08/03/2025
ጉዳዮ፤ የቢሮ ኪራይ ድጋፍ ስለማሰባሰብ
የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር ከአእምሮ ህመም ጋር ውጤታማ ኑሮ በሚኖሩ ሰዎች የተመሠረተ የብዙኃን ማህበር ነው።
ይህ ማህበር በ2011 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በርካታ አባላት አሉት። የማህበሩ አባላት የአቻ ለአቻ ድጋፍ (peer support) የሚያገኙበት፣ እርስ በርስ ተገናኝተው ተሞክሯቸውን በመጋራት የተሻለ የጤና ድጋፍ የሚያገኙበትን ቢሮ ተከራይቶ እየሠራ ይገኛል። የቢሮ ኪራዩን ከአባላት፣ ከበጎ ፈቃደኛ ግለሰቦች፣ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት ድርጅት መጠነኛ ድጋፍ ከሚያገኘው ገቢ እየከፈለ ነበር።
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ የቢሮ ኪራይ በመጨመሩ የሚከፍለው ገንዘብ እጥረት ስለገጠመው ወደ መላው ህብረተሰብ ጉዳዩን ይፋ ለማውጣት ተገዷል።
ይህን ማህበር በመደገፍ የበኩላችሁን ተሳትፎ እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ወርሃዊ ክፍያው 28250 ብር ሲሆን የአመት ክፍያው 339,000 ብር ነው።
ድጋፍዎትን በሚከተለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር በማስገባትና ያስገቡበትን የባንክ ደረሰኝ (ስክሪንሾት) በቴሌግራም ቻናላችን ላይ እንድትለጥፉምን ወይም በፌስቡክ ገጻችን (inbox) እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
ስለምታደርጉልን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000276683636
የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር
በአካል ልታገኙን ለምትፈልጉ የማህበሩ አድራሻ
አዲስ አበባ፣ ቄራ፣ ኪዳኔ ምህረቱ ህንጻ፣ 6ኛ ፎቅ ላይ ነው።
website: www.mhsua.org
ስልክ: +251945 565656
የማህበሩ አባል መሆን የምትፈልጉ ይህንን የአባልነት ቅፅ መሙላት ትችላላችሁ፤
https://docs.google.com/.../1FAIpQLScwmiUYsFmp2t.../viewform
የጋራ ድምጻችን ለአእምሮ ጤና!!!