27/02/2026
የዳሌ መገጣጠሚያን የመታደግ ህክምና
የዳሌ ራስ መበስበስ (AVN) እንዳለብዎ ታውቋል? ተስፋ አይቁረጡ! መፍትሄው እጃችሁ ላይ ነው፤ ቁልፉ "ጊዜ" ነው! ⏱️
የዳሌ ራስ መበስበስ በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች (ደረጃ 1 & 2 ) ላይ ከተገኘ፣ የራስዎን ተፈጥሮአዊ የመገጣጠሚያ አጥንት በሰው ሰራሽ ሳይቀየር ማዳን ይቻላል። አጥንትን ለመታደግ የሚረዱ ዋና ዋና የሕክምና አማራጮች፦
1️⃣ የዳሌ ራስን ማስተንፈስ እና የዘር ግንድ ህዋስ ህክምና
ይህ የቀዶ ህክምና ሂደት በአጥንቱ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ ግፊት በመቀነስ ወደ አጥንቱ የሚሄደውን የደም ዝውውር እንዲመለስ ያደርጋል።
ቀዶ ህክምናው የማያስፈልገው እና የሞቱ ህዋሳትን ዳግም የማደስ ሕክምና ነው። ከታካሚው የዳሌ አጥንት ላይ የራሱን መቅኒ ህዋሳት በማውጣት ጉዳት ወደደረሰበት የአጥንት ክፍል በመውጋት አጥንቱ ራሱን እንዲጠግን ይደረጋል። ይህ ሕክምና በአብዛኛው ከዳሌ ራስ አጥንትን በመብሳት የማስተንፈስ ህክምና (core decompression) ጋር ተቀናጅቶ የሚሰጥ ሲሆን፣ የአጥንት መውደቅን እና መሰባበርን በአስተማማኝ ሁኔታ ይከላከላል።ይህም አዲስ አጥንት እንዲያድግና እንዲተካ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
2️⃣መንስኤውን በአስቸኳይ ማስቆም
ማንኛውም ህክምና ውጤታማ እንዲሆን እነዚህን እርምጃዎች መውሰድ ግዴታ ነው፦
-የስቴሮይድ (ዴክሳ/Dexa) መድሃኒቶችን ያለአግባብ መውሰድ በአስቸኳይ ማቆም!
-አልኮል እና ሲጋራን ሙሉ በሙሉ ማቆም፡፡
⚠️ ማሳሰቢያ፦ መንስኤዉን ካላቆሙ የዳሌ ራስን የማትረፋ ህክምና ዉጤት ላይኖረዉ ይችላል::
3️⃣ አጋዥ መድሃኒቶች
በሀኪም ትእዛዝ የሚሰጡ፣ የአጥንት ጥንካሬን የሚጨምሩ እና አጥንት እንዳይፈራረስ የሚረዱ መድሃኒቶች እንደ ተጨማሪ መፍትሄ ያገለግላሉ።
ጤናዎ በእጅዎ ነው! ምልክቶቹን ቀድመው በመለየት እና ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ የራስዎን አጥንት ይታደጉ። 🙏
📌 መረጃው ለሌሎችም እንዲደርስ እና ህይወትን እንዲያተርፍ Share ያድርጉ!
_ _
Have you been diagnosed with Avascular Necrosis (AVN) of the hip? Don’t lose hope! The solution is in your hands, the key thing
is “time”!
If avascular necrosis of the hip is detected in its early stages (Stage 1 and 2), it is possible to save your natural hip joint without replacing it with an artificial one.
Main treatment options that help preserve the bone include:
1️⃣ Core Decompression and Stem Cell Therapy
This surgical procedure reduces the high pressure inside the bone and helps restore blood flow to the affected area.
Stem cells are taken from the patient’s own bone marrow and injected into the damaged area of the bone to help it heal and repair itself.
This treatment is often combined with core decompression and can significantly help prevent bone collapse and further damage.This creates a favorable environment for new bone to grow and replace the damaged bone.
2️⃣ Stopping the cause immediately
For any treatment to be effective, the following steps are essential:
-Stop inappropriate use of steroid medications (such as Dexa/dexamethasone) immediately
-Completely stop alcohol consumption and smoking
⚠️ Reminder: If the cause is not stopped, bone-preserving treatments may not be successful.
Supportive medications
Medications prescribed by your doctor can help strengthen the bone and prevent further bone damage. These are used as supportive treatment.
Your health is in your hands! Detect the symptoms early and visit a medical facility to save your bone.
📌 Share this information so others can benefit and save their quality of life!