16/11/2025
፦ የተቀነባበሩ ምግቦች ያለ እድሜ ለሚከሰት የአንጀት ካንሰር ያጋልጣሉ!
❓ የጥናቱ መነሻ ጥያቄ
• ከመጠን ባለፈ ሁኔታ የተቀነባበሩ ምግቦችን (Ultraprocessed foods) ያለ እድሜ (ከሃምሳ በታች) ለሚከሰት የአንጀት ካንሳር (early-onset colon cancer) ያጋልጡ ይሆን?
🔍 የጥናቱ ቀልፍ ውጤቶች
👩⚕️በቁጥር 29,105 ለሚደርሱና እድሜያቸው ከ50 ዓመት በታች ለሆኑ ተሳታፊዎች የአንጀት ምርመራ (endoscopy) የተሰራ ሲሆን የተቀነባበሩ ምግቦችን በከፍተኛ መጠን የሚወስዱት ሴቶች በትንሹ ከሚወስዱት አንፃር የተለመዱት የአንጀት ካንሰሮች በ45% ጨምረው ተገኝተዋል።
በጥናቱ ውጤት መሰረት ምን ማድረግ ይገባል?
• የተቀነባበሩ ምግቦችን (የታሸጉ ቀላል ምግቦች፣ ፈጣን ምግቦች፣ የተቀነባበረ ስጋ፣ ለስላሳ መጠጦችና የተቀመመ ፓስታ) በእጅጉ መቀነስ ያለ እድሜ የሚከሰትን የአንጀት ካንሰርን ለመካላከል ሊረዳ ይችላል።