26/07/2025
ከበርካታ የሙዝ ጠቀሜታዎች መካከል ጥቂቶቹን ከዚህ
እንደሚከተለው
ለማየት እንሞክራለን፡፡1. ለአእምሮ እድገት
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ
የፖታሺየም ንጥረነገርን
ይዟል፡፡ ይህም ንጥረ
ነገር የአንጐልን የሥራ ብቃት ለማሻሻል እና ለማሳደግ
እንዲሁም ንቁና ጤናማ አዕምሮ እንዲኖረን በማድረግ
ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡
2. ለስትሮክ
በሙዝ ውስጥ ያለው ፖታሺየም፣ የደም ሥርዓትን
በማስተካከል ባልታሰበ ሁኔታና በድንገት የሚከሰተውን
የስትሮክ ችግር ለመከላከል ያግዛል። ሙዝ በሰው
ልጆች የአመጋገብ ሥርዓት ውስጥ ተካቶ ዘወትር
ለምግብነት የሚውል ከሆነ፣ በስትሮክ ምክንያት
የሚመጣውን ድንገተኛ ሞትና የአካል ጉዳት ከ50-60
በመቶ ለመቀነስ ያስችላል፡፡
3. ለደም ግፊት
ሙዝ በተፈጥሮው በውስጡ የሚይዘው ዝቅተኛ
የጨው መጠን በመሆኑ የደም ግፊትን ለማረጋጋት
ይረዳል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በውስጡ ያለው
ፖታሺየም የደም ግፊትን ለማስተካከልና በግፊት ሳቢያ
የሚከሰቱ ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል ከፍተኛ
ጠቀሜታ አለው፡፡
4. ለጨጓራ ህመም
አብዛኛዎቻችን ሙዝ ከበድ ያለ ምግብ እንደሆነ
በማሰብ፣ ሙዝ የጨጓራ ህመማችንን
እንደሚያባብስብን ስንናገር እንደመጣለን፡፡ ይሁን እንጂ
ሙዝ ለጨጓራ ችግሮች ሁነኛ መፍትሔ ነው። ሙዝ
በባህርይው በጣም ለስላሳ በመሆኑ በጨጓራ ላይ
መጨናነቅን የማይፈጥር ሲሆን የጨጓራ አካባቢን
በመሸፈን፣ የጨጓራ ውስጥ አሲድን በማስተካከልና
በማመጣጠን የጨጓራ ቁስለት እንዳይፈጠር ለማድረግ
ያስችላል፡፡
5. ለድብርት
ሙዝ በውስጡ የሚይዘውና ትራይፕቶፋን የተባለው
ንጥረ ነገር በሰውነታችን ውስጥ ሴሮቶኒን የባለ
ሆርሞን እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ ይህ ሆርሞን አይነተኛ
ተግባሩ ሰውነታችንን ከድካምና ከድብርት በማላቀቅ
ወደተሻለ ስሜት ውስጥ እንድንገባ ማድረግ ነው፡፡
6. ለሆድ ድርቀት
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው ፋይበር ለምግብ መፍጨት
ሥርዓታችን ከፍተኛ ጠቀሜታን ይሰጣል፡፡ የምግብ
መፍጨት ሥርዓትን የሚያከናውኑት የሰውነታችን
ክፍሎች በቂ የውሃ መጠን እንዲኖራቸው በማድረግ
ሆድ ድርቀትን ይከላከላል፡፡ አንጀት የተለሳለሰ እንዲሆን
በማድረግ ከሰውነታችን መውጣት የሚገባቸው
አላስፈላጊ ነገሮች (ቆሻሻዎች) እንዲወገዱ ለማድረግ
ይረዳል፡፡
7. ለስኳር ህመም
ሙዝ በውስጡ ከፍተኛ ቫይታሚን B6 የያዘ ነው።
ይህም በደም ውስጥ የሚኖረውን ከፍተኛ የስኳር
መጠን እንዲቀንስ በማድረግ፣ በሰውነታችን ውስጥ
የሚገኘውን የስኳር መጠን ለመቆጣጠር ያስችለናል፡፡
ከስኳር መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰተውን የጠዋት
ህመምንም ያስቀራል፡፡
8. ሙዝና ደም ማነስ
በሙዝ ውስጥ የሚገኘው የብረት ማዕድን ጠቀሜታው
በደማችን ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው
የሔሞግሎቢን ምርት እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡ ይህም
በሔሞግሎቢን እጥረት ሳቢያ የሚከሰተውን የደም
ማነስ እንዳይከሰት ያደርጋል፡፡
9. ሙዝ ለስካር
ሙዝ ከወተትና ከማር ጋር ተደባልቆ ለምግብነት
ሲውል በከፍተኛ መጠጥ ወይም በስካር ሳቢያ
የሚከሰትን ሃንግኦቨር (ያደረ ድምር) በቀላሉ
ያስወግዳል፡፡ በመጠጥ ሳቢያ የተጐዳን ሰውነት
እንዲነቃቃና ብርታት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድም
ሙዝ ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል፡፡ የሲጋራ እና መሰል
ሱሶች ተጠቂ የሆኑ ሰዎች ሱሱን ለማቆም እንዲችሉ
ሙዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
10. ለሞቃታማ አየር
በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች
ሙዝን ቢመገቡ ሰውነታቸው ሙቀቱን እንዲቋቋም
በማድረግ፣ የተረጋጋና የተስተካከለ የሰውነት ሙቀት
እንዲኖረን ያደርገናል፡፡