Addis Home Care

Addis Home Care Professional Home-based Health Care provider in Addis Abebe Ethiopia.

Happy New Year!
15/09/2023

Happy New Year!

21/07/2022

U. T. I /Kidney Infections

22/04/2022

የልባችንን ጤና ሁሌም መከታተል እና መጠበቅ ሁሌም አንዘንጋ።

በቪዲዮ ላይ የተጠቀሱትን የጤና ምክር በመተግበር የልባችንን ጤና እንጠብቅ ።

የጭንቅላ እጢ ምልክቶች   አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ /ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማ...
16/04/2022

የጭንቅላ እጢ ምልክቶች

አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ /ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚባለው ነገር መታወቅ አለበት፡፡

👉 ራስ ምታት:

👉 የእይታ ችግር:

👉 የሚጥል በሽታ ካለ

👉 የሰውነት መስነፍ:

👉 መንገዳገድ (ባላንስ አለመጠበቅ)፡

👉 ምንም ምልክት አለመኖር፡- ለሌላ ተብሎ በተሰራ ምርመራ አጋጣሚ የአንጎል እጢ ሊገኝ ይችላል። የእጢው እድገት እና ባህሪ ታይቶ ኦፕራስዮን ወይም ሌላ የሕክምና አማራጭ ሊያስፈልገው ስለሚችል ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

👉 መስማት መቀነስ:- አዲስ ወይም ቀስ በቀስ እየባሰ የሚሄድ የመስማት ችግር

👉 ሽንት ወይም ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል

👉 ትንታ (chocking):
👉 ማስመለስ:

👉 የመናገር ችግር:

👉 የማስታወስ ችግር (መርሳት)፡

👉 የፊት እና አገጭ ላይ ከባድ ህመም መሰማት

👉 የንቃት መቀነስ:

👉 የጭንቅላት መጠን መጨመር:

👉 ከልክ ያለፈ የሰውነት መጠን መጨመር:

15/04/2022

እራሳችንን ከተለያዩ አደንዛዥ ዕፅዎች በመጠበቅ የህይወት ግቦቻችንን እናሳካ!

ሲጋራን /ትንባሆን ልክ እንደዚ ለስነ-ውበት መጠቀም እየቻልን ለምንድን ነው ወደ ሳንባችን እያስገባን እድሜያችንን በግማሽ ምናሳጥረው??? 🤔🤔🤔
12/04/2022

ሲጋራን /ትንባሆን ልክ እንደዚ ለስነ-ውበት መጠቀም እየቻልን ለምንድን ነው ወደ ሳንባችን እያስገባን እድሜያችንን በግማሽ ምናሳጥረው??? 🤔🤔🤔

በወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂበወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂ ወይም Seasonal allergy እየተባለ የሚጠራው የህመም አይነት ጉንፋን መሰል ምልክቶች ያሉት ወ...
10/04/2022

በወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂ

በወቅቶች መቀያየር ምክንያት የሚፈጠር አለርጂ ወይም Seasonal allergy እየተባለ የሚጠራው የህመም አይነት ጉንፋን መሰል ምልክቶች ያሉት ወቅቶች ሲፈራረቁ ወይም በዓመት አንዴ የሚከሰት የአለርጅ አይነት ነው፡፡

ምልክቶች

📌 የጆሮ ህመም፣ራስ ምታት፣የጉሮሮ መከርከር
📌 የአፍንጫ መደፈን፣ያለማሽተት እንዲሁም ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ መብዛት
📌 ማስነጠስ፣የአክታ ስሜት መሰማት፣ማሳል
📌 የአይን ማሳከክ፣መቅላት፣ ማስለቀስ እና ማበጥ
📌 ድብርት
📌 የድካም /አቅም ማጣት/ ስሜት
📌 የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ወቅታዊ የአፍንጫ አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች

📌 እርጥበት እና ቅዝቃዜ
📌 ጭስ
📌 የዛፍ ፣የአበባ/አረምና የሳር ሽታዎች
📌 በሞቃታማ ወቅት የአፍንጫ አለርጂን የሚያባብሱ

መፍትሄው

📌 የሚያስነሳብንን ነገሮች በመለየት እሱን ለመከላከል መሞከር
📌 ቫይታሚን ሲ አዘውትሮ መውሰድ
📌 በተቻለን መጠን የአየር ሁኔታው የማይስማማን ከሆነ ቦታ ለመቀየር መሞከር
📌 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
📌 በቅዝቃዜ እና በብናኝ ለሚፈጠር አለርጂ አልፎ አልፎ እንፋሎት መታጠን

በዶ/ር አለ

"ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና" - ዶ/ር ሲሳይ ተክሉ ፣ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት ከማህፀን ውጪ እርግዝና የሚንለው እርግዝና ከማህፀን ውጪ ሲፈጠር ሲሆን ስንደ ስያሜው፣ በአብዛኛው...
07/04/2022

"ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና" - ዶ/ር ሲሳይ ተክሉ ፣ የማህፀን እና ፅንስ ስፔሻሊስት

ከማህፀን ውጪ እርግዝና የሚንለው እርግዝና ከማህፀን ውጪ ሲፈጠር ሲሆን ስንደ ስያሜው፣ በአብዛኛውን ደግሞ ይሔ የሚሆነው በማህፀን ቱቦ ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ የማህፀን ቱቦዎች ውስጥ እርግዝና ሲከሰት ፅንሱ እድገቱን መቀጠል የማይችል እና በቱቦዎቹ ውስጥ በቆየ ቁጥር ደግሞ በእናትየው ጤና ላይ አደጋ የሚያስከስት ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና በአፋጣኝ ሕክምና የሚያስፈልገው ሲሆን ፅንሱን ማስቀጠልም ስለማይቻል፣ ፈጥኖ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ወደሚቻልበት የህክምና ማዕከል በመሄድ በመድሐኒት ወይም በቀዶ ህክምና ፅንሱን ማውጣት ተገቢ ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና ምልክቶች
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል፡፡ ይሔም ማለት እናቶች በፅንስ ክትትል ወቅት የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ ሲያደርጉ የሚታወቅ ክስተት ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡

ከዚህ ውጪ በተረፈ ምልክቶቹ (ካሉ) የሚታዩት በአብዛኛው ከ4ኛ እስከ 12ኛው የእርግዝና ሳምንት ነው፡፡

እነዚህም ምልክቶች፡-
- የወር አበባ አለማየት
- ማቅለሽለሽ እና ሌሎች የእርግዝና ምልክቶች
- በአንድ ትከሻ ጫፍ ላይ ህመም ስሜት መሰማት
- በአንድ በኩል የሚያጋድል የሆድ ህመም
-ደም ወይም ቡናማ ፈሳሽ በማህፀን መፍሰስ
-በሚሸናበት ወቅት ምቾት መንሳት ሊሆኑ ይቸላሉ፡፡

ይሄ በዚህ እንዳለ እነዚህ ምልክቶች የማህፀን ውጪ እርግዝና ምልክቶች ብቻ አይደሉም፣ የሆድ ዕቃ/ጨጓራ መታወክን ጨምሮ ሌሎች ህመሞች ምልክቶች ናቸው፡፡

ሕመሙን መኖሩን የምናረጋግጠው ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች አይተን በሽንት የእርግዝና ምርመራ ካደረግን በኋላ የፅንስ አልትራሳውንድ ምርመራ በማድረግ ነው፡፡

ከማህፀን ውጭ የሚፈጠር እርግዝና መንስኤዎች ግልፅ ባይሆኑም አልፎ አልፎ ሲከሰቱ የሚስተዋለው ዋናው መንስኤ በማህፀን ቱቦዎቹ ውስጥ ያለ ችግር ምክንያት ነው፡- ይሄም ማለት ቱቦዎቹ ሲጠቡ ወይም በሆነ ምክንያት ሲዘጉ ነው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ አንዳንድ ለሕመሙ ተጋላጭነት የሚዳርጉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
- በማህፀን ቱቦዎች ላይ የሚከሰት ኢንፌክሽን/ በአብዛኛው በአባላዘር በሽታዎች ምክንያት የሚመጣ፣
- ከዚህ ቀደም የተከሰተ ከማህፀን ውጭ እርግዝና- ይሔ ሲሆን ድጋሚ የሚከሰትበትን ዕድል በ 10 በ 100 ይጨምረዋል፡፡
- በቀዶ ህክምና ወቅት የሚደርስ የማህፀን ቱቦ ጉዳት - በተለይም የማህፀን ቱቦ መዘጋት
- የማህንነት ህክምና
- ማጨስ
- እድሜ መጨመር ፣ የእናቶች እድሜ ከ35-40 በላይ ሲሆን

ህክምናው

ሀኪምዎ ለእርስዎ የሚሆን የህክምና አይነት ከማህፀን ውጪ እርግዝናው እንደተከሰተበት ቦታ እና እንዳጋጠመው የጤና ውስብስብ ችግር ላይ ተመረኩዞ በመድሃኒት ወይም በቀዶ ህክምና ህክምና ያደርግሎታል፡፡

በመድሃኒት፡- ጊዜው ያልገፋ በማህፀን ቱቦ ውስጥ ለተከሰተ፣ ያልፈነዳ፣ ሊያድግ የማይችል ፅንስ ሲኖር
ቀዶ ህክምና ደግሞ በመድሃኒት ለመወገድ ትልቅ የሆነ ፅንስ ሲሆን ወይም ፅንሱ ያለበት የማህፀን ቱቦ የፈነዳ

ድጋፍ
ከማህፀን ውጪ እርግዝና ከተከሰተ በኃላ እናቶች ላይ ሀዘንን እና ትካዜን ማየት የተለመደ ቢሆንም ብዙ የሚቆይ ነገር ግን ሆኖ አይስተዋልም፡፡ ሀኪምዎ ጋር በመሄድ ስለወደፊት የእርግዝና እቅዶች እንዲሁም ስለ ስነልቦናዊ ድጋፍ ምክክር ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ስለተከታይ እርግዝና መሞከር

ተከታይ እርግዝና ከባለቤትዎ ጋር ለመሞከር ስታስቡ ሁለታችሁም አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባችኋል፡፡

የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞችየጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን።ጡት ማጥባት ለልጅሽ1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላ...
04/04/2022

የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞች
የጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን።
ጡት ማጥባት ለልጅሽ

1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ
2. ከአለረጂክ ይከላከላል።
3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል
4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል
5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል
6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል

ጡት ማጥባት ላንቺ

7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል
8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል
9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል
11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል
12. ወጪ ቆጣቢ ነው።

(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

16/03/2022

➕➕ የተረሳ እንክብል ➕➕

🖲የሚዋጥ የወሊድ መቆጣጠሪያ ለምትወስዱ ሰዎች በመሀል መውሰድ ብትረሱ እንደ ወሊድ መቆጣጠሪያው አይነት ተጨማሪ ጥንቃቄ ያስፈልጋችሁዋል

🖲ባለ 1 ሆርሞን ወይም ለምታጠባ እናት የሚሆነውን እንክብል የምትጠቀሙ ከሆነ፣ አወሳሰድ ላይ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

🖲በተመሳሳይ ሰአት ካልተወሰደ ማለትም፣ ከሚወሰድበት ሰአት ለ3 ሰአት እንኳን ከተዛነፈ እርግዝና የመፈጠር እድል ይኖራል

🖲በዚህን ግዜ፣ መዳኒቱን መውሰድ ሳታቋርጡ ለ 2 ተከታታይ ቀናት ግንኙነት ከማድረግ መቆጠብ ወይም ተጨማሪ የእርግዝና መከላከያ፣ እንደ ኮንዶም እና ፖስት ፒል መጠቀም አለባችሁ።

🖲ባለ ሁለት ሆርሞን መከላከያ የሚወሰድ ከሆነ ደሞ፣ አንድ ቀን ብቻ ሳትወስዱ ከረሳችሁ በማግስቱ ሁለት እንክብል ወስዶ የተቀረውን መቀጠል።

👉አብዛኛውን ግዜ ተጨማሪ መከላከያ መውሰድ አያስፈልግም

👉ነገርግን የተዘለለው እንክብል የወር አበባ መቶ ከሄደ የመጀመሪያው ሳምንት አካባቢ ከሆነ ፣ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ፣ ኮንዶም ወይም ፖስት ፒል መጠቀም ያስፈልጋል።

🖲ሁለት ቀን እና ከዛ በላይ ከረሳችሁ ደሞ፣ የረሳችሁትን እንክብል ትተውት እና ካስታወሳችሁበት ቀን ጀምሮ በቀን በቀን እየወሰዳችሁ። ለሚቀጥሉት 7 ቀናት ከግንኙነት መቆጠብ። ካልተቻለ ደሞ በግንኙነት ግዜ ተጨማሪ መከላከያ ያስፈልጋል።
ዶ/ር ሰይፈ

04/03/2022

አስፈላጊውን የኮቪድ-19 የክትባት መጠን በመውሰድ ራስዎን ከበሽታው ይከላከሉ!
ዛሬውኑ ይከተቡ!

02/03/2022

💊 ለመሆኑ_ስለ_ጤናዎ_ምን_ያህል_ያውቃሉ?

የጤና ባለሙያ ማግኘት የሚፈልጉት መቸ ነው? የህመም ስሜት ሲሰማዎ ወይስ በእቅድ?

✔️ ልብ ይበሉ! ምልክት ሳያሳዩ ብዙ አመታትን በሰውነታችን ውስጥ ያሉ ገዳይ እና ጎጅ በሽታዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ስለ ጤናዎ ለማወቅ የህመም ስሜትን አይጠብቁ። ጤና የሁሉ ነገር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ጤናን በቀላሉ መጠበቅም ሆነ ማበላሸት ይቻላልና!

🔆 ለእርስዎ የሚጠቅመዎት ቀድመው ስለ ጤናዎ ማወቅ እንጅ ሲታመሙ መድሀኒት መጠቀም ብቻ አይደለም።

🔆 ለእርስዎ የሚጠቅመዎት የአኗኗር ዘይቤዎትን ምቹና የተስተካከለ በማድረግ እራስዎን ከበሽታ ነፃ ማድረግ እንጅ ችግሩ ከመጣ በኋላ መጣደፍ ብቻ አይደለም።

🔆 ለእርስዎ የሚጠቅመዎት ቀድመው በቂና ጠቃሚ የጤና መረጃዎችን ማግኝት እንጅ ሲታመሙ ምክር እና ህክምና ማግኘት ብቻ አይደለም።

#ስለነዚህ ይወቁና ይጠቀሙባቸው
1. የጤና ትምህርት
2. የእረፍትና እንቅልፍ ጊዜ
3. የአካል እንቅስቃሴ
4. የአመጋገብና አጠጣጥ ዘይቤ
5. ስለ ክትባት
6. ጭንቀትና ውጥረትን መቆጣጠር ስለመቻል
7. ሰአት አጠቃቀም
8. ሌሎችንም በስርአቱ በመጠቀም ጤናን ቀለል ማድረግ ይቻላል።

ጤና በባለቤቱ እጅ ነውና እኛም በየቀኑ ጠቃሚ መረጃ በማድረስ ዋና የጤና አጋርዎ ለመሆን ዝግጁ ነን።

አዲስ የቤት ለቤት ህክምና
ADDIS HOME CARE

Phone - 09 44 08 07 44 / 09 29 36 44 17

22/02/2022

የአእምሮ ጤንነት እና ቡና
አሉታዊ እና አዉንታዊ ተፅዕኖ

17/02/2022
17/02/2022
15/02/2022
14/02/2022

አዲስ የቤት ለቤት ህክምና አገልግሎት

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች:

🔆 ድህረ ቀዶ ጥገናና ማንኛውንም ቁስል ማጠብና መቀየር ( Wound Care )

🔆 የስኳር ፣ ደም ግፊትና የልብ በሽታ ታማሚዎች የህክምና አገለገሎቶች መስጠትና አመጋገብ ማስተማር

🔆 የመጀመሪያ እርዳታ መስጠትና በሃኪም የታዘዙ መድሃኒቶች በታዙልዎት አግባብና ሰአት ባሉበት መጥተን መስጠት

🔆 በሃኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶች አጠቃቀም ማስተማርና መስጠት

🔆 የኮሮና ታማሚዎችን መንከባከብ

✅ ፅኑ ህሙማን እንክብካቤ
✅ ፊዚዮቴራፒ አገልግሎት
➡️ለስትሮክ
➡️ ለስብራት
➡️ ለወገብ ህመም
➡️ ለጡንቻ መሸማቀቅ
➡️ ለአካል ጉዳተኞች
➡️ ለተለያዩ ህሙማን

✅ የኦክስጅን አቅርቦት እና ህክምና

✅ ለደም ግፊትና ለስኳር ክትትልና እንክብካቤ

✅ የምግብ ቱቦ ማስገባትና መመገብ

✅ የሽንት ቱቦ ማስገባትና መቀየር

🔆 ሌሎች አገልገሎቶችን እንደየ በሽታው አይነት በብቁ እና ልምድ ባካበቱና የሙያ ስነምግባሩን በተላበሱ የጤና ባለሙያዎች ባሉበት ድረስ መጥተን አገልግሎት እንሰጣለን፡፡

ለበለጠ መረጃ - 0929364417

10/02/2022

የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ
___________
ከታህሳስ 21 - 27/2014 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከየካቲት 04/2014 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 0118275936 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት፣ የመለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡

ለፈጣንና ወቅታዊ መረጃዎች
በቴሌግራም t.me/healthinovation
በግሩፓችን t.me/HIVN19
በFb fb.com/andualemsew/ ይከታተሉን።

Address

Addis Ababa
0001

Telephone

+251929364417

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Home Care posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Addis Home Care:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram