Medan home care nursing service መዳን የቤት ለቤት ህክምና

Medan home care nursing service መዳን የቤት ለቤት ህክምና Home care service

17/05/2022
04/04/2022

የእንቅልፍ አተኛኘት አቅጣጫ ጥሩ እና መጥፎ ጎናቸው!

1. በጀርባቸው የሚተኙ!

🔻 ጥቅሙ

በጀርባ መተኛት ትራስ አከርካሪን የመደገፍ ሥራውን በትክክል እንዲወጣ ይረዳዋል። በትክክለኛው አለም ሁሉም ሰው ትራስ ሳይጠቀም በጀርባው መተኛት ይፈልጋሉ፤ ይህም አቅጣጫ አንገታችን ነፃ አቅጣጫ ላይ እንዲሆን ይረዳዋል። ከመጠን በላይ/ብዙ ትራስ መጠቀም የአተነፋፈስ ሥርዓትን አስቸጋሪ ያደርገዋል።

በጀርባ መተኛት ውበትን ከመጠበቅ አንፃር ይመከራል፤ ሌሊቱን ሙሉ ፊታችን ለንጽህ አየር እንዲጋለጥ በማድረግ ይረዳል። የተጠቀምነው የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲክስ በትራሱ እንዳይጠረግ ከማድረጉ በተጨማሪ የፊት መሸብሸብን ወይም መጨማደድን ይቀንሳል።

🔻 ጉዳቱ

ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ እጦት በጀርባ ተንጋሎ ከመተኛት አቅጣጫ ጋር ይያያዛሉ። በነገራችን ላይ በጀርባ መተኛት ከእንቅልፍ እጦት ጋር በቅርበት የተገናኘ ነው ለዚህም ነው ዶክተሮች በጎን አቅጣጫ በኩል መተኛትን እንደመፍትሄ የሚመክሩት።

በጀርባችን በምንተኛበት ወቅት የመሬት ስበት ሃይል የምላሳችን ሥር ወደ አየር ቧንቧ አቅጣጫ እንዲታጠፍ ያስገድደዋል ይህም ሥርዓተ ትንፈሳን በማስተጓጎል ጎረቤትን እንቅልፍ የሚነሳ አስቀያሚ ማንኮራፋት እንዲፈጠር ያደርጋል።

ጥሩ እንቅልፍ የሚተኙ እና ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎችን በማነፃፀር የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው፦ ጥሩ ያልሆነ እንቅልፍ የሚተኙ ሰዎች አብዛኛውን የመኝታ ጊዜ የሚያሳልፉት በጀርባቸው እንደሆነ አረጋግጠዋል።

2. በጎናቸው የሚተኙ!

🔸 ጥቅሙ

በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች በአንድ ላይ! ማህፀን ውስጥ እንዳለ ጽንስ እግራቸውን እጥፍጥፍ አድርገው የሚተኙ እና እግራቸውን ዘርግተው የሚተኙ ሰዎች፤ አብዛኛው ማህበረሰብ በጎን በኩል እንደሚተኙ ሪፓርት ተደርጓል።

በእርግዝና ወቅት በግራ ጎን በኩል እንዲተኙ ዶክተሮች ይመክራሉ፤ ምክንያቱም ወደ ልብ ያለውን የደም ፍሰት ስለሚጨምር ነው ይህም ለእናት እና ልጅ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።

በእርግዝና ወቅት በጎን በኩል እንድትተኚ ይመከራል ምክንያቱም በጀርባ በኩል መተኛት የታችኛው ጀርባ ላይ ግፊት ይፈጥራል (በአብዛኛው ፌንት እንድታደርጊ አስተዋጽዎ ያድርጋል)። እንደሚታወቀው በእርግዝና ወቅት በሆድ በኩል መተኛት አይቻልም።

🔸 ጉዳቱ

በተመሳሳይ ሁኔታ በግራ ጎን በኩል መተኛት ሆድ እና ሳንባ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደርጋል። ሁሉም በጎናቸው የሚተኙ ሰዎች እንደሚያውቁት በዚህ አቅጣጫ በሚተኙበት ወቅት የእጅ መደንዘዝ ሊያጋጥም ይችላል።

ጭንቅላትን እጅ ላይ አስደግፎ መተኛት የተለመደ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን በጡንቻ እና ነርቭ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ያስከትላል። ጭንቅላትን (አጠቃላይ ሰውነትን) በአንድ እጅ ላይ ማሳረፍ የደም ፍሰትን ይከለክላል በተጨማሪም ነርቭን ወደታች ይጫናል።

3. በሆዳቸው የሚተኙ!

🔹 ጥቅሙ

በሆድ በኩል መተኛት ማንኮራፋት እና የእንቅልፍ ችግርን ያስቀራል። ነገር ግን በጣም ጥሩ የሚባለው ጎኑ በሌሊት ሠዓት ቦርጫችን ወደ ውስጥ እንዲገባ ያደርጋል።

🔹 ጉዳቱ

በሆድ በኩል መተኛት በአብዛኛው እንደሚታወቀው በጣም አስቀያሚ የሚባል የአተኛኘት አቅጣጫ ነው።
የአከርካሪ የተፈጥሮ መንጋደድን በማዛባት ቀጥ እንዲል ያደርገዋል ይህም የታችኛው ጀርባ ህመምን ያስከትላል።

ሌሊቱን ሙሉ ጭንቅላትን ወደ አንድ አቅጣጫ አድርጎ መተኛት የአንገት ህመምን ያስከትላል። ይህ የአተኛኘት አቅጣጫ ምርጫዎ ከሆነ ትራስ በመጠቀም ሰውነትዎ በአንድ አቅጣጫ መተኛትም ያለማምዱት።

19/03/2022

Home care nursing service

https://t.me/MHCNS
08/03/2022

https://t.me/MHCNS

፨ በደም ስር የሚሰጡ መድሀኒቶችን እንሰጣለን ፨ የተለያዩ ቁስሎችን ማጠብና መንከባከብ ፨ የሽንት መሽኛ ቱቦ ማስገባት ፨ በፅኑ የታመሙ ሰዎች መንከባከብ ፨ ለ ስትሮክ ታማሚ የፊዚዮቴራ.....

11/01/2022
09/12/2021

We follow 1 -DM
2-Stroke
3- Hypertension
4-Paralayis patient
5-Childeran and Wound care etc ...in your home ...coming soon

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medan home care nursing service መዳን የቤት ለቤት ህክምና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram