04/11/2025
ዓይን አውጣነት በተግባር !
================
በዚህ ዘመን ያለን ጤና ባለሙያ ማጭበርበር ፈፅሞ አይቻልም!
የነቃ፣ ለትግል የበቃ Smart የጤና ባለሙያ ተፈጥሯል።
ከፊል የጤና ሽፋንን ብቻ ለመስጠት ታስቦ በኢትዮጵያ ጤና መድህን ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ ጤና ባለሙያው እንዲመዘገብ የወረደውን መመሪያ ፣ ሙሉ የጤና ሽፋን ካልሆነ አንመዘገብም በሚል ጤና ባለሙያው መብቱን እያስከበረ ባለበት ሰዓት ፤ ሁሉን ነገር በኃይል ለመፍታት የሚዳክሩ የአገዛዙ ካድሬዎች ፣ ጤና መድህን መመዝገብ በፈቃድ እንደሆነ መመሪያው ቢገልፅም እነሱ ግን በተዘዋዋሪ የማስገደጃ ስልቶችን እየተጠቀሙ ይገኛሉ።
1ኛው ፦ ከታች በተለጠፈው ደብዳቤ እንደምታዩት "ጤና መድህን አልፈልግም ብላችሁ ስማችሁን እና ፊርማችሁን አስገቡ በማለት ባለሙያውን እያስገደዱት ይገኛሉ።
2ኛው = ጤና መድህን ካልገባችሁ Staff ህክምናን እናቆማለን
3ኛ= ከዚህ በኋላ የጤና መድህን አባልነት ምዝገባ የለም
የሚሉ አስገዳጅ ነገሮችን እያደረጉ ይገኛሉ።
አሁንም ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነገሮች መመሪያው ውስጥ ሳይካተቱ Amoxacilin እና paracetamol ለማውጣት ብለን አንፈርምም❗️
1ኛ = ቴሌ፣ ባንክ፣አየር መንገድ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በመንግስትም ተቋም የማይሰጡ አገልግሎቶችን ከግል ተቋም የምርመራም እና የመድሃኒት አገልግሎቶችን በማግኘት በደረሰኝ ማወራረድ ይችላሉ --ሙሉ ወጪያቸውን ተቋሙ ይሸፍናል።
ወደኛ ስንመጣ( የሰው ጤና ስንሰጥ የራሳችንን ጤና ለTB, HBV, HCV, HIV,ለጨረር የምናጋልጥ ባለሙቻዎች) ጤና ተቋም ላይ የሌለን መድሃኒትም ሆነ ምርመራ በግላችን ወጪውን እንድንችል የተደረገው በአስቸኳይ መስተካከል አለበት❗️
2ኛ = End stage liver disease 2 Chronic Viral Hepatitis ተብለው የጉበት ንቅለ ተከላ የሚያስፈልጋቸው ፤ በአቅም እጥረት ወደ ውጭ ሄደው ህክምናውን ሳያገኙ ህይወታቸው ያለፈባቸው ባለሙያዎች አሉን - ነፍሳቸውን ይማርና.....
እነዚህ ባለሙያዎች ለ Hepatitis virus የተጋለጡት የሰውን ህይወት ለማዳን ሲሉ ነው፤ ግን የራሳቸውን ህይወት በአቅም እጥረት ምክንያት ተነጠቁ። ስለዚህ ጤና መድህኑ የውጭ ህክምናን እንዲያካትት እንጠይቃለን❗️
3ኛ፦ Valvular replacement የሚያስፈልጋቸው ብዙ የጤና ባለሙያዎቻችን አሉ። ባለፈው በጤና ባለሙያው ርብርብ የልብ ቀዶ ህክምና ያደረገች እህታችንን ሁላችንም እናስታውሳታለን።
ስለዚህ እንዲህ አይነት ህክምናዎችን ወረፋ ሳንጠብቅ በግል የልብ ቀዶ ህክምና ማዕከላት በነፃ የመታከም መብትን ጤና መድህን ውስጥ እንዲካተት እንፈልጋለን❗️
4ኛ = የመነፀር፣ ፣የተቦረቦረ ጥርስን የመሙላት፣ የዲያሊስስ፣ ከፊል የመስማት ችግርን የሚጨምሩ የህክምና መሳሪያዎችን ፤ድንገተኛ የተፈጥሮ አደጋ በሚገጥሙን ግዜ ያሉት ህክምናዎች በጤና መድህኑ እንዲካተቱ እንጠይቃለን❗️
እነዚህ ወሳኝ ጉዳዮች ሳይካተቱ አንድም ባለሙያ ባለመፈረም መብታችንን እንድናስከብር እለምናችኋለሁ❗️