27/10/2025
👇👇ጡት የማጥባት ተቀመታውን ምን ያህል ያዉቃሉ?
♦️ጡት ማጥባት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ህፃናት በተወለዱ በአንድ ሰዓት ውስጥ የእናት ጡት ወተት መጀመር አለባቸው፡፡
♦️ የእናት ጡት ወተት በውስጡ ከፍተኛ የሆነ ንጥረ ምግብ ከመያዙም ባሻገር ህፃናት በተለዩ በሽታዎች እንዳይጠቁ ከፍተኛ የሆነ በሽታን የመከላከል አቅም በውስጡ አለው፡፡
♦️ከዚህም በተጨማሪ ጡት ማጥባት ለህፃናቱም ሆነ ለእናቶች እጅግ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡
👉👉ለእናቲቱ ያለው ጠቀሜታ:
• ጡት ማጥባት እናቶችን ከማህፃንና ከጡት ካንሰር በሽታ ይከላከላል
• በእናቲቱ እና በተወለደው ህፃን መካከል ከፍተኛ ግንኙነት እንዲኖር ይረዳል
• ከእርግዝና በፊት ወደ ነበራት ክብደት እንድትመለስ ይረዳል
• ተጨማሪ ወጪ እንዳታወጣ ይጠቅማል
• ጥሩ እረፍት እንዲኖራት ያስችላል
👉👉ለህፃኑ ያለው ጠቀሜታ በጥቂቱ:
• የጡት ወተት በውስጡ ከፍተኛ የሆነ በሽታን የመከላከል አቅም አለው፡፡ ይህም ህፃናት በቀላሉ በበሽታ እንዳይጠቁ ይረዳል፡፡
• ህፃናት የተሟላ ንጥረ ምግብ ያገኙበታል ይህም ህፃናት እስከ ስድስት ወር ያለምንም ተጨማሪ ምግብ እንዲቆዩ ያደርጋል፡፡
• ህፃናት ከፍተኛ የአዕምሮ ዕድገት እንዲኖራቸው ያስችላል
• ህፃናት በአለርጂክ፣ በአስም ወይም አተነፋፈስን በሚያውክ በሽታ እናዳይጠቁ ይከላከላል
• የጡት ወተት ለህፃናቱ የምግብ ፍጭት ሂደት ቀላል ነው የህፃናት አላስፈላጊ ውፍረትን ይከላከላል
• የተቅማጥ እና ተውከት በሽታን ይከላከላል
ስለዚህ ከተወለዱበት አንስቶ እስከ ስድስት ወር ድረስ የእናት ጡት ወተት ብቻውን ፣ ስድስት ወር ላይ የእናት ጡት ወተት ብቻውን በቂ ስለማይሆን ከጡት ወተት በተጨማሪ የተመጣጠነ ምግብ ያስፈልጋቸዋል ይህም የተመጣጠነ ምግብ በጣም ለስላሳና በቀላሉ ሊመገቡት የሚያስችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡