የጤና መረጃ

የጤና መረጃ This page is Created to provide BEST Medical information ወዳጅ ዘመድዎ እንዲደርሰው ሼር በማድረግ ያሳውቁ
FACEBOOK
www.facebook.com/ethiomedhealth
ፔጃችንን Like በማድረግ ይከታተሉን
(1)

27/11/2025

═════════════════
ልጆች መቼ ነው አልጋ ላይ መሽናት የሚያቆሙት?
═════════════════
አብዛኞቹ ህፃናት 5 ዓመት ሲሆናቸው ሌሊት ላይ ሽንታቸውን መቆጣጠር ይችላሉ:: ሆኖም 10-15% የሚሆኑ ህፃናት እስከ 7 አመታቸው ድረስ ይቸገራሉ፡፡ ሽንት ለሊት ሊያመልጣቸው ይችላል፡፡ጥናቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ይህ ችግር ያለባቸው ህፃናት እድሜያቸው በ 1 ዓመት በጨመረ ቁጥር ቺግሩ በ15% እየቀነሰ ይሄድና እድሜያቸው 15 ዓመት ሲሞላ 99 በመቶ ህፃናት ከዚህ አይነቱ ችግር ሙሉ ለሙሉ ነፃ ይሆናሉ፡፡
::
ሆኖም አንድ ሕጻን 6 አመት እና ከዛ በላይ ሆኖ ሽንትን ለመቆጣጠር ካልቻለ ወላጆች ሐኪም መማከር አለባቸው፡፡ ሽንትን መቆጠጠር ያለመቻል ችግር በወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ላይ ከሚፈጥረው ስነ-ልቦናዊና ማሕበራዊ ተፅዕኖ ይልቅ በልጆች ላይ የሚፈጥረዉ ስነ ልቦናዊ ተፅዕኖ እጅግ የበረታ ነው፡፡
ወላጆች ሊያወቁት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ልጆች ሆነ ብለው አሰበውና አቅደው ወይም በእነርሱ ግድ የለሽነትና ሥንፍና የሚመጣ ችግር እንዳልሆነ ልረዱ ይገባል፡፡ ስለዚህ እንዲህ አይነት ቺግር ያለባቸውን ህፃናት ማሸማቀቅ ማናደድ እንዲሁም በሰዉ ፊት ʺለሊት አልጋ ላይ ሸንቷል!ʺ ብሎ ማሳፈር በፍፁም ተገቢ አይደለም፡፡

ሽንትን ሌሊት ያለመቆጣጠር ችግር መንስኤው ምንድነው? ምክንያቱ ብዙ ቢሆንም ዋና ዋናዎቹ የምከተሉት ናቸው
═════════════════
1. ትልቅ የሆነ እንቅልፍ እና የሽንት ፊኛ ከመጠን በላይ ሲወጠር መንቃት አለመቻል
2. የጉሮሮ መጥበብ እና ትንፋሽ መቆራረጥ እና ማንኮራፋት (obstructive sleep apnea)
3. በቤተሰብ ተመሳሳይ ችግር ካለ(በተለይ እናት እና አባት ላይ በ ልጅነታ ቸው አጋጥሞቸው ከሆነ)
4. የሆርሞን መዛባት በተለይ የቫሶፕሬሲን (ADH) የሚባለው ሆርምን ማታ ላይ በአግባቡ የማይመረት ከሆነ
5. የሽንት ፊኛ ተገቢውን የሽንት መጠን መያዝ ወይም መሸከም አለመቻል(በነርቭ ቺግር ወይም የአፈጣጠር ችግር ምክንያት)
6. የአይምሮ ጭንቀት
7. አስቸጋሪና አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ እና ያን ተከትሎ ከፍተኛ ድንጋጤ እና ፍርሃት
8. አሰቃቂ አካላዊ ድብደባና ቅጣት
ወሲባዊ ጥቃት/የአስገድዶ መደፈር በተለይ ሴት ታዳጊዎች ላይ
10. የነርቭ ዘንግ(spinal cord) ችግሮች(spina bifida)
11. ከፍተኛ የሺንት መጠን ማምረት - polyuria (በስኳር ፣ በኩላሊት ችግሮች ወይም በሌሎች ምክንያቶች)
12. ረጅም ጊዜ የቆየ ሆድ ድርቀት
13. የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

═════════════════
ዶ/ር ፋሲል መንበረ (በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የሕፃናት ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር)
═════════════════
Via:- SPMMC.
═════════════════

27/02/2025
17/07/2023

እንኳን ደስ ያላችሁ! ደስ ብሎናል!
ሁሉም ተማሪዎች አልፈዋል!
100% !

ተማሪዎቻችን በExit Exam ከፍተኛ ነጥብ አስመዝግበዋል።

የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስቴር በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ባስጀመረው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መውጫ ፈተና የኮሌጃችን ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸውን በትናንትናው ዕለት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት :- በያዝነው 2015 ትምህርታቸውን የሚያጠናቅቁ 151 የሕክምና ተማሪዎች( Intern) የሚከተለውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

- 44 በመቶው 85 እና ከዚያ በላይ አግኝተዋል ።
74 በመቶው ተፈታኞች ደግሞ ከ80 እና ከዚያ በላይ ውጤት አግኝተዋል።

ውድ መምህራን እና የኮሌጁ ማሕበረሰብ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ!
ውድ ተማሪዎች እንኳን ለዚህ ስኬት አበቃችሁ!

Via :- SPMMC

17/07/2023

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የላቀ ወጤት!

በአገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዩኒቨርሲቲያችን በግምባር ቀደምትነት ተማሪዎችን በማሳለፉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳን ደስ አላችሁ።
***

በአገር ዓቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተተገበረው እና በዩኒቨርሲቲያችን ባሉ 8 ኮሌጆች፣ 2 ኢንስቲትዩቶችና 1 ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ 73 ትምህርት ክፍሎች ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

በአጠቃላይ ካስፈተናቸው 3,089 ተማሪዎች ውስጥ 2,760(89.35%) ተፈታኞች በብቃት አልፈዋል። ፈተናውን ከወሰዱ 73 ትምህርት ክፍሎች መካከል 34 ትምህርት ክፍሎች ሙሉ በሙሉ (100%) አሳልፈዋል።

ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል በመደበኛ መርሐግብር ካስፈተናቸው 2,919 ተማሪዎች 2,703 (92.6%) ያለፉ ሲሆን ቀሪዎቹ 170 ተማሪዎች በተከታታይ መርሐግብር ተፈተነው 57(33.53%) ፈተናውን በብቃት አልፈዋል።

ይህም ውጤት በአገሪቱ ካሉ አቻ ተቋማት ቀዳሚ ያደርገዋል።

በዚህም መላው የዩኒቨርስቲያችን ማህበረሰብና አጋሮቻችን ከፍተኛ ኩራትና ደስታ ተሰምቷቸዋል። የተገኘው ስኬት አበረታችና ለቀጣይ ትልቅ ኃላፊነትን የሰጠን ነው።

ስለሆነም ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የቴክኒክ ረዳቶች፣ የአስተዳደር ሠራተኞች፣ ትምህርት ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር አካላት እንዲሁም መላ የትምህርት ቤተሰቡ በትብብር ያስመዘገባችሁት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን።
***
ለልህቀት እንተጋለን!
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግኝኙነት ዳይሬክቶሬት
ሐምሌ 09/2015 ዓ.ም

05/06/2023
01/11/2022

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ የምትፈልጉ:
ሙያ እና ሥራ ልምዳችሁንና
መስራት የምትፈልጉ አከባቢ

Inbox or comment ላይ
በ English, or Amharic Or Afan Oromo ፃፉ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጤና መረጃ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram