17/10/2025
💡እነሆ የልብ ጤናችሁን ለመጠበቅ ቁልፍ የሆኑ ምክሮች፦
የልብና የደም ሥር በሽታዎች በዓለም የሞት ዋና ምክንያቶች መካከል ቢሆኑም፣ በአንድነት ይህን መቀየር እንችላለን!
✅ እንቅስቃሴ ያድርጉ፡ በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ መካከለኛ የሆነ እንቅስቃሴ ያድርጉ። መራመድ፣ ብስክሌት መንዳት ወይም በመደነስ መዝናናት የሚረዱ ናቸው።
✅ ጤናማ ምግብ ይመገቡ፡ ብዙ ፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ጥራጥሬ እህል እና ቀላል ፕሮቲኖችን በምግቦቻቹ ጨምሩ። ስብ፣ ስኳርና ጨውን ያስወግዱ።
✅ ጭንቀትን ያስቀንሱ፡ ሜዲቴሽን፣ ዮጋ፣ ወይም ጥልቅ እስትንፋስ በመውሰድ ጭንቀትን ቀንሱ እና ልብን ጤናማ ያድርጉ።
✅ ማጨስ ማቆም፡ ትምባሆን ማጨስ ማቆም በልብ በሽታ የመያዝ እድልን እጅግ ይቀንሳል።
✅ መደበኛ ምርመራ ያድርጉ፡ የደም ግፊት፣ ኮሌስትሮል መጠን እና አጠቃላይ የልብ ጤና በመደበኛ ምርመራ በማድረግ ጤናዎን ይከታተሉ።
✅ በቂ ውሃ ይጠጡ፡ በስኳር የተሞሉ መጠጦችን ያስወግዱ። ይህ የሰውነት ተመጣጣኝ ክብደትን ለመጠበቅ ይረዳል።
እነዚህን ልምዶች በመከተል እና በጤና ጉዞአችን እርስ በርስ በመደጋገፍ እንትጋ።
አስታውሱ፤ ለጤናማ ነገ ዛሬ ልብዎን ይንከባከቡ !