21/09/2022
Fatty Liver / የሰባ ጉበት /
* ከአልኮል ጋር የሚገናኝ ወይም የማይገናኝ ተብሎ ሲከፈል በአብዛኛው የሚታየው ከ አልኮል ያልተጎዳኘ የሰባ ጉበት በሽታ በጉበት ውስጥ ጤናማ ያልሆነ የስብ መከማቸት ሲሆን የከፋ የጤና ጉዳት አያስከትልም።
* ስብ /Fat/ በጉበት ውስጥ በመጠኑ ሊገኝ ሲችል ግን ከ 5 - 10% ከበለጠ የሰባ ጉበት /steatosis/ ይባላል።
*በተለይ ባደጉት ሃገራት እስከ 25% የሚሆን ህዝብ በዚህ ሁኔታ እንደሚጠቃ ይታመናል።
# ማን ላይ ይከሰታል?
- በጣም ውፍራም /የስብ መጠናቸው ከፍ ያለ/
- የስኳር ወይም ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው
- ከፍተኛ የኮሌስትሮል እና triglyceride መጠን ያላቸው
- የጉበት ኢንፌክሽን
- ደካማ /ኢ-ጤናማ/ የአመጋገብ ስርአት ወይም የምግብ ጉዳት ያለባችው
- በተለያየ ምክንያት የሰውነት ክብደት በድንገትና በብዙ ሲቀንስ
- ሌሎችና በአብዛኛው ግን ያለ ምንም ምክንያት ሊከሰት ይችላል።
* ይህ ሁኔታ እንደ ማንቂያ /alarm/ ሊቆጠር ይችላል። በራሱ የከፋ ጉዳት ባያመጣም ጤናማ ያልሆነ የሰውነት ወይም የጉበት ስራ /metabolism/ ማሳያ ነው። ይህም ቀስ በቀስ ጥንቃቄ ካልተደረገ ጉበትን በማሻከርና በማደደር cirhosis የተባለውን የጉበት አካላዊ ጉዳት በማስከተል ወደ ጉበት እጢ /cancer/ ወይም የጉበት መክሸፍ /failure/ ሊያደርስ ይችላል።
* ምልክቶች : - ድካምና የሰውነት መዛል ፣ ማቅለሽለሽ ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በቀኝ የላይኛው የሆድ ክፍል ላይ ህመም ፣ የሆድ መነፋትና መወጠር ፣ ቆዳን ማሳከክ ፣ የቆዳ ወይም አይን ቢጫ መሆን ፣፣፣፣እና ሌሎችም ሲሆኑ በአብዛኛው ግን ምንም ምልክት ላይታይ ይችላል።
፠ ከደም ናሙና የጉበትና ኮሌስትሮል ምርመራዎች ጠቋሚ ቢሆኑም በአብዛኛው Fatty Liver / የሰባ ጉበት / የሚረጋገጠው በሶኖግራፊ /ultrasound/ ነው።
# ህክምናና መከላከያ መንገዶች :
- የግድ መወሰድ ያለበት መድሃኒት /standard treatment/ የሌለው ሲሆን በዋነኝነት የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር ጉዳቱን መቆጣጠር ወይም መመለስ ይቻላል።
እነዚህም: ፨፠ ጤናማ የሆነ አመጋገብና ዘውትር የሰውነትት እንቅስቃሴ /exercise/ ማድረግ ፣ ተጓዳኝ የስኳር ወይም ግፊት በሽታ ካለ መታከምና ክትትል ማድረግ ፣ የሰውነት ክብደትንና የስብ መጠንን መቀነስ ፣ የኮሌስትሮልና የቅባት መጠንን መቀነስ ፣ የሚወስዱትን የአልኮል መጠን መቀነስ ወይም መገደብ ፣ እንዲሁም ተገቢ የሆኑ መድሃኒቶችን ብቻ መጠቀም ፠፨
* ይህ እንዳለ ሆኖ ቋሚ የሆነ የጤና ክትትል ማድረግና የሁኔታው መባባስና ማስጨነቅ ከቀጠለ ሃኪምዎን ማማከርና ምርመራም ማድረግ የግድ ይላል። ቸር ያቆየን!
ዶ/ር ዳንኤል ተከተል