Dr Henok Tesfaye ዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ- የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Dr Henok Tesfaye ዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ- የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስት

Dr Henok Tesfaye ዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ- የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስት Provides information on nuclear medicine and healthcare related news

16/02/2024
24/08/2023

This story on NBC 10 Boston focuses on research about how nuclear medicine imaging of the brain is helping researchers find better interventions and treatmen...

👉🦴የአጥንት ቅኝት (Bone scan) ምንነትና አስፈላጊነት፡  ይህ የአጥንት ምርመራ የአጥንትዎን ጤና ለመገምገም  የሚረዳ  ምርመራ ነው። የምርመራው አሰራር ሂደቱን ስንመለክት፡ አነስተኛ...
06/02/2023

👉🦴የአጥንት ቅኝት (Bone scan) ምንነትና አስፈላጊነት፡

 ይህ የአጥንት ምርመራ የአጥንትዎን ጤና ለመገምገም የሚረዳ ምርመራ ነው።
 የምርመራው አሰራር ሂደቱን ስንመለክት፡ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር አመንጪ ንጥረ ነገር በመርፌ ወደ ደም ስርዎ ውስጥ በማስገባት ከውጭ በሚገኝ ጨረር ለቃሚ መሳሪያ (SPECT or SPECT/CT) አማካኝነት ስርጭቱን በምስል በመከታተል የሚደረግ ምርመራ ሲሆን። ወደ ሰውነት የገባው ንጥረ ነገር ወደ አጥንቶችዎ በመጓዝ ችግር ያለባቸው ቦታዎችን ያጎላል። ቅኝቱ ወደ 30 ደቂቃ ያክል ይወስዳል እና ምንም አይነት ህመም የለውም።
 መላውን የሰውነት አጥንት በመቃኘት የሚከተሉትን ጨምሮ የተለያዩ የአጥንት በሽታዎችን ለመመርመር ይረዳል፡-
o ስብራት (fracture)
o የመገጣጠሚያ ህመም (Arthritis)
o የፓጄትስ የአጥንት በሽታ (Paget’s disease of bone)
o ከአጥንት ለሚነሳ ካንሰር (Primary bone tumor)
o ከተለየ ቦታ ወደ አጥንት ለተሰራጨ ካንሰር (Metastatic tumor to the bone) እና
o የአጥንት፣ የመገጣጠሚያዎች ወይም ሰው ሰራሽ የመገጣጠሚያዎች ቅየራ ኢንፌክሽንኖችን (bone, joint and prosthetic joint infections)

👉ከምርመራው በፊት ቅድመ ዝግጅቱ ምን ይመስላል?

 ከምርመራው በፊት, ለተወሰነ ጊዜ መጾም ያስፈልግዎታል.
 ታካሚዎች ማንኛውንም አለርጂዎች, የቅርብ ጊዜ ቀዶ ጥገናዎች እና የሚወስዱትን ወቅታዊ መድሃኒቶች ለሐኪማቸው ማሳወቅ አለባቸው
 እርጉዝ ወይም የሚያጠቡ እናቶች ከሆኑ ማሳወቅ አለባቸው

👉ከምርመራ በኋላ ፡

 መብላት እና መድሃኒቶችን መውሰድን ጨምሮ መደበኛ እንቅስቃሴዎችዎን መቀጠል ይችላሉ። ራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሩን ከሰውነት ስርአትዎ ለማስወጣት እንዲረዳዎ ብዙ ፈሳሽ እንዲጠጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።

👉የአጥንት ቅኝት ምርመራን በማድረግ ወደ አጥንት የተሰራጨ የካንሰር በሽታን ቀደም ብሎ ማወቁ ፈጣን ሕክምና እንዲጀመር በማድረግ በታካሚው ላይ አወንታዊ ውጤትን ማየት ያስችላል። ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶች የሚሰጡ ሕክምናዎች የሚያሳዪትን ምላሾችን ለመገምገም ይረዳል። ወደ አጥንቶች ሊሰራጩ ከሚችሉት በጣም የተለመዱ የካንሰር ዓይነቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።
 የፕሮስቴት ካንሰር
 የጡት ካንሰር
 የሳምባ ካንሰር
 የታይሮይድ ካንሰር
 የኩላሊት ካንሰር
 የኮሎሬክታል ካንሰር እና
 የጣፊያ ካንሰር

በዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስትና
ረዳት ፕሮፌሰር

📌የኒውክለር ህክምና(nuclear medicine) ምንድን ነው?      =============================👉የኒውክለር ህክምና እጅግ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር የሚያመነጭ ንጥረ ...
16/01/2023

📌የኒውክለር ህክምና(nuclear medicine) ምንድን ነው?
=============================
👉የኒውክለር ህክምና እጅግ አነስተኛ መጠን ያለው ጨረር የሚያመነጭ ንጥረ ነገርን (ራዲዮፋርማሲዪቲካል) በመጠቀም ለታካሚዎች የምርመራና የህክምና አገልግሎት የምንሰጥበት የህክምና ዘርፍ ነው ።ንጥረ ነገሩ በሚዋጥ ፣ በመርፌ ወይም በትንፋሽ ለታካሚ የሚሰጥ ሲሆን በውስጡ መጠነኛ የመድሀኒት ውህድ በመያዙ በሴሎችና በሕብረ ሕዋሳት አማካኝነት በቀላሉ ወደ ሰውነታችን ይወሰዳል።ወደ ሰውንታችን የገባውን ጨረር አመንጪ ኬሚካል ስርጭቱን ከሰውነት ውጭ ባሉ የምርመራ መሣሪያዎችን (እንደ SPECT/CT, PET/CT and PET/MRI) በመጠቀም ተግባራዊ ምስሎችን ማግኘት ይቻላል። ህክምናው በሁሉም የህክምና ዘርፎች ተፈላጊ ሲሆን ነገርግን በካንሰር ፣ በልብ እና በነርቭ ታካሚዎች ላይ እጅግ ጉልህ አስተዋጾ አለው።

ከሲቲ እና ከኤምአርአይ በምን ይለያል?
👉ሲቲ እና ኤምአርአይ በሽታን ለማግኘት የአንድን አካል ክፍል የቅርጽ ለውጥ(Anatomical changes) በማየትና በመመርመር ችግሩን የምናገኝበት ህክምና ሲሆን በአንፃሩ የኒውክልር ምርመራ የአካል ክፍል አሠራር ለውጥ(physiologic changes) በማሳየት በሽታው የቅርፅ ለውጥ ከማምጣቱ በፊት ከጅምሩ የተዛቡ ነገሮችን ለይቶ ለማወቅና ለማከም ያገለግላል። ከቅርብ ጊዜያት በፊት የመጡ የኒውክለር ህክምና መሳሪያዎች ሁለቱንም ማለትም የአሠራርና የቅርፅ ለውጥን በአንድ መሳሪያ ማሳየት የሚችሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች ናቸው።

👉የምርምራው ጥቅሞች ምንድን ናችው?
 በሽታን ለማወቅ (diagnosis)
 የበሽታውን ደረጃ ለመወሰንና(disease severity assessment)
 የካንሰር የስርጭት ደረጃን ለማወቅ(staging)
 ለተለያዩ የካንሰር ዓይነቶች የሚሰጡ ሕክምናዎች የሚያሳዪትን ምላሾችን ለመገምገም (treatment response)
 ከህክምና በኋላ በድጋሚ የሚከሰት ካንሰርን በጊዜ ለማወቅና (cancer recurrence)
 ከጨረር ህክምና በፊት ጨረሩ የሚያርፍበት የካንሰር ቦታ ለማሳየት(treatment planning) የሚረዳ ዘመናዊ የምርመራ አይነቶችን ያካተተ ነው።

👉በተጨማሪም ከምርመራ ባሻገር በተለይ
 የኢንዶክሪን እና ኒውሮኢንዶክሪን ህመሞች
 ወደ አጥንት የተሰራጨ የፕሮስቴት ካንሰር
 ወደ ጉበት ለተሰራጨ የትልቅ አንጀት ካንሰርና
 የታይሮይድ ካንሰር ላለባቸው ሕሙማን በጣም ጠቃሚ የሆነ ሕክምና አለው።

ህክምናውን በቅርብ በሀገራችን በሚገኙ ተቋማት በማስጀምር የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስትና
ረዳት ፕሮፌሰር

Address

Swaziland Street
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dr Henok Tesfaye ዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ- የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Dr Henok Tesfaye ዶ/ር ሔኖክ ተስፋዬ- የኒውክለር ህክምና ስፔሻሊስት:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram