25/04/2026
አንድ ሰው የሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ ቢገኝበት ምን ይከሰታል? ምንስ ማድረግ ይኖርበታል?
የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ ውጤትዎ ፖዘቲቭ ከሆነ ምን ማድረግ ይኖርብዎታል፦
- መደበኛ ክትትል ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው
- የጉበት ሥራ ምርመራ እና የቫይረስ መጠን ክትትል (Viral load) ያስፈልጋል
- አንዳንድ ታካሚዎች የፀረ-ቫይረስ መድኃኒት ሊያስፈልጋቸው ይችላል
- የጉበትን ጤና ለመጠበቅ ከአልኮል መጠጥ መራቅ ያስፈልጋል
- የቤተሰብ አባላት ምርመራ ማድረግና ክትባት መውሰድ ይኖርባቸዋል
መደበኛ ምርመራ የጉበት ካንሰርን አስቀድሞ ለመለየት ይረዳል
መከላከል ይቻላል!
- የሄፓታይተስ ቢ መውሰድ (አስተማማኝ እና ውጤታማ)
- ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ማድረግ
- በእርግዝና ወቅት ምርመራ ማድረግ
- ሹል ነገሮችን አብሮ አለመጠቀም
በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የምንሰጣቸው አገልግሎቶች፦
- የሄፓታይተስ ቢ ምርመራ
- የሄፓታይተስ ቢ ክትባት
- በጉበት ስፔሻሊስት እንዲሁም በተላላፊ በሽታዎች ስፔሻሊስት የሚሰጥ ክትትል እና ህክምና
ቅድመ ምርመራ ሕይወትን ያድናል!
📍 ይመርመሩ, ይከተቡ, ጉበትዎን ይጠብቁ !
ላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል
በሀኪምች ህብረት ለህብረተሰብ ጤና የቆመ
ለተጨማሪ መረጃ :
Telegram | Facebook | LinkedIn | TikTok | Website |Youtube