Ethiopian Health News-EHN

Ethiopian Health News-EHN Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Health News-EHN, Medical and health, Addis Abeba, Addis Ababa.

Ethio-Health News-EHN will give helath information and education
-Will encourage health promotion
-Will give health tips
-Will update on health professionals issues

01/12/2025
በማርበርግ ቫይረስ ተይዛ ህክምና ስትከታተል የቆየች አንዲት ታማሚ ከበሽታው በማገገም ከቫይረሱ ነፃ መሆኗ በመረጋገጡ ከህክምና ማዕከል ወጥታለች።_________የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ...
30/11/2025

በማርበርግ ቫይረስ ተይዛ ህክምና ስትከታተል የቆየች አንዲት ታማሚ ከበሽታው በማገገም ከቫይረሱ ነፃ መሆኗ በመረጋገጡ ከህክምና ማዕከል ወጥታለች።
_________

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ እንደገለፁት ታማሚዋ የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክት በማሳየቷ ህክምና ሲደረግላት ቆይቶ፣ የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላት ከቫይረሱ ነፃ መሆኗ በመረጋገጡ ከህክምና ማዕከል እንድትወጣ መደረጉን አስረድተዋል።

የበሽታው ታማሚ ህፃን በአምላክ ምትኩ 15 ዓመቷ ሲሆን በሽታው መኖሩ በላቦራቶሪ ምርመራ ተረጋግጦ፣ በተደረገላት ህክምና ከበሽታው ማገገም ችላለች፡፡

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቱ በሚታይበት ወቅት ወዲያውኑ ወደ ጤና ተቋም የሚመጡ አካላት የማገገም ዕድላቸው ሰፊ በመሆኑ ሁሉም ሰው ሳይዘናጋ የቫይረሱ ምልክቶች ሲኖሩ ፈጥኖ ወደ ህክምና ማዕከል መምጣት በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ያስችላል።

በቀጣይ ቀናት ከማርበርግ ቫይረስ በሽታ አገግመው የሚወጡ ታማሚዎች ስለመኖራቸውም የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል።

አርቲስቱ በምን ምክንያት አረፈ???ኮሜድያኑ በድንገተኛ ህመም አረፈ😭በበርካታ የኮሜዲ ስራዎች ላይ የሚታወቀው ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈተወዳጁ ኮሜዲያን ወንደ...
30/11/2025

አርቲስቱ በምን ምክንያት አረፈ???

ኮሜድያኑ በድንገተኛ ህመም አረፈ😭

በበርካታ የኮሜዲ ስራዎች ላይ የሚታወቀው ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ በድንገተኛ ህመም ህይወቱ አለፈ

ተወዳጁ ኮሜዲያን ወንደሠን አውራሪስ ለብዙ ዓመታት በሳቅ ሲያጥመቅ የኖረው ወንደሠን፣ እንደ ምንጮች ዘገባ በድንገተኛ የልብ ህመም ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ተሰምቷል።

በአሁን ሰአትም አስክሬኑ ለምርመራ በሚኒሊክ ሆስፒታል
እንደሚገኝ ተገልጿል።

ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ፣ ለአድናቂዎቹ እና ለመላው ኢትዮጵያውያን በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን።

28/11/2025
የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎችአዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ...
28/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማርበርግ ቫይረስ በሽታ (Marburg Virus Disease) በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ሲሆን በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል።

የበሽታው ምልክቶች ለቫይረሱ በተጋለጥን ከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ የሚታዩ ሲሆን፤ ምልክቶቹ:-

👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ፣

👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣

👉 የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣

👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣

👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ ናቸው።

የበሽታው መተላለፊያ መንገዶች

👉 ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣

👉 በታመመ ወይም በሞተ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች (እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌ እና ሌሎች መገልገያዎች) ጋር በሚኖር ንክኪ፣

👉 በተጨማሪ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል።

የበሽታው መከላከያ መንገዶች

👉 የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣

👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ ካለዎት እና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣

👉 ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣

👉 ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣

👉 ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእጅ ጓንት መጠቀም፣

👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ እንደሚገባ የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።

28/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶቹን ቀድሞ መለየት ስርጭቱን በቶሎ በማስቆም የመዳን እድልን ያሻሽላል!


Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/11/2025

Good news

በዛሬው እለት በማርበርግ ቫይረስ የተያዘ የለም!

ጥንቃቄ አይለየን

27/11/2025

(መሠረት ሚድያ)- ከሰሞኑ በጂንካ ከተማ እንደተከሰተ የተነገረለት የማርበርግ ቫይረስ ምልክቶችን አሳይተዋል የተባሉ ግለሰቦች አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ውስ....

27/11/2025

ስለ ማርበርግ ቫይረስ በሽታ ተደጋግሞ የሚነሱ ጥያቄዎች



Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/11/2025

Address

Addis Abeba
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Health News-EHN posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram