19/08/2025
🇪🇹 ኢትዮጵያ የፈቃድ ሞትን ተግባራዊ ማድረግ ልትጀምር ነው
| የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ጥር ወር በሕክምና ባለሙያ የታገዘ ሞት የሚፈቅድ አዋጅ ማፅደቁን ተከትሎ፤ ጤና ሚኒስቴር ሕጉን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱ ተዘግቧል።
ረቂቅ መመሪያው ውሳኔው ከመተላለፉ በፊት በትንሹ ሶስት የጤና ባለሙያዎች በምርመራው ላይ መስማማት እንዳለባቸው ይደነግጋል። በተጨማሪም የቅርብ ዘመዶች የሕመምተኛው ሕይወት ማቆያ ድጋፍ እንዲነሳ በጽሁፍ በፈቃዳቸው መጠየቅ እንደሚችሉ ያስቀምጣል።
አዋጁ በመሳሪያ ላይ ብቻ የተመሠረተ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲቋረጥ ይፈቅዳል፡፡ ሕጉ ተግባራዊ የሚሆነው የልብ እና የመተንፈሻ አካላት የአሠራር ሥርዓት መመለስ በማይቻልበት ደረጃ ሥራቸውን ሲያቆሙ ወይም የአንጎል ሞት ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
ሕጉ በማይድን ህመም የሚሰቃዩ ዜጎችን ለመርዳት ያለመ ነው ተብሏል ሲል ሰፑትኒክ ዘግቧል፡፡
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)