24/12/2025
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
______________
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በሙሉ፤ ፈተናው በታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን እየገለፅን፦
1. የፈተናው መርሃ-ግብር
- በ23/04/2018 ዓ.ም…… Public Health, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Medical Radiology Technology, Environmental Health እና Human Nutrition
- በ24/04/2018 ዓ.ም…… Medicine, Nursing, Anesthesia, Midwifery, Dental Medicine, Psychiatric Nursing, Emergency and Critical Care Nursing, Pediatric and Child Health Nursing, Surgical Nursing እና Physiotherapy
ሁሉም ተፈታኝ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (orientation) መከታተል፤ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራትና፤ የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል::
2. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡