Akaki kality Executive werda 9 youth lege

Akaki kality Executive  werda 9 youth lege "Akaki kality w_9 youths League_ብልፅግና"

"የተከልናቸዉን ችግኞችን የማንከባከብ ግዴታችንን እንወጣለን"          ወጣት ማቴዎስ ጌታቸውበቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከከተማ ዉበት እና አረንጕዴ ልማት ጽ/ቤት ...
11/11/2023

"የተከልናቸዉን ችግኞችን የማንከባከብ ግዴታችንን እንወጣለን"

ወጣት ማቴዎስ ጌታቸው

በቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ከከተማ ዉበት እና አረንጕዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በመንገድ አካፋይ የተተከሉ ችግኞችን የማንከባከብ ተግባር አከናዉነዋል።

ህዳር 1/3/2016ዓ.ም

በፕሮግራሙ ከ12ቱም ወረዳ የተወጣጡ የሊጉ አባላት የተገኙ ሲሆን ችግኞች በፀሐይ እንዳይደርቁ ለማድረግ ዉሃ የማጠጣት እና አረምን የማረም ስራ ተሰርተዋል::

የአቃቂ ቃሊቲ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ሰብሳቢ ወጣት ማቴዎስ ጌታቸው እንደገለፀው ወጣቱ ኃይል የተተከሉ ችግኞችን በማንከባከብ ዓርአያ መሆን አለበት ብለዋል:: ወጣት ማቴዎስ አክለዉም ብልፅግና ፓርቲ ከወጣቶች ጋር በመሆን የተለያዩ ዉጥኖችን እስከ ግብ ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ይገኛል በማለት ገልፀዋል:: ከዚህ አኳያ የአረንጕዴ አሻራ ስራ ዉጤታማ እንዲሆን በየአከባቢ የሚገኘው ወጣት የበኩሉን አወንታዊ አስተዋፅዖ እንዲያደርግም ጥሪ አስተላልፈዋል::

በእለቱም የከተማ ዉበት እና አረንጕዴ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው በላይ በእግድነት የተጋበዙ ሲሆን በክረምት መርሀ ግብር የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብና ውሀ በማጠጣት ከተማችንን እንደ ስሟ ውብ ማድረግ የሁላችንም ሀላፊነት ነው ብለዋል::

"Biqiltuuwwan dhaabne kunuunsuun dirqama keenya haa baanu!"

Dargaggoo Maatiwoos Geetaachoo

Liigiin Dargaggoo Badhaadhinaa Kutaa Magaala Aqaaqii Qaallittii waajjira Magariisuu fi Miidhagina Magaalaa waliin ta'uun sagantaa kunuunsa biqiltuuwwan walakkessa daandiitti dhaabamanii raawwataniiru

Sagantaa kana irratti miseensonni Liigichaa Aanaawwan 12 irraa walitti bobba'ani kan hirmaatan yoo ta'u, biqiltoota bishaan obaasuun kunuunsaniiru.

Walitti qabaa Liigii Dargaggoo Kutaa Magaalichaa Obbo Maatiwoos Geetaachoo ergaa dabarsaniin,dargaggoonni biqiltoota dhaabuu qofa osoo hin taane kunuunsuu irrattis fakkeenya adda duree ta'uu qaba jedhaniiru.
Paartiin Badhaadhinaa dargaggoota waliin karoorfatee hojiiwwan hedduu galmaan gahuuf kan hojjetu ta'uu eeranii,kaayyoon Ashaaraa magariisaa akka milkaa'u dargaggoonni nannoo jiran hundatti shoora isaanii akka bahan waamicha dabarsaniiru.

Dura bu'aan waajjira Magariisummaa fi miidhaginaa Kutaa Magaalaa Aqaaqii Qaallittii Obbo Geetaachoo Balaay saganticha irratti argamuun, biqiltoota yeroo gannaa dhaabaman bishaan obaasuun,aramuufi kunuunsuun miidhagina Magaalaa eeguun qoodha hunda keenyaati jechuun ergaa dabarsaniiru.

Akaki kality prosperity

09/09/2022

አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያውያን ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በአንድነት የሚያልፉበት እንደሚሆን እምነታችን ነው - የሀገራት አምባሳደሮች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያውያን ያጋጠሟቸውን ፈተናዎች በማለፍ ለሰላምና ልማት በአንድነት የሚሰሩበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ገለጹ፡፡

ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ለኢትዮጵያውያን የመልካም አዲስ ዓመት ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሮቹ በመልዕክታቸው÷ ኢትዮጵያውያን በመጪው አዲስ ዓመት በተባበረ መንፈስ አንድነቷ የተጠበቀ ጠንካራ ሀገርን ለማስቀጠል የሚሰሩበት እንደሚሆን እምነታችን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርክሂን አዲሱ ዓመት ለመላ ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የጤና፣ የብልጽግና፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያውያን ያገጠሟቸውን ፈተናዎች በብቃት የመወጣት አቅም ያላቸው ህዝቦች ናቸው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንዶኔዥያ አምባሳደር አል ቡሲራ ባስኑር በበኩላቸው÷ አዲሱ ዓመት ኢትዮጵያውያን ያላቸውን መልካም ገጽታና እሴት የሚያስተዋውቁበትን አጋጣሚ እንደሚፈጥር አንስተዋል፡፡

በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በጋራና በትብብር መንፈስ የተሻለች ሀገር እንዲገነቡ እድል እንሚፈጥርም አመላክተዋል፡፡

“የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ኢትዮጵያውያን አዲስ ተስፋ የሚሰንቁበት ጊዜ ነው” ያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ የአየር ላንድ አምባሳደር ኒኮላ ብሬናን ናቸው።

ዓመቱ የኢትዮጵያውያን ሰላምና መረጋጋትን እንዲሁም አንድነታቸውን ይበልጥ የሚያጠናክሩበት እንዲሆን ያላቸውን መልካም ምኞት ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ምክትል ኃላፊ ሄይኮ ኒትስሽኬ ÷በአዲሱ ዓመት የተሟላ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ማየት ምኞታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በአዲሱ ዓመት ሀገራቸውን በተባባረ ክንድ ወደ ተሻለ ፖቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት የሚያሸጋግሩበት እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ÷ አዲሱ ዓመት ለመላ ኢትዮጵውያን የሰላምና የብልጽግና እንዲሆንላቸው የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።

30/08/2022
25/08/2022
25/07/2022
21/07/2022
21/07/2022

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki kality Executive werda 9 youth lege posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category