14/11/2025
ቫይታሚን ዲ(D) ለጤናችን ያለው ጠቀሜታ
✔️1. ለጤናማ የጥርስና የአጥንት እድገት ፡- በሰዉነት ዉስጥ የካልሲየም (Calcium ) መጠንን ለመቆጣጠርና የፎስፈረስ (Phosphorus ) መጠንን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡
✔️2. በሽታ የመከላከል ፣ የአንጎል እና የነርቭ ስርዓት ጤናን ለመደገፍ ይረዳል ፣
✔️3. የኢንሱሊን መጠንን ለማስተካከልና የስኳር በሽታ ህክምናን ለመደገፍ ፣
✔️4. የሳንባ ተግባር እንዲሁም የልብንና የደም ቧንቧዎችን ጤንነት ለመጠበቅና ለመደገፍ ፣
✔️5. በሰዉነታችን ዉስጥ መቆጣትን (ኢንፍላሜሽንን) ለመቀነስ እንዲሁም ለሴል እድገት፣የስኳር ሜታቦሊዝምን፣ የበሽታ መካለከልንና የነርቭንና ጡንቻ ስርዓት አገልግሎትን ለመደገፍ ይረዳል፡፡
ቫይታሚን ዲ'ን ከምን ማግኘት እንችላለን?
✔️ ከምግቦች:- አሳ፣ የአሳ ዘይት፣ የበሬ ጉበት፣ ከእንቁላል አስኳል፣ ከእንጉዳይና ከአይብ።
✔️ ከምግብ ሰፕልመንቶች:- የተለያዩ ምግቦችን በቫታሚን ዲ በማበልፀግ፡፡
✔️ የቫይታሚን ይዘት ካላቸው መድሀኒቶች
📲 🔵የቫይታሚን ዲ እጥረት ምልክቶች ምንምን ናቸው?
አንዳንዴ ምንም አይነት ምልክቶች ላያሳይ የሚችል ቢሆንም ከምልክቶች ውስጥ እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
> በተደጋጋሚ መታመም
> ተደጋጋሚ የድካም ስሜት መኖር
> የአጥንትና የጀርባ ህመም
> የመገጣጠሚያ ህመም
> የአጥንት ስብራት
> የስሜት መቀነስ( የቀዘቀዘ ስሜት) እና ጭንቀት
> የቁስል የመዳን ፍጥነት መቀነስ
> የፀጉር መነቀል ወይም መርገፍ
> በጡንቻዎች ውስጥ ህመም ዋናዋና ናቸው ::
🔵የቫታሚን ዲ እጥረት ሊያስከትላቸው የሚችለው ጉዳቶች (ኮምፕሊኬሽኖችን) ሊያስከትል ይችላል፡፡ እነሱም:-
> የልብና የደም ቧንቧ ችግሮች
> የራስ የበሽታ መከላከል፣ የራሳችንን አካል የመጉዳት ችግሮች (autoimmune problems)
> የነርቭ ችግሮች
> ኢንፌክሽኖች
> የእርግዝና ወቅት ችግሮች (ኮምፕሊኬሽኖች)
> የተለያዩ ካንሰሮች( በተለይ የጡት፣ የፕሮስቴትና የትልቁ አንጀት ካንሰሮች) ናቸዉ፡፡
🔵የቫይታሚን ዲ እጥረት መኖርን እንዴት ሊያውቁት ይችላሉ ?
በቀላል የደም ምርመራ የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳለቦዎት ለማወቅ ይረዳል፡፡
#የቫይታሚን ዲ እጥረት ህክምና እና ጥንቃቄዎች
የቫይታሚን ዲ እጥረት ብዙውን ጊዜ በተጨማሪ ምግብ ይታከማል። አንድ የጤና እንክብካቤ ባለሙያ ጉድለት እንዳለብዎ ካወቀ የሚከተሉትን አማራጮች ሊመክሩ ይችላሉ።
1. የቫይታሚን ዲ መድኃኒቶች
> በአፍ የሚወሰዱ ቫይታሚን ዲ መድኃኒቶች በጣም ጥሩ ህክምና ናቸው:: የቫይታሚን ዲ መርፌዎችንም ለከባድ እጥረት፣ ዶክተሩ ግምት ውስጥ ማስገባት ይችላል
- የመጠን ምክሮችን ዶክተርዎን መጠየቅ
> ማግኒዥየም ቫይታሚን ዲን ለማንቀሳቀስ ይረዳል, ስለዚህ እርስዎም ይህን ማዕድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. በቫይታሚን ዲ የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ፣
3. የፀሐይ ብርሃን ተፈጥሯዊ የቫይታሚን ዲ ምንጭ ስለሆነ፣ ዶክተርዎ ብዙ ጊዜ ወደ ውጭ እንዲወጡ ሊመክርዎ ይችላል።
~ ይሁን እንጂ ከመጠን በላይ የአልትራቫዮሌት መጋለጥ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖ ከግምት ውስጥ በማስገባት አጠቃላይ የፀሐይ መጋለጥን በመገደብ እና የፀሐይ መከላከያዎችን በመተግበር ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል።
አጠቃላይ የተሟላ የህክምና አገልግሎት ለአዋቂና ለህፃናት
📲 Tiktok:
https://www.tiktok.com/?_t=ZM-90akSDYbnPE&_r=1
📲 Facebook:
https://facebook.com/profile.php?id=100087371935839
📲 Instagram:
https://www.instagram.com/aynalem_hospital?utm_source=qr&igsh=MXBtYzdubW5jdzEzYg==
📲 Telegram:
https://t.me/Aynalem_Primary_Hospital
📲 Website:
www.aynalemhospital.com
☎️ 011-347 10 27 / 011-348 17 45/46
🏠 አድራሻ: ዐይንዓለም ሆስፒታል - አየር ጤና ከሳሚ ካፌ ጀርባ
https://maps.app.goo.gl/zyGJLynGhoNPgL4GA