04/03/2024
❖ የጉልበት ህመም
ጉልበታችን ከ4 አጥንቶች የተሰራ የሰውነታችን ክፍል ነው።
1. ሎሚ (patella)
2. የታፋ አጥንት (Femur)
3. የቅልጥም አጥንት (Tibia)
4. ትንሿ ቅልጥም (Fibula) ሲሆኑ እርስ በእርሳቸው በተለያዩ ጅማቶች የተያያዙ ሲሆኑ በመሀከሉ ደግሞ ሜኒስከስ (Meniscus) የሚባል ይገኛል። ይህም በጉልበት አጥንቶች መሀከል የሚፈጠረውን ፍትጊያ (friction) እንዲቀንስ የሚረዳ ሲሆን በተጨማሪም የሰውነታችን ክብደት በእኩል ወደ ቅልጥማችን እንዲተላለፍ ይረዳናል። ከነዚህ በተጨማሪ በጉልበታችን መሀል ሳይኖቪያል (synovial fluid) ፈሳሽ ይገኛል።ይህም እግር በሚዘረጋበት እና በሚታጠፍበት ጊዜ እንደ ማለስለሻ አይነት የሚጠቅም ነው።
ጉልበት የላይኛውን (የታፋችን) አጥንት ከታችኛው አጥንት (ቅልጥም) የሚያገናኙ 4 ዋና ዋና ጅማቶች ሲኖሩት እነዚህም የየራሳቸው ጥቅሞች አሏቸው።
1. አንቴሪየር ክሩሼት ሊጋመንት (Anterior cruciate ligament): ይህ ጅማት በጉልበት መሀከለኛ ክፍል የሚገኝ ሲሆን ጥቅሙም የታችኛው የእግራችን አጥንት (ቅልጥም /tibia) እንዲዞር (rotation) እና ወደፊት እንዳይንሸራተት ( forward movement) ይቆጣጠራል።
2. ፖስቲሪየር ክሩሼት ሊጋመንት ( posterior cruciate ligament): ይህ ጅማት የታፋ አጥንታችን አንፃራዊ በሆነ መልኩ በቅልጥማችን ላይ እንዳይንሸራተት እና የታችኛው የእግራችን አጥንት (ቅልጥማችን) ወደኋላ እንዳይንሸራተት ይረዳናል።
3. ላተራል ኮላተራል ሊጋመንት (Lateral collateral ligament): ይህ ጅማት የታፋችን አጥንት (Femur) ከታችኛው የባታችን አጥንት (Fibula) ጋር የሚያገናኝ ነው። የሚጠቅመውም ጉልበታችን ከጎን በኩል ከውስጥ ወደ ግራ / ቀኝ እንዳይታጠፍ (ሸብረክ) እንዳይል varus force የሚረዳ ነው።
4. ሚዲያል ኮላተራል ሊጋመንት (Medial collateral ligament): ይህ ጅማት የታፋችን አጥንት ከቅልጥም አጥንታችን ጋር የሚያገናኝ ነው። የሚጠቅመውም ጉልበታችን ከግራ ወይም ከቀኝ ጎን (ቀኝ ወይም ግራ ጉልበት) ወደ ወስጥ እንዳይታጠፍ የሚረዳ ነው።
ጉልበታችን በተለያዩ ምክንያቶች የተለያዩ አይነት ህመም /ጉዳት ሊያጋጥም ይችላል። ከነዚህም መካከል:-
1. አደጋ /Trauma
2. እድሜ /age
3. ከፍ ያለ የሰውነት ክብደት / Obesity
4. Bone fracture /ስብራት
5. የሎሚ / የአጥንት ስብራት
6. የጉልበት እብጠት
7. የጉልበት መገጣጠሚያ መቅላት
8. የጅማቶች መጎዳት / Ligament injury
9. Dislocation / subluxation (ውልቃት)
10. Muscle strain / የጡንቻ መሸማቀቅ
11. Muscle contusion / የጡንቻ መመታት (መቁሰል)
12. Tendinitis / የጅማቶች መቆጣትና መቁሰል
13. Meniscal Lesions / የጉልበት የውስጥኛው ክፍል መጎዳት
14. Artheritis
15. Post surgical injury / ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚከሰት ጉዳት
16. Knee stifness /የጉልበት ግትር መሆን/ እንደፈለጉ ለማጠፍ እና መዘርጋት መቸገር
17. Ligament sprain
18. የስራ ባህሪ / የስራ ጫና
19. ከበድ ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ( አትሌቶች፣ ኳስ ተጫዋቾች፣ የሰውነት ግንባታ ወይም በተለምዶ ብረት የሚያነሱ ሰዎች)።
20. የመሳሰሉት ይገኙበታል።
አንድ በጉልበት ህመም የተጎዳ ሰው ወደ ሚከተሉት ሙያተኞች/ ክሊኒኮች ሄዶ የህክምና አገልግሎት ማግኘት ይችላል:-
1. ፊዚዮቴራፒስት /physiotherapist
2. የአጥንት ስፔሻሊስት /Orthopedician
3. Medical Pain management / የመድሀኒት ህክምና
የህክምና ሙያተኞች የተለያዩ አይነት የህክምና መመርመሪያ ዘዴዎችን በመጠቀም ህክምናቸውን ሊያከናውኑ ይችላሉ። ከነዚህም አንዱ ኢሜጂንግ (Imaging) ነው። ለምሳሌ:- X-ray, MRI, CT-scan, እና አንድአንድ የላብራቶሪ ምርመራዎች ሊያዙ ይችላሉ። ይህ የሚሆነው ግን እንደሙያ ዘርፉ ነው።
በጉልበት ህመም የተጎዳ ሰው የሚከተሉትን ጥንቃቄዎች ሊያደርግ ይገባዋል:-
የሰውነት ክብደትን መቀነስ
ተረከዛቸው ከፍ ያሉ ጫማዎችን አለመልበስ
ቀለል ያሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማድረግ
ረዘም ላለ ሰዓት መቆምን መቀነስ
በምንንበረከክበት ሰዓት ንጣፍ ማድረግ
በካልሺየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
የመሳሰሉት ይገኙበታል።
❖ የጥንቃቄ ማሳሰቢያ:- አንዳአንድ የጉልበት ህመም ያለባቸው ሰዎች ያለምንም የባለሙያ ምክር ስፖርት መስራት እንደ መፍትሄ ይወስዱታል። ይህ አካሄድ ህመሙን ሊያባብሱ የሚችሉ ስፖርቶች ሊሰሩ ስለሚችሉ በቅድሚያ ወደ ባለሙያ በመሄድ የህመም አይነት መለየትና የስፖርት እንቅስቃሴ የሚያስፈልጋቸው ከሆነም መስራት ያለባቸውንና የሌለባቸውን የእንቅስቃሴ አይነቶች ለማወቅ ከ #ፊዚዮቴራፒ ባለሙያ ምክር ማግኘቱ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።
✆ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
0920118530
0956212223
# በአካል ለመምጣት አያት ሞል የሚገኘው ክሊኒካችን ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ክፍት ነው!!
* የቴሌግራም ቻናላችን በመቀላቀል እንደዚህ አይነት የጤና መረጃዎችን ያግኙ። በተጨማሪም ልናቀርብላች የምትፈልጉትን ከእኛ ሙያ ጋር የተያያዙ ህመሞችን መፃፍ ወይም መጠየቅ ትችላላቹ።