ጤና ለአዳም

ጤና ለአዳም Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጤና ለአዳም, Adiss Abeba, Addis Ababa.

ለጠቅላላ እውቀትኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከ...
09/06/2025

ለጠቅላላ እውቀት
ኢንተርኔትን ስንጠቀም ልንጠነቀቅ የሚገቡን 10 ጉዳዮች

1. የግል መረጃችንን ከማጋራት መቆጠብ፤

2. የምናውቃቸውን ሰዎች ብቻ ማነጋገር

3. በኦንላይን ብቻ የምናውቃቸውን ሰዎች ከፍተኛ እምነት አለመጣል፤

4. የጓደኝነት ጥያቄን በአካል ከምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንቀበል፤

5. ሁልጊዜ ስለምንለጥፈው ነገር በጥንቃቄ ደጋግሞ ማንበብ

6. በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ መለያዎች ላይ የግላዊነት(privacy 🔏) መጠበቂያዎችን መጠቀም፤

7. ሁሉም ሰው በኦንላይን እሱ እንደሆነ የሚነግረን ሁሉ እውነት አድርጎ አለመቀበል፤

8. ተገቢ ያልሆነ ይዘትን ሲያጋጥመን ወዲያውኑ ሪፖርት እናድርግ፤

9. ከጓደኞቻችን እና ከቤተሰባችን ጋር ስንመለከታቸው ምቾት የሚሰጡንን ምስሎች ብቻ ማጋራት፤

10. የይለፍ ቃላችንን በፍጹም ከማጋራት መቆጠብ፤

ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና...
02/06/2025

ሰውዬው በሚስቱ ሞያ ይማረራል፡፡ ገና ወደ ቤቱ ለመምጣት ሲያስብ የሚበላው እንጀራና ወጥ ትዝ ሲለው ሐሞቱ ፍስስ ይላል፡፡ «እንግዲህ ለዚያ ሊጥ ልሂድለት» ብሎ ይመጣል፡፡ ይህ ነገር ሰለቸውና ከሚስቱ ጋር ተፋታ፡፡ ወደ ጓደኛውም ቤት ሄደ፡፡ ጓደኛው አልጋ አንጥፎ ተቀበለው፡፡
ማታ ራት ቀረበ፡፡ ምን የመሰለ ነጭ ጤፍ ላይ አልጫና ቀዩ ተጋድሞ ቀረበለት፡፡ በአንድ በኩል ቃሪያው፣ በአንድ በኩል ስልጆው፣ በአንድ በኩል ፍትፍቱ፣ በአንድ በኩል አተር ክኩ ተሰለፈ፡፡ «ወይ ሞያ እኔማ ኖርኩ አይባልምኮ» እያለ ያማርር ጀመር፡፡ «አንተማ ታድለህ» ይለዋል ጓደኛውን፡፡ «ይሁን እስኪ» ይላል ያኛውም፡፡ ጠላው ሲቀርብ ደግሞ እያደነቀ ጠጣ፡፡ «ከኖሩ ላይቀር እንዲህ ነው» ይል ጀመር፡፡ ያችንም ባለሞያ ሚስት በምስጋናና በአድናቆት አረሰረሳት፡፡

በልተው ሊያጠናቅቁ ሲሉ ጋባዡ ሊጠጣበት ያነሣው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡ ደነገጠ፡፡ ሚስት ከጓዳ መጣች፡፡ «ምንድን ነው የተሰበረው?» አለች፡፡

«ያ የምትወጅው ብርጭቆ ተሰበረ፡፡» አላት ባሏ በተስለመለመ ድምፅ፡፡ ተናደደችና አንዴ በጥፊ አላሰችው፡፡ ጓደኛው ደነገጠ፡፡ «እንዲህ ሰብረህ ሰብረህ የአባት የናቴን ስጦታ ጨረስከው፡፡ አንተ ምን ታደርግ ተንቀባርረህ ከነ ጓደኛህ ትልፋለህ» እያለች ቁም ስቅሉን ታሳየው ጀመር፡፡ ባልዬው ፀባይዋን ያውቃልና ዝም አለ፡፡ ያም ጓደኛው «ምን ለብርጭቆ ደግሞ ነገ ይገዛል፤ ዋናው ጤና ነው» አለ ነገር ያበረደ መስሎት፡፡ «አንተ ደግሞ አርፈህ ተቀመጥ፤ ሚስትህን እንደዚህ አማረሃት ይሆናል ይኼኔ፤ ቀላዋጭ» አለችና አቀመሰችው፡፡ ተፈታተነው ስሜቱ፡፡ ግን እንግድነቱ በልጦበት «ኧረ የኔዋስ እንዳንቺ» አለና ጀምሮ ተወው፡፡ ወደ ጓዳ ገባችና አንድ ፍልጥ ይዛ መጣች፡፡ እስኪ ጨርሰው አለቺው፡፡ ዓይኑ ተቁለጨለጨ፡፡ «እንዳንቺ የባሰባት አይደለችም» ሲላት ፍልጡን ይዛ መጣች፡፡

ይህንን ሲያይ ባልዬው «ቀስ ብለህ አምልጥ» አለው፡፡
በዚያ ሌሊት እየገሠገሠ የሚስቱ እናት ጋ ሄደ፡፡

እናቲቱም «ምነው ልጄ» አሉት
«እማማ፤ ከሌሊት ፍልጥ፣ የቀን ሊጥ ይሻለኛል ብዬ መጣሁ፡፡ አላቸው ይባላል፡፡
ወዳጄ ያለህን ካላሰብከው የባሰው ላይ ትወድቃለህ ያልኩ ለዚህ ነው፡፡
እስኪ ወዳጄ ያለህን ዕወቀው፤ አክብረው፤ አሟጠህ በሚገባ ተጠቀምበት፤ በዚያ ኑርበት፤ አጊጥበት፡፡ ከዚያ ሌላውን ለመያዝ ፈልግ፡፡ ባለህ የማትረካ ከሆንክ ግን ሩጫህ የተሻለ ነገር ፍለጋ ሳይሆን ሌላ ነገር ፍለጋ ብቻ ይሆናል፡፡

"በእጅ የያዙት ወርቅ....."

ወዳጄ ውዷ ሚስትህን አጥብቀህ ያዝ የባሰ አለና!
ከተመቻችሁ ፎሎ ላይክ ሼር ማረጉ አይሠሳ
👇👇👇👇👇👇

01/06/2025

25ቱ የአለማችን የሳይንስ አባቶች
----------------------------//////--------------
1. ጋሊሊዮ ጋላሊ = የፊዚክስ አባት
2. አሪስጣጣሊስ = የባዮሎጂ አባት
3. ዳቢር ኢብን ሀያን = የኬሚስትሪ አባት
4. ሚካኤል ፋራዳይ=የኤሌክትሪክ ሲቲ አባት
5. ዳዮፋንተስ = የአልጄብራ አባት
6. ኢዩክሊስድ = የጂኦሜትሪ አባት
7. ሒፖክራተስ = የህክምና አባት
8. ፍላሎረንስ ናይቲንግ= የነርሲንግ እናት
9. ግሪጎር ሜንዴል = የጄኔቲክስ አባት
10. ፊጣጎራዝ = የቁጥር አባት
11. ኒኮስ ማኪያቬሊ = የፖለቲካ ሳይንስ አባት
12. ኢሜል ደርካይም = የሶሺዮሎጂ አባት
13. አዳም ስሚዝ = የኢኮኖሚክስ አባት
14. አይዛክ ኒውተን = የካልኩለስ አባት
15. ካርል ማርክስ = የኮሙኒዝም አባት
16. ማርኮኒ = የሬዲዮ አባት
17. ኧርነስት ሩዘርፎርድ = የኒውክሌር ፊዚክስ አባት
18. አልበርት ኢንስታይን = የአንፃራዊ ቲዎሪ አባት
19. ማክስ ፕላንክ = የኳንተም ቲዮሪ አባት
20. ዱሜትሪ ሜንዴሌቭ = የፔሬዲክ ቴብል አባት
21. ቬሳልየስ = የአናቶሚ አባት
22. መሀመድ ዮኑስ = የማይክሮ ክሬዲት አባት
23. ሜሪ ኩሪ = የኒውክሌር አባት
24. ሉክ ሆዋርድ = የሜትሮሎጂ አባት
25. ኧርነስት ሀኬል = የኢኮሎጂ አባት

©️ከዕውቀት ማህደር

"አልችልም ስትልበሰው ዘንድ የማይቻል በእኔ  ዘንድ ይቻላል ይልሃል::          (ሉቃስ 18_27)"እጨነቃለሁ ስትልየሚስጨንቅህን ሁሉ በኔላይ ጣል ይልሃል::             (1ኛ ጰ...
01/06/2025

"አልችልም ስትል
በሰው ዘንድ የማይቻል በእኔ
ዘንድ ይቻላል ይልሃል::
(ሉቃስ 18_27)

"እጨነቃለሁ ስትል
የሚስጨንቅህን ሁሉ በኔ
ላይ ጣል ይልሃል::
(1ኛ ጰጥ 5:7)

"ደክሞኛል ስትል
አሳርፍሃለሁ ይልሃል::
(ማቴ 11:28 _30)

"አቅቶኛል መቀጠል አልችልም ስትል
ጸጋዬ ይበቃሃል ይልሃል:;
(2ኛ ቆሮ 12:9)

"ማድረግ አልችልም ስትል
ኃይልን በምሰጥህ በእኔ ሁሉን
ትችላለህ ይልሃል::
(ፊል 4:13)

"ብቃት የለኝም ስትል
ብቃት አለህ ይልሃል::
(2ኛ ቆሮ 9:8_9)

"ፈርቻለሁ ስትል
የፍርሃት መንፈስ
አልሰጠሁህም ይልሃል::
(2ኛ ጢሞ 1:7)

"እራሴን ይቅር ማለት አልችልም ስትል
እኔ ይቅር እልሀለሁ ይልሃል::
(1ኛ ዮሐንስ 1:9)

ይሄ ለኔ አይገባኝም ነበር ለምን እኔ ላይ ሆነ ስትል
ነገር ሁሉ ለበጎ ነው ይልሃል::
(ሮሜ 8:28)

"ብለሃት የለኝም ስትል
ጥበብን እሰጥሃለሁ ይልሃል::
(1ኛ ቆሮ 1: 30_31)

02/04/2024
02/04/2024
11/05/2023

Address

Adiss Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጤና ለአዳም posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram