ኢትዮሜድካል / Ethiomedical

ኢትዮሜድካል / Ethiomedical የኢትዮሜድካል የፌስቡክ ገፅ ዋና አላማ ትክክለኛ እና ቅቡልነት ያላቸው ጤናን የሚመለከቱ መረጃዎችን ማቅረብ ነው !!!

ማንኛውም ሰው ጤናን የተመለከተ መረጃ እንድቀርብለት ከፈለገ መልክት ያስቅምጥልን ፤ ባለሙያም ሆኖ አብሮን መስራት የሚፈልግ ካለ መቀላቀል እና የራሱን ድርሻ ማበርከት ይችላል፡፡ በምናቀርበው መረጃ ላይም የምትሰጡት ገንቢ አስተያየትም ሆነ ቅሬታም እንቀበላለን ፤ ለማስተካከልም እንሞክራለን፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተጻፉትን ዓይነት አስተያየቶች እንዳይስተናገዱ እናደርጋለን፡፡
• ሌሎችን የሚያስቀይሙና ስሜትን የሚጎዱ
• ብሔርን ፡ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥላቻ፣
• ወሲብ ቀስቃሽ ወይም መልካም ክብርና ዝናን የሚያጠፉ
• በጨዋ ቋንቋ ያልተጻፉ ወይም ስድብን የያዙ ቃላት ወይም ቅያሜ ሊያመጡ የሚችል ቋንቋ ያላቸው
• ንግድን የሚያስተዋውቁ፡ አትራፊ ለመሆን ምርትና አገልግሎታቸውን ለማስተዋወቅ የሚፈልጉ
• የጤና ስነ ምግባር የማይፈቅደውን ሀሳብ ለማራመድ የሚፈቅዱትን
• የሌሎችን ደህንነት እና ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉና መሰል ተግባራትን የሚያበረታቱ

12/05/2025

Here are some flowers that are commonly associated with happiness and can uplift mood through their color, fragrance, or...
07/05/2025

Here are some flowers that are commonly associated with happiness and can uplift mood through their color, fragrance, or symbolism:
1. Sunflower – Symbol of joy, warmth, and positivity. Its bright yellow petals resemble the sun and naturally evoke happiness.
2. Gerbera Daisy – Known for vibrant colors and cheerful appearance, they represent purity, cheerfulness, and innocence.
3. Tulip – Especially in bright colors like yellow or orange, tulips bring a sense of springtime renewal and contentment.
4. Peony – Associated with romance, prosperity, and good fortune; their full blooms often bring delight.
5. Lily of the Valley – Symbolizes sweetness and the return of happiness.
6. Marigold – Bright and bold, marigolds are culturally used in celebrations and symbolize creativity and passion.
7. Chrysanthemum – In many cultures, they symbolize joy, optimism, and a long life.

  ( ዝቅተኛ የሂሞግሎቢን መጠን)        🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶የደም ማነስ በመባል የሚታወቀው ዝቅተኛ የሂሞግሎቢን መለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል፡-1.የአይረን (ብ...
29/04/2025

( ዝቅተኛ የሂሞግሎቢን መጠን)
🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶🛶

የደም ማነስ በመባል የሚታወቀው ዝቅተኛ የሂሞግሎቢን መለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፤ ከእነዚህም መካከል፡-

1.የአይረን (ብረት) እጥረት | Iron deficiency!

በዓለም ዙሪያ በብዛት የሚከሰት የደም ማነስ መንስኤ ሲሆን፤ በአብዛኛው በቂ ምግብ ባለመመገብ፣ የደም መፍሰስ (ለምሳሌ:- የወር አበባ፣ የጨጓራ ደም መፍሰስ) ወይም አይረን በሚገባ አለመመጠጥ ምክንያት ነው።

2. የቫይታሚን እጥረት | Vitamin deficiency!

እንደ ቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት ያሉ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እጥረት የቀይ የደም ሴሎችን ምርት መቀነስ እና የሄሞግሎቢን መጠን መቀነስ ያስከትላል።

3. ሥር የሰደዱ በሽታዎች | Chronic diseases!

ሥር የሰደደ የኩላሊት በሽታ፣ ካንሰር፣ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ፣ ሩማቶይድ አርትራይተስ እና የአንጀት ቁስለት በሽታ የመሳሰሉት ሁኔታዎች ሰውነታችን ቀይ የደም ሴሎችን የማምረት አቅም ላይ ጣልቃ ስለሚገቡ ለደም ማነስ ይዳርጋሉ።

4. የአጥንት መቅኒ መታወክ | Bone Marrow Disorders!

እንደ አፕላስቲክ የደም ማነስ፣ ማይኤለዲስፕላስቲክ ሲንድረም እና ሉኪሚያ (Aplastic Anemia, Myelodysplastic Syndromes, and Leukemia) ያሉ ሁኔታዎች መቅኒ በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎችን የማፍራት ወይም የማምረት አቅምን ይጎዳል።

5. ሄሞሊሲስ | Hemolysis!

በአውቶኢሚውን ችግር (Autoimmune Disorders)፣ በኢንፌክሽን፣ በመድሃኒት ወይም በተወሰኑ በዘር በሚወረሱ ወይም በሚተላለፉ ሁኔታዎች ምክንያት የቀይ የደም ሴሎች መጥፋት (Destruction) ሊከሰት ይችላል። በዚህም ምክንያት የሂሞግሎቢን መጠን ዝቅተኛ ይሆናል።

6. ሥር የሰደደ ኢንፍላሜሽን | Chronic Inflammation!

በሰውነት ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ኢንፍላሜሽን ቀይ የደም ሕዋሳት እንዳይመረቱ እንቅፋት ሊሆንና የደም ማነስ ሊያስከትል ይችላል።

7. የዘረመል መዛባት | Genetic Disorders!

እንደ:- ሲክል ሴል አኒሚያ እና ታላሴሚያ ያሉ በዘር የሚተላለፉ በሽታዎች በሂሞግሎቢን ምርት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉና ሥር የሰደደ የደም ማነስ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

8. የሆርሞን መዛባት | Hormonal Imbalances!

እንደ ሃይፖታይሮዲዝም ወይም አድሬናል እጥረት ያሉ ሁኔታዎች በቀይ የደም ሴሎች መመረት ላይ ተጽዕኖ በማድረግ ለደም ማነስ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

9. የደም መፍሰስ | Blood Loss!

እንደ የጨጓራና ትራክት ቁስለት፣ ከባድ የወር አበባ ፍሰት ወይም በአደጋ የሚከሰት የአካል ጉዳት የመሳሰሉ አጣዳፊ ወይም ሥር የሰደደ የደም መፍሰስ ሁኔታዎች የሂሞግሎቢን መጠን እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል።

10. የተመጣጠነ ንጥረ-ምግቦች ጉዳይ | Nutritional Factors!

በተለይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት (በታዳጊ ሀገሮች) ለቀይ የደም ሴሎች ምርት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ-ምግቦችን በበቂ ሁኔታ አለመመገብ ለደም ማነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

https://linktr.ee/Ethiomedical - ሊንኩን በመጫን ሁሉንም  አካውንቶቻችንን ፎሎው ያድርጉ 🙏
13/04/2025

https://linktr.ee/Ethiomedical - ሊንኩን በመጫን ሁሉንም አካውንቶቻችንን ፎሎው ያድርጉ 🙏

Linktree. Make your link do more.

13/04/2025
=== Hepatitis B ቫይረስ በዉስጧ ያለች እናት =====በወሊድ ጊዜ ለልጇ ማድረግ/መደረግ ያለበት ጥንቃቄ=የቫይራል ሎድ መጠን ከወሊድ በፊት በሀኪም ትእዛዝ መሰረት ማድረግ, ዉጤቱን መ...
03/04/2025

=== Hepatitis B ቫይረስ በዉስጧ ያለች እናት ====

=በወሊድ ጊዜ ለልጇ ማድረግ/መደረግ ያለበት ጥንቃቄ=

የቫይራል ሎድ መጠን ከወሊድ በፊት በሀኪም ትእዛዝ መሰረት ማድረግ, ዉጤቱን መሰረት አድርጎ ህክምና ሊያስፈልግ ይችላል::

የ Hepatitis B vaccine እና Hepatitis B immunoglobulin የሚባሉ የቅድመ ጥንቃቄ መድኃኒቶች ከወሊድ በፊት በሀኪም ትእዛዝ መሰረት ማዘጋጀት::

ከወሊድ በኋላ በሀኪም ትእዛዝ መሰረት ከተቻለ በ 12 ሰዓት ዉስጥ ልጆች መድኃኒቶችን አንዲያገኙ ማድረግ::

ከዛም በኋላ በኢትዮጵያ የክትባት ስርዓት መሰረት ቀሪ ክትባቶችን መውሰድ ያስፈልጋል::

ይሄን ጥንቃቄ በማድረግዎ እስከ 90% ይደርስ የነበረውን የመተላለፍ ዕድል ወደ 1% ዝቅ ማድረግ ይቻላል

ከወሊድ በኋላም ልጆውን ወደ ህፃናት ሀኪም በ መውሰድ በቂ ክትትል ማድረግ እንዲሁም 9 ዎር ሲሞላው የ hepatitis B ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል::

For some reason if we failed to give the vaccine and immunoglobulin with in 12hrs, even if the efficacy is dropping after that, we can still give until 7 days.

After 7 days, we can still administer the vaccine, but the immunoglobulin is no longer necessary since the window for passive immunity has passed.

-ዶ/ር ሀብታሙ ስሜነህ: የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት

08/01/2025

  diabetics
04/01/2025

diabetics

የእርግዝና ወቅት ስኳር ምንድነው?የስኳር ህመም ከቋሚ ህመሞች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢንሱሊን ሆርሞን እጥረት ወይም በትክክል አለመስራት ምክንያት የሚከሰት ነው። የአይን ፣ የኩላሊት...
04/01/2025

የእርግዝና ወቅት ስኳር ምንድነው?

የስኳር ህመም ከቋሚ ህመሞች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢንሱሊን ሆርሞን እጥረት ወይም በትክክል አለመስራት ምክንያት የሚከሰት ነው። የአይን ፣ የኩላሊት ፣የ ልብና የነርቭ ችግሮች የሚያስከትል ህመም ነው።

ስኳር በአራት ዋናዋና አይነቶች ያሉት ሲሆን የእርግዝና ወቅት ስኳር አራተኛው አይነት ስኳር በመባል ይታወቃል።

✨የእርግዝና ወቅት ስኳር (GDM) ምንድነው?

የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው።

በአብዛኛው ከ28 ሳምንት እስከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት ድህረወሊድ ድረስ ይቆያል።
በእርግዝና ሰዓት ከሚገኙት የስኳር አይነቶች 90% የሚሆነው የስኳር አይነት ሲሆን ከእርግዝና በኋላ የሚጠፋ አይነት ነው።

በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩትም ከፍተኛ ተጋላጭነት ካለ በምርመራ ሊታወቅ ይችላል።

⚡️ምልክቶቹስ?

• የውሃ ጥም
• የሽንት መብዛት
• የምግብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር
• የልጅ መፋፋት
• የእንሽርት ውሃ መብዛት
• የፅንስ ያፈጣጠር ችግር

💥አጋላጭ ሁነቶች (risk factors)

• የቤተሰብ የስኳር ህመም
• ያለቅጥ ውፍረት
• የበፊት እርግዝና ስኳር
• የደም ግፊት
• የኮሌስትሮል መብዛት
• በርግዝና ወቅት ያላግባብ ክብደት መጨመር እና ወዘተ...

⛄️እንዴት ይታወቃል?

ሃኪሞችሽ አጋላጭ ሁነቶችሽ ካዪ በኋላ ከ24-28 ሳምንት የስኳር ምርመራ ያደርጉልሻል። ይህም ጣፋጭ ስኳር (40% glucose) በአፍሽ ከወሰድሽ በኋላ በየአንድ ሰዓት ልዪነት የደም ስኳር መጠንሽ በመለካት የእርግዝና ስኳር እንዳለ እና እንደሌለ ይነግሩሻል።

በሌላ የምርመራ ዘዴ (HgA1C) በመመርመርም ማወቅ ይቻላል።

ባደጉ አህጉራት ማንኛውም ነፍሰጡር እናት ለስኳር ምርመራና ልየታ የምታደርግ ሲሆን በታዳጊ አገራት የተወሰኑ ነፍሰጡሮች አጋላጭ ባህሪያቸው ታይቶ የሚመረመር ይሆናል

👉ምክንያቱ ምንድነው?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር ለምን እንደሚከሰት በትክክል ምክነያቱ ባይታወቅም ብዙ ሳይንሳዊ ሠላምቶች አሉ።

• የሆርሞን አለመመጣጠን በእርግዝና ወቅት የእንግደልጅ እጅግ በጣም ብዙ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ሲሆን ከእነዚህም PLG (plasental lactogen )አንዱ ነው። ይህም ሆርሞን ኢንሱሊን በህዋሳት ወስጥ እንዳይሰራ በማደናቀፍ የደም ውስጥ ስኳር እንዲጨምር ያደርጋል። ስቴሮይድ ሆርሞን እና የእድገት ሆርሞን እንደዚሁ በተመሳሳይ የኢንሱሊን ስራን በማስተጓጎል እንደ ምክነያት ይነሳሉ።

• አካባቢያዊ ተፅኖ በእርግዝና ወቅት የክብደት መጨመር ህዋሳቶች ለኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይታዘዙ ሊያደርግ ይችላል የሚል ሌላ መላምትም አለ።

🤹🏽‍♀️ለመጀመሪያ ጊዜ በርግዝና ወቅት የታወቀ ስኳር የቆየ መሆኑ አለመሆኑ እንዴት ይታወቃል?

• ከሃያ ሳምንት በፊት የተከሰተ ስኳር
• HgA1C ከ7% በላይ ከሆነ
• የረጅም ጊዜ የስኳር ህመም ውስብስ ችግሮች ካሉ ለምሳሌ የአይን ችግሮች ፣ የኩላሊት ህመም የመሳሰሉት
• የልጅ የአፈጣጠር ችግር ካለ
የቆየ ስኳር አመላካቾች ስለሆኑ በድህረ ወሊድ ጊዜ በድጋሚ ክትትል ያሻል።

🎗ውስብስብ ችግሮች

የእረግዝና ወቅት ስኳር በእናትና በፅንስ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል

እናት ላይ
• ፅንሱ በመመፋፋቱ ምክንያት ለኦፕራሲዮንና ለመሳሪያ ወሊድ መጋለጥ
• የምጥ መርዘም
• ለልብ ችግር ተጋላጭነት መጨመር
• በወሊድ ወቅት ደም መፍሰስ
• የእንግደ ልጅ መቅደም

ፅንሱ ላይ
• የፅንስ መፋፋት
• ያለጊዜ መወለድ እና የአተነፋፈስ ችግር
• የስኳር ማነስ (hypoglycemia)
• የፅንስ መታፈን
• ሆድውስጥ መጥፋት
• ተደጋጋሚ ውርጃ
• የጨቅላ ቢጫነት
• የጨቅላ ሙቅት መውረድ (hypothermia)

🎟 ህክምናውስ?

• የአኗኗር ዘዬ መቀየቀር ፦ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚፈቀዱ መጠነኛ እንቅስቃሴዎችን መድረግ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በመተው አልያም በመቀነስ የደም ስኳርን መቆጣጠር ይቻላል።

• መድሃኒት፦ የአኗኗር ዘዴ በመቀየር ካልተስተካከለ ወይም በሃኪምሽ ከታመነበት መርፌ (insulin) ወይም ኪኒን (oral hypoglycemic agent) በመጠቀም የደም ስኳርሽ ማስተካከል ይቻላል።

• የስኳር ህመም ውስብስብ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ ቁርስ ከመብላትሽ በፊትና በማንኛውም ጊዜ ምግብ ከበላሽ ከሁለት ሰዓት በኋላ የስኳር መጠንሽን መለካት አትርሺ

• መለካት ብቻ በቂ ስላልሆነ የለካሽውን በመመዝገብ በክትትልሽ ወቅት ለሃኪሞችሽ በማሳየት የመድሃኒትሽ መጠን ለማስተካከል ይረዳል።

• ከፍተኛ የስኳር መጠን ካለሽ ደግሞ ሆስፒታል ተኝተሽ ጥብቅ የፅንስ ክትትል እና የስኳር ልኬት ሊደረግልሽ ይችላል።

☔️🍦እንዴት መከላከል ይቻላል?

አጋላጭ ሁነቶችን በመቀየር ማለትም ከእርግዝና በፊት ክብደት ማስተካከል፣ ጤነኛ የአኗኗር ዘዴን መከተል ፣ ስፓርት እንቅስቃሴ መስራት ፣ ጭንቀት ማስወገድ ፣ አደገኛ አመጋገብ በማስቀረት (ጣፋጭ ፣ አልኮሆል፣ ጮማ እና ጨው) በመተው ፣ በቂ ውሃ በመጠጣት እና በቂ እረፍት በማድረግ) ስኳር እና ሌሎች ቋሚ ህመሞችን መከላከል ይቻላል።

በወቅቱ የእርግዝና ክትትል በማድረግ የስኳር ምርመራ በማድረግ በወቅቱ መታከም።

የወደፊት እጣፈንታውስ?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር በአብዛኛው ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ሲሆን የተወሰነው ግን ወደሁለተኛው የስኳር አይነት ሆኖ ሊቀጥል ይችላል።

• የወደፊት የስኳር ህመም ፣ የደም ግፊት እና የልብ ህመሞች ተጋላጭነትን ይጨምራል።

• የወደፊት የእርግዝና ወቅት ስኳር እና አለቅጥ ውፍረትን ያጋልጣል።

• ስለዚህ ድህረ ወሊድ ከስድስት ሳምንት በኋላ የስኳር መጠን በመለካት እና በየ ጊዜው በመመርመር ቋሚ የስኳር ህመም እንደሌለሽ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ዶ/ር ነጋልኝ መቻል ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

03/01/2025

Linktree. Make your link do more.

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኢትዮሜድካል / Ethiomedical posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram