Dr Kassahun Medium Clinic

Dr Kassahun Medium Clinic Serve with great care and respect

23/07/2025
23/07/2025

ሰላም ዶክተር የ6 ወር ልጅ አለኝ። ያለማቋረጥ ያለቅሳል ፣ ይፈራገጣል ተደጋጋሚ ያስታውከዋል። ካካ ሲል ደም ና ንፍጥ የቀላቀለ ነው : ከጀመረው አሁን 12 ሰዓት አለፈው! በጣም ጨንቆኛል ምን ሊሆን ይችላል? እባክህ በአስቸኳይ እርዳታህን እፈልጋለው"
(የወላጅ ጥያቄ)

👉ህፃናት ላይ ከሚከሰቱ የአንጀት ችግሮች አንዱ አንጀት በአንጀት ውስጥ የመግባት ችግር ነው! ይህም Intussusception በመባል ይታወቃል። አንጀት ወደ አንጀት በመንሸራተት የሚከሰት ከባድ በሽታ ነው።

👉ይህ ችግር ብዙ ጊዜ ምግብን ወይም ፈሳሽን በአንጀት ውስጥ እንዳያልፍ ያግዳል። በተጎዳው የአንጀት ክፍል ላይ ያለውን የደም አቅርቦትን ያቋርጣል።

👉ይህም ወደ የአንጀት መበስበስ ወይም ሞት ፣ የሆድ እቃ መቁሰል እና የአንጀት መበሳት ሊያስከትል ይችላል።
👉በመጨረሻም እስከ ሞት ድረስ የሚያደርስ ከባድ ህመም ነው።

✍ጥያቄ -1: ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?

👉ምልክቱ በልጆች እና በአዋቂዎች ሊለያይ ይችላል።

👉ከዚህ በፊት ሙሉ ጤናማ የነበረ ህፃን የመጀመሪያው ምልክት በድንገት በሆድ ህመም ምክንያት ከፍተኛ ለቅሶ ሊሆን ይችላል።
👉 የሆድ ህመም ያለባቸው ህጻናት ሲያለቅሱ ጉልበታቸውን ወደ ደረታቸው ይስባሉ።
👉ብዙ ጊዜ ከ15_20 ደቂቃ ባለው ጊዜ ህመሙ ይመጣል እና ይሄዳል።
👉እየቆየ ሲሔድ ረዘም ላለ ጊዜ ሊቆይ ይችላል።
👉ሌሎች ተጨማሪ ምልክቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ:

👉👉ደም እና ንፍጥ የተቀላቀለ ሰገራ
👉👉ተደጋጋሚ ትውከት
👉👉የሆድ እብጠት ወይም መነፋት
👉👉ድካም ወይም የሰውነት መዛል

✍✍ሁሉም ህፃናት ሁሉም አይነት ምልክቶች ይኖራቸዋል ማለት አይደለም።
👉አንዳንድ ጨቅላ ሕጻናት ግልጽ የሆነ ህመም ላይኖራቸው ይችላል።

✍ጥያቄ-2: ወደ ህክምና መሔድ ያለባቸው መቼ ነው?

👉ይህ ችግር ድንገተኛና አፋጣኝ ሕክምና የሚያስፈልገው አደገኛ ህመም ነው።

👉ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ ለሕክምና ዕርዳታ ወደ ጤና ተቋም መሔድ ያስፈልጋል።

👉በጨቅላ ህጻናት ላይ የሆድ ህመም ምልክቶች በተደጋጋሚ ጉልበቶቹን ወደ ደረቱ በመሳብ እና ማልቀስ ሊያካትቱ እንደሚችሉ ማስታወስ ተገቢ ነው።

✍ጥያቄ-3: መንስኤው ምን ሊሆን ይችላል?

👉አንጀት ረጅም ቱቦ ቅርጽ ያለው የሰውነት ክፍላችን ነው።
👉በintussusception የሚፈጠረው አንዱ የአንጀት ክፍል - ብዙውን ጊዜ ትንሹ አንጀት - በአቅራቢያው ባለው የአንጀት ክፍል ውስጥ ሲንሸራተት የሚከሰት ችግር ነው።
👉 ይህ አንዳንድ ጊዜ ቴሌስኮፒ ተብሎ ይጠራል ምክንያቱም ሊሰበሰብ የሚችል ቴሌስኮፕ አንድ ላይ በሚንሸራተቱበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው።

👉በብዛት ምክንያቱ አይታወቅም።

👉በልጆች ላይ በአብዛኛው በበልግ እና በክረምት ወቅት ይከሰታል።
👉 ይህ ችግር ያለባቸው ልጆች የጉንፋን ምልክቶች ወይም የአንጀት ኢንፌክሽን ምልክቶች ስለሚኖሯቸው አንዳንዶች በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቫይረስ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉ መገመት ይቻላል።

✍ጥያቄ-4 : ህክምና ባይደረግላቸው ሊከሰት የሚችለው ችግር ምን ሊሆን ይችላል?

👉ችግር የተከሰተበት የአንጀት ክፍል የደም አቅርቦት ሊቋርጥበት ይችላል።
👉ሕክምና ካልተደረገለት የደም እጦት የአንጀት ግድግዳ እንዲሞት ያደርጋል።
👉 ይህም የአንጀት ግድግዳ መበሳት ሊያመራ ይችላል።
👉ይህም የሆድ እቃ ቁስለት (Peritonitis) ያስከትላል።
👉ይህ ቁስለት ለሕይወት አስጊ የሆነ፣ ለሞት የሚያበቃ እና አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልገው ችግር ነው።

✍ጥያቄ-5: ችግሩ በምን ምርመራ ይረጋገጣል?

👉ችግሩን ለማ

28/05/2025
28/05/2025
እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።
20/04/2025

እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም በዓል ይሁንላችሁ፣ ይሁንልን።

17/04/2025

ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቂያ
የስራ መደቡ መጠሪያ ጽዳት
የቅጥር ሁኔታ በኮንትራት
ደመወዝ በስምምነት
የስራ ሰአት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
ቦታ 40/60ኮንዶሚኒየም

13/02/2025

ምች (cold sore) ከሚከሰቱ የቆዳ ኢንፌክሽኖች መካከል ዋነኛዉ ሲሆን በተለይም የላይኛዉ ወይም የታችኛዉ የከንፈር ጠርዝ ከፊታችን ቆዳ ጋር በሚገናኝበት አካባቢ ላይ በሚወጡ ውኃ የቋጠሩ ጥቃቅን ቁስለቶች በማስከተል ይታወቃል።

በተለምዶ የምች በሽታ የምንለው (Cold sores ) የሚከሰተው የኸርፒስ (Herpes) ቫይረስ 1 በሚባሉ በሽታ አምጭ ተዋህስያን እንደሆነ የሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የምች በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች...

የላይኛዉን ወይም የታችኛዉን የከንፈር ጠርዝ በ ቀኝ ወይም ግራ በበኩል ከፊት ቆዳ ጋ የሚያገናኘዉ ቦታ አካባቢ የመለብለብ፣የማሳከክ ወይም ጨምድዶ የመያዝ ስሜት ሊሰማዎት ይችላል።

ከዚህም ከ 24 ሰዓታት በኋላ ከታች ቀልተዉ ዉኃ የቋጥሩ ጥቃቅን የቁስለቶች ስብስብ ይፈጠራል።

በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከተፈጠሩ በኋላ በቀላሉ በመፈንዳት ፈሳሽ ሊያፈልቁ ይችላሉ ከዛም ወድያዉ በመድረቅ በቅርፊት ይሸፈናሉ።

ከላይ ከተጠቀሱት ምልክቶች በተጓዳኝ የራስምታት፣ትኩሳት ፣የድካም ስሜት እንዲሁም በአንገት ወይም በብብት ዉስጥ የሚገኙ ሊምፍ ኖድ የሚባሉ ዕጢዎች እብጠት ሊያስከትል ይችላል።

በምች የሚመጡ ቁስለቶች ከ2-4 ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ ያለ ጠባሳ ይድናሉ።

በምች ለሚመጡ ቁስለቶች በቤታችን ምን ማድረግ እንችላለን?

-የሕመም ማስታገሻ

በምች በሽታ ሚመጡን ቁስለቶች በተያያዘ የሚሰማዎትን ሕመም ለመቀነስ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ በፋርማሲ የምናገኛችውን አይቡፐሮፈን(Ibuprofen) እና አሴታሚኖፈን (Paracetamol) የሚባሉ የሕመም ማስታገሻዎችን በፋርማሲ ባለሙያው ትዕዛዝ መሠረት መጠቀም

-ማቀዝቀዝ

ከምች በሽታ ጋር ተያይዞ የሚመጣዉን በቁስለቱ ዙርያ የሚከሰት የቆዳ መቅላት እና መቆጣትን ለመቀነስ በቀዝቃዛ ዉኃ በተነከረ ጨረቅ ወይም በበረዶ ቁራጭ በከቀን ዉስጥ ለተወሰነ ግዜ ከ5-10 ደቂቃ በቦታዉ ላይ መያዝ እንደሚረዳ የቆዳ ሐኪምዎች ይናገራሉ።

-እራስን ከጭንቀት ነፃ ማድረግ

የአዕምሮ ዉጥረትን መቅነስ የሰዉነትን በሽታ መከላከል አቅም እንደሚጨምር በጥናትዎች ተረጋግጧል።

ስለዚህም የሚያዝናኑን ነገሮችን በመፈለግ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ልንከላከለው እንችላለን።

(የጤና ወግ)

30/11/2024

ፎሮፎር (Seborrheic dermatitis)

ፎሮፎር በባሕሪው ጠንካራ ያልሆነ ብዙም ምልክት የሌለው እና ትንንሽ ብናኞች ያሉት ሊሆን ይችላል፤ይህ የተለመደው ዓይነት ፎሮፎር ሲሆን ዳንድረፍ (dandruff) በመባል ይታወቃል።

በተቃራኒው ደግሞ ጠንካራ የሚባለው የፎረፎር ዓይነት አብዛኛውን የራስ ቆዳችንን እንዲሁም ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ላይ ጭምር ሊከሰት ይችላል፤ ቅርፊቶቹም ወፍራም እና ከራስ ቆዳችን ጋር የተጣበቁ ሊሆኑ እንደሚችሉ የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ብዙውን ግዜ ፎሮፎር ከሁለት ሳምንት እስከ አንድ ዓመት ባሉ ሕጻናት እና ከጉርምስና ዕድሜ በላይ በሆኑ ግለሰቦች ላይ ይከሰታል።

አብዛኞቹ ፎሮፎር የሚኖርባቸው ግለሰቦች ሌላ ተጓዳኝ ህመም አይኖራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግን ከHIV ፣ ከፓርኪንሰን ፣ ከሚጥል ህመም (Epilepsy) ፣ ከጭንቀት ጋር ተያይዞ ሊከሰት እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

የፎሮፎር መንስኤ በትክክል ይሄ ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ከቆዳችን ጋር ተስማምተው በሚኖሩ (normal flora) የፈንገስ ዓይነት (Malassezia) ምክንያት ይከሠታል ተብሎ ይታሰባል።

ፎሮፎር ወዝ አመንጪ ዕጢዎች (Sebaceous glands) ተከማችተው በሚገኙበት የአካል ክፍሎቻችን (የራስ ቆዳ ፣ ፊት፣ ደረት አካባቢ፣ የላይኛው የጀርባችን ክፍል ፣ የውጭኛው የጆሮ ክፍል ፣ ብብት ፣ ጡት ስር ፣ በላይኛው የጭን ክፍል እና ብልት መካከል በሚገኘው ቦታ) ላይ ይከሰታል ።

ፎሮፎርን መድኃኒትነት ያላቸው መታጠቢያ ሻምፖዎችን ለምሳሌ (ketoconazole 2%, Selenium sulfied, Ciclopirox , Zinc pyrithione) በመጠቀም መቆጣጠር እንደሚቻል የህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ሻምፖውን ተቀብተን ከ5-10 ደቂቃ አቆይተን መታጠብ ይህንንም በሳምንት ከ 2-3 ጊዜ መደጋገም ያስፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የማሳከክ ስሜት ካለው፣ጠንካራ የሚባለው የፎሮፎር ዓይነት ከሆነ፣ከራስ ቆዳችን ውጪ ከተከሰተ፣ተጓዳኝ ህመሞች ካሉ እንዲሁም ሕጻናት ላይ ከተከሰተ የቆዳ ሐኪም በሚያዘው መሠረት ተጨማሪ መድኃኒቶች ያስፈልጋሉ።

ፎሮፎር እንዳይመላለስብን ማድረግ ያለብን ምልክቶቹ እስኪጠፉ በሻምፖ መታጠብ ፤ ምልክቶቹ ከጠፉ በኋላ ሻምፖውን በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም ፎሮፎር እንዳይመላለስ ይረዳል ።

በፎሮፎር ምክንያት የፀጉር መነቃቀል የተለመደ አይደለም ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ የማሳከክ ስሜት ካለ ጊዜያዊ የሆነና ተመልሶ የሚተካ የፀጉር መነቃቀል ሊያስከትል ይችላል ።

በመጨረሻም የቆዳ ሐኪም ሳያማክሩ መድኃኒቶችን ባለመጠቀም ቆዳዎትን ከተጨማሪ ጉዳት መጠበቅ እንዳለቦት የቆዳ ህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ።

HakimEthio

እርስዎም ስለ ፎሮፎር ያልዎትን አስተያየት ያካፍሉን!!

በአይን ስለሚደረጉ የመድኃኒት ጠብታዎች አጠቃቀም!የአይን ጠብታ ተጠቅመው ያውቃሉ? የአይን ጠብታ አጠቃቀምን በተመለከተ ምን ያህል ግንዛቤ አለዎት? እስኪ ዛሬ በአይን ስለሚደረጉ የመድኃኒት ጠ...
17/11/2024

በአይን ስለሚደረጉ የመድኃኒት ጠብታዎች አጠቃቀም!

የአይን ጠብታ ተጠቅመው ያውቃሉ? የአይን ጠብታ አጠቃቀምን በተመለከተ ምን ያህል ግንዛቤ አለዎት? እስኪ ዛሬ በአይን ስለሚደረጉ የመድኃኒት ጠብታዎች አጠቃቀም ጥቂት እንበልዎት!

1. የሚጠቀሙትን የአይን ጠብታ መድኃኒት ይለዩና ክዳኑን ይክፈቱ፡፡ ሰው ባጠገብዎ ካለ ጠብታውን ሌላ ሰው ቢያደርግልዎ ይመረጣል፡፡

2. ጠብታውን ለማድረግ እንዲመች በጀርባዎ ተንጋለው ይተኙ ወይንም አንገትዎን ወደ ላይ ቀና ያድርጉ፡፡

3. ጠብታውን የሚያደርገው ሰው እጁን ከታጠበ በኃላ በምስሉ ላይ እንደሚታየው በአንድ እጁ ጠብታ የሚጨመርበትን አይን የታችኛው ቆብ ወደታች መጎተት አለበት፡፡ በዚህ ጊዜ ህመምተኛው አይኖቹን ከፍቶ ወደ ላይ ማየት አለበት፡፡

4. በምስሉ ላይ እንደሚታየው ጠብታ የሚያደርገው ሰው በሌላ እጁ የጠብታውን ብልቃጥ በመያዝ በአይን ኳስ /እንክብል/ እና በታችኛው የአይን ቆብ መካከል ባለው ክፍተት አንድ ጠብታ ማድረግ፡፡ በዚህ ጊዜ የጠብታ ብልቃጡ ጫፍ ከአይን ሽፋሽፍትም ሆነ ከሌላ የአይን አካል ጋር መነካካት የለበትም፡፡

5. በስዕሉ ላይ እንደሚታየው ጠብታው ከተደረገ በኃላ ታማሚው አይኑን በስሱ በመጨፈን አይንና የላይኛው የአፍንጫ አካል የሚገናኙበት ቦታ ላይ በጠቋሚ ጣቱ ከ 2 እስከ 3 ደቂቃ መጫን አለበት፡፡

6. ከአንድ በላይ የጠብታ አይነት በአንድ አይን ላይ በተመሳሳይ ጊዜ የሚያደርጉ ከሆነ በእያንዳንዱ ጠብታ መካከል ቢያንስ የ 5 ደቂቃ ልዩነት መኖር አለበት፡፡
ይህ ሳይሆን ቀርቶ መድኃኒቶቹ በአንድ ላይ ተከታትለው ከተጨመሩ ከኃላ የተደረገው ጠብታ ቀድሞ የተደረገውን ጠብታ ሳይሰራ ከአይን አጥቦ ሊያወጣው ይችላል፡፡

7. መድኃኒቱን ከተጠቀሙ በኃላ እንዳይቆሽሽ ከድነው በመያዣው ውስጥ በመክተት በጥንቃቄና ልጆች በማይደርሱበት ቦታ ያስቀምጡ፡፡ አንዳንድ የግላኮማ የአይን ጠብታ መድሃኒቶች በፍሪጅ ውስጥ መቀመጥ ሊኖርባቸው ስለሚችል መድሃኒቱን ሲገዙ ባለሙያውን ያማክሩ፡፡

8. በምንም ሁኔታ በሀኪም ያልታዘዘ የአይን ጠብታን ወይንም ለሌላ ሰው የታዘዘን ጠብታ ከመጠቀም ይቆጠቡ።

ዶ/ር አርጋው አበራ: የአይን ህክምና ስፔሻሊስት
Youtube:

Share your videos with friends, family, and the world

09/11/2024

የጉበት በሽታ እና እርግዝና

Heptatis B ምንድነው?

👉ጉበትን የሚያጠቃ ቫይረስ (heptatis B virus) በሚባል የሚከሰት የበሽታ አይነት ነው

በምን በምን ይተላለፋል?
🫱በደም ንክኪ
🫱ጥንቃቄ የጎደለው የግብረ ስጋ ግንኙነት
🫱ስለታማ ነገሮችን በጋራ መጠቀም (እፅ የሚጠቀሙ ሰዎች ለዚ በጣም የተጋለጡ ናቸው )
🫱በሥራ ጊዜ በስለታማ ነገሮች መወጋት(needle stick injury)
🫱በሰውነት ፈሳሽ (ከላብ በስተቀር ያሉ ፈሳሾች)
🫱ከእናት ወደ ልጅ በእርግዝና ጊዜ

ተጋላጭ የሆኑት እነማናቸው?
🫱የጤና ባለሙያ
🫱 ሴተኛ አዳሪዎች
🫱እፅ ተጠቃሚዎች
🫱በቫይረስ የተጠቃች እናት ሆድ ውስጥ ያለ ልጅ

በምን እንከላከለው?

👉ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦች Hep B ቅድመ መከላከያ ክትባት መውሰድ
👉የሚያስተላልፉትን ነገሮች መከላከል

ክትባቱ መች መች ይሰጣል (schedule)?

🫱1st dose (የመጀመሪያው) በመጀመሪያ ቀን
🫱2nd dose (ሁለተኛው) በወሩ
🫱3rd dose (ሶስተኛው) ሁለትኛውን ከወሰዱ ከ6ወር በሁአላ

ሕክምናውስ ከእናት ወደ ልጅ ?

👉ፅንሱ 7 ወር (28ሳምንት) ሲሞላው የእናትየው በደሟ ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ከ >200,000 iu/ml በላይ ከሆነ እና HepeAg (active virus) ተሰርቶ ፖሰtቭ ከሆነ እናትየው ከ28ሳምንት ጀምሮ እስከምትወልድ ድረስ ፀረ-ቫይረስ መድሃኒት እንዲሰጣት ይደረጋል ይህም ከእናት ወደ ልጅ ጉበት በሽታ የመተላለፉን ነገር ይቀንሳል (የእናትየው የቫይረስ መጠን ከመጠን በላይ መቀነስ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ይረዳል)

👉ከዚ በተጨማሪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ልጁ እንደተወለደ hep b ክትባት እና Ig G ለልጁ እንዲሰጥ ይደረጋል

ከዛ በሁአላ ልጁ ከፀረ 5 ክትባቶች (penatavalent) በ6, 10, 14ኛው ሳምንት እንዲወስድ ይደረጋል :: ይህም ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ይረዳል 👌

Reference
👉Uptodate
👉Obsteteric managment protocol for hospital 2021
👉IPC participant manual
👉Immunization in practice manual 2023

ትኩረት ለጉበት!
እናት ጤና ልጅም ደና ❤️

Address

BoleBulbula Infront Of Medhanialem Church
Addis Ababa

Telephone

+251974070001

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Kassahun Medium Clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Kassahun Medium Clinic:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram