ፣ ታብሌት የመሳሰሉትን በብዛት የሚጠቀሙ ልጆች የተለያዩ የባህርይ እክሎች እና የተግባቦት እክሎች ያጋጥማቸዋል። በሀገራችንም አሁን ላይ የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች እየታዩባቸው ያሉ ህፃናት እየበዙ ነው ይህም ብዙ ልጆች ከወራት እድሜያቸው ጀምሮ ቲቪና ስልክ ላይ በተለያየ ቋንቋ የተለያዩ ነገሮችን ማየታቸው እና ከእኩዮቻቸው ጋር ተግባቦት አለመኖሩ ለዚህ እክል ተጠቂ እንዲሆኑ እያደረጋቸው ይገኛል ።

የቨርቹዋል ኦቲዝም ምልክቶች
የቨርቸዋል ኦቲዝም ምልክቶች ከአንድ ልጅ አንድ ልጅበየተለያየ ሊሆን ይችላል ። ሆኖም ምልከቶች ከምንላቸው ውስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
🧩 ከፍተኛ እንቅስቃሴ (እረፍት የለሽ መሆን)
🧩ትኩረት ማድረግ አለመቻል ወየረም አጭር ትኩረት መስጠት
🧩 ጨዋታዎች ላይ ፍላጎት መቀነስ
🧩ማህበራዊ መስተጋብር ወይም ተግባቦት አለመኖር
🧩ተለዋዋጭ ስሜት
🧩 የመረዳት እክል
🧩 የንግግር እና ቋንቋ መዘግየት
🧩 የተገደበ የአይን ግንኙነት እና ማህበራዊ መስተጋብር
🧩ተደጋጋሚ ባህሪያት ወይም የተገደበ ፍላጎት
🧩ስሜትን የማቋቋም እክል
🧩ለነገሮች ስሜታዊነት (sensitive)
🧩ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎች (ለምሳሌ፡ እጅ መጠቅለል፣ መሽከርከር)
🧩 ብስጭትና ቁጣዎች ከምልክቶቹ ውስጥ ይጠቀሳሉ።

የቪርቹዋል ኦቲዝም መንስኤ

👉🏽ቪርቹዋል ኦቲዝም ህፃናት በሞባይሎች፣ በታብሌት፣ በቴሌቭዥን፣ በኮምፒውተሮች እና በላፕቶፕ ስክሪን ላይ የረዘመ ጊዜ ሲያሳልፉ የሚፈጠር ሁኔታ ነው
ይህም
1. ከመጠን በላይ የስክሪን ጊዜ፡ ከ 3 አመት በፊት ለዲጂታል ስክሪኖች ለረጅም ጊዜ መጋለጥ በተለይም ያለአዋቂዎች መስተጋብር።
2. የማህበራዊ መስተጋብር እጦት፡ የወላጅ እና የልጆች ውይይት፣ የአካል ጨዋታ እና መስተጋብር መቀነስ።
3. የአካባቢ እንቅስቃሴ አለመኖር ፡ የገሃዱ አለም የስሜት ህዋሳት ልምዶችን የሚገድቡ ስልክና ቲቪ አጠቃቀም ያካትታል ።

ቨርቸዋል ኦቲዝምን መከላከል፡-

🧩 ቲቪ እና ስልክ የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብ
• ከ 2 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የስክሪን ጊዜ አለማድረግ።
• ከ2-5 አመት ለሆኑ ህጻናት ቢበዛ 1 ሰአት/ቀን (በክትትል)።
🧩 ማህበራዊ ተግባቦትና መስተጋብርን ማበረታታት።
• በመናገር፣ በማንበብ፣ በመዘመር እና በአካላዊ ጨዋታ እንዲሳተፉ ማድረግ።
🧩አነቃቂ አካባቢን መስጠት፡-
• አሻንጉሊቶችን፣ የስሜት ህዋሳትን እና ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ ልምዶችን ለልጆች ማሳየትና መአስተማር ።
🧩ጤናማ የስክሪን አጠቃቀም ሞዴል፡
ወላጆች ቲቪና ስልክ አጠቃቀምን በመገደብ ረገድ በምሳሌነት መምራት አለባቸው።

የቪርቹዋል ኦቲዝም ቴራፒዎች

👉🏽በዋነኛነት የባህርይ ቴራፒ እና የስፒች ቴራፒ
👉🏽የስክሪን ጊዜን ማቆም ወይም መገደብ
👉🏽የአካል እንቅስቃሴዎችን መጨመር
👉🏽ፊት ለፊት የሚናገሩበትን መንገድ መፍጠርና ማስተዋወቅ
👉🏽 ምቹና ደጋፊ አካባቢ መፍጠር

ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒ ካስፈለጎ
ይደውሉ 👇👇👇
+251940103047
+251954999933
📍 አድራሻ : መገናኛ ሲቲ ሞል 3ኛ ፎቅ
ጃዚኤል( ማህሌት) ሰፒች ቴራፒ

በማህሌት አዘነ
ስፒችና ላንጉጅ ቴራፒስት

Facebook -ጃዚኤል Speech and Language Therapy
Telegram - http://T.ME/MAHLETSPEECHTHERAPY
Tiktok- Jaziel speech therapy
Instagram- ጃዚኤል (ማኅሌት) Speech and Language Therapy

Telegram group——https://t.me/Jazielspeechtherapyclinic

ፍላሽ ካርዶችንና የቴራፒ መጫወቻ እቃዎች ለማግኘት

https://t.me/JoMaFlashcards
☎️0978396662
0991239091
📍ኦንላይን (ዴሊቨሪ መሪ አያትና መገናኛ)

21/05/2025

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to ጃዚኤል or ማኅሌት Speech and Language Therapy clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram