27/01/2026
በወንዶች ላይ ብቻ ስለሚከሰተው - የፕሮስቴት እጢ እብጠት፦
✔ ምልክቶች:-
➲ሽንት ለመሽናት መቸገር ፣ ከሸኑ በኋላ አለመጨረስ ስሜት ፣ መንጠባጠብ ፣ ማታ ማታ በተደጋጋሚ ሽንት ለመሽናት መነሳት ወዘተ...አጠቃላይ የሽንት እንቅስቃሴ ላይ መስተጓጐል ያመጣል።
✔ምክንያቶች
➾የእድሜ መግፋት (ከ60 አመት በላይ ያሉ ወንዶች 50በመቶ ይህ እጢ እንደሚገኝ በናሙና ምርመራ ተረጋገጧል፣ እድሜያቸው 85 እና በላይ የሆኑት ላይ ይህ አሀዝ 90በመቶ ይጠጋል)
➾የሆርሞን ባላንስ ችግር
➾በቤተሰብ ታሪክ ውስጥ ካለ
➾ውፍረት፣ የስኳር ህመም...ናቸው።
✔ህክምናው
➾አነስተኛ ምልክት ላላቸው :-የኑሮ ዘይቤ ማሻሻል እና ክትትል ይደረጋል(Watchful waiting )
➾የመድሀኒት ህክምና
➾መካከለኛ እና ከባድ ምልክት ላሳዪ ሰዎች :-መለስተኛ እና ከፍተኛ ቀዶ ህክምና (minimally invasive procedure --or-- TURP, prostatectomy ) ይደረጋል።
✔ይህ እብጠት - ካንሰር ያልሆነ እብጠት ነው።
✔እክሉ:- ከፍተኛ ለመሽናት መቸገርን፣ ደም የቀላቀለ ሽንትን፣ ተደጋጋሚ የሽንት ቧንቧ ካመጣ እንዲሁም የሽንት ፍኛ ጠጠር ከፈጠረ ➲ሀኪምዎን መማከር አለብዎት።