Bethel Teaching General Hospital & its Sister Companies

Bethel Teaching General Hospital & its Sister Companies Bethel Teaching General Hospital-BTGH COMMITTED FOR EXCELLENCE

13/02/2015

Bethel Teaching General Hospital invites again all Ethiopian medical communities to use its 64 slice CT scanner. You can get the service at Bethel Hospital no 2 near Awash Winery

ቤቴል ሆስፒታል በ13፣ በ15ና በ17 ዓመት የዕድሜ ክልል የእግር ኳስ ቡድኖቹ ተወዳድሮ ሁለት ዋንጫዎች አግኝቷል፡፡ ይህንኑ በፎቶ እንቃኘው
04/02/2015

ቤቴል ሆስፒታል በ13፣ በ15ና በ17 ዓመት የዕድሜ ክልል የእግር ኳስ ቡድኖቹ ተወዳድሮ ሁለት ዋንጫዎች አግኝቷል፡፡ ይህንኑ በፎቶ እንቃኘው

03/02/2015

አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው ቤቴል ሆስፒታልን አደነቁ

ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ እንድታልፍ ያደረጉት ታዋቂው አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የግል ተቋማት እግር ኳስን በመደገፍ ስፖርቱ የተሻለ ደረጃ ላይ እንዲደርስ ማድረግ እንደሚችሉ አስታወቁ፡፡ ቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ13 እና በ15 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኙ የእግር ኳስ ቡድኖቹ ሻምፒዮን ሆነው ዋንጫ አግኝተዋል፡፡


አሠልጣኝ ሰውነት ቢሻው የቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል የእግር ኳስ ቡድኖች ዕሑድ ጥር 24 ቀን 2007 ዓ.ም በነበራቸው የመጨረሻ የዋንጫ ውድድር ላይ ተገኝተው እንደገለፁት በዓለም ላይ በእግር ኳስ ታዋቂ የሆኑት ሁሉ የጀመሩት በልጅነታቸው ሲሆን ሆስፒታሉ ይህንኑ ተገንዝቦ በታዳጊዎች ላይ የተመሠረተ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ማድረጉ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል፡፡


ይህን የቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል ጥረት ሌሎችም ሊከተሉት እንደሚገባ የጠቆሙት አሠልጣኝ ሰውነት ሆስፒታሉ በዚህ መሰሉ ተግባር ሲሳተፍ የመጀመሪያው እንዳልሆነ እንደሚያውቁ አመልክተዋል፡፡

ሆስፒታሉ የጀመረውን እንቅስቃሴ በማጠናከር በጥራት ወደ ማዘጋጀት ደረጃ መድረስና ለብሔራዊ ቡድን የሚበቁበትን ሁኔታ ማመቻቸት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡


በአሠልጣኝ ሰለሞን አንቼ የሚመሩትና ቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በ13 እና በ15 ዓመት ዕድሜ ክልል ያቀፋቸው የእግር ኳስ ቡድኖቹ ተጋጣሚዎቻቸውን በ13 ዓመት የቤተሰብን ቡድን በ15 ዓመት ደግሞ የቤተል አካባቢን ቡድኖች በአምስቱ መለያ ምቶች በማሸነፋቸው ከዕለቱ የክብር ዕንግዶች የዋንጫ ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

በዕለቱ ሮም ሜዳ እየተባለ በሚጠራው የመወዳደሪያ ሜዳ በ17 ዐመት ዕድሜ ክልል በተደረገው ውድድር የቤተሰብ ቡድን የሆስፒታሉን ቡድን በአምስቱ መለያ ምቶች አሸንፎ ዋንጫ ወስዷል፡፡

በኮልፌቀራንዮ ክፍለከተማ የወረዳ 7 ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስቻለው ፈራኒ ቤቴል ቲቺንግ አጠቃላይ ሆስፒታል በስፖርት ብቻ ሳይሆን በአካባቢ ልማትና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከአሜሪካ የመጡት ሚስተር ካየል ሳንደርስና ቀድሞ የእግር ኳስ ዳኛ የነበሩት ወይዘሮ ፍቅርተ ይትባረክ ባዩት የታዳጊዎች ውድድር መደሰታቸውንና ለቡድኖቹ የአቅማቸውን ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን አመልክተዋል፡፡

በ13፣ በ15ና በ17 ዓመት የዕድሜ ክልል የተወዳደሩት የሆስፒታሉ ቡድን አባላት ምሽት ላይ የራት ግብዣ በተደረገላቸው ወቅት የሆስፒታሉ ባለቤት ዶክተር ይገረሙ አስፋው በተወካያቸው በኩል ባስተላለፉት መልዕክት እንኳን ደስ ያላችሁ ካሉ በኋላ ሆስፒታሉ ምንጊዜም ከጎናቸው መሆኑንና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግላቸው አስታውቀዋል፡፡

16/01/2015

Bethel is providing training on 64 slice CT Scanner

Bethel Teaching General Hospital is giving training to its radiologists & radiographers in its no. 2 hospital.

The training which focuses on the newly brought 64 slice CT Scanner application is being given by the application specialist Gregory Muzikanski from Israeli company ELSMED.

Mr. Muzikanski said the focal point of the five days training is to adhere the professionals to the adjustable approach of the application of the newly built CT Scanner.

One of the trainees Dr. Hailemariam Berhane said in his part even though the training is at its beginning stage it is attractive & worthy.

The ICT head of the hospital Tibebu Solomon said his department is playing a role in facilitating the training.

CONGRATULATIONS TO ALL BETHEL TEACHING GENERAL HOSPITAL EMPLOYEESA NEW CHAPTER IS WRITTEN !OUR LABORATORY IS ACCREDITTED...
29/12/2014

CONGRATULATIONS TO ALL BETHEL TEACHING GENERAL HOSPITAL EMPLOYEES

A NEW CHAPTER IS WRITTEN !

OUR LABORATORY IS ACCREDITTED BY ENAO

THIS MEANS THAT THE LAB RESULT IS ACCEPTABLE ALL OVER THE WORLD

THE PHOTOS SHOW SOME OF THE ACTIVITIES OF AWARDING & WELCOMING CEREMONY

Photos show activities of Physicians from Wings of Healing-UK
27/12/2014

Photos show activities of Physicians from Wings of Healing-UK

25/12/2014

ENAO accredits four organizations

Written by LEULSEGED WORKU

Ethiopian Herald reported that the Ethiopian National Accreditation Office (ENAO) certified two medical, one testing and one inspection organization yesterday at Kaleb Hotel.

Awarding the organizations, Office Director General, Araya Fisseha, said that the organizations are awarded after the accreditation approval committee witnessed their competence.

According to him, the overall aim of the accreditation is to improve the quality and competency of different sectors.

Organizations awarded by the Accreditation Office for meeting several international standards are the Sante Medical Center Laboratory, the Ethiopian Conformity Assessment Enterprise, the Bethel Teaching General Hospital and the Addis Ababa Abattoirs Enterprise.

The Accreditation Office’s vision is to be identified as a leading example where the credibility of an internationally recognized accreditation body plays a critical role in support of the National Quality Infrastructure (NQI). By so doing it intends to contribute its share to the rise of the economic development and the reduction of poverty in the nation, Ethiopian Herald announced.

25/12/2014

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ለአራት ተቋማት ዕውቅና ሰጠ

በሺቢያምጽ ደምሰው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ አክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ለሁለት የሕክምናና ለአንድ የፍተሻ እንዲሁም ለአንድ የኢንስፔክቴሽን ተቋም አክሬዲቴሽን ሰጠ፡፡

ሪፖርተር ጋዜጣ ትናንት እንደዘገበው አክሬዲቴሽን የተሰጣቸው ሳንቴ የሕክምና ማዕከልና ቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲሆኑ በፍተሻው ዘርፍ ደግሞ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፤ በኢንስፔክሽን ዘርፍ ደግሞ የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅቶች ናቸው፡፡

በሕክምና ላብራቶሪ ሳንቴ የሕክምና ማዕከል በሁለት የፍተሻ መስኮች አክሬዲቴሽን ያገኘ ሲሆን፣ እነሱም በሔማቶሎጂ (በነጭና ቀይ የደም ሴል ቆጠራ ላይ በሚያተኩር ምርመራ) ላይ እና በክሊኒካል ኬሚስትሪ የፍተሻ መስኮች ናቸው፡፡

ሌላው አክሬዲቴሽን የተሰጠው ቤተል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል ዕውቅና ያገኘው በኢንዶክሪኖሎጂ (የእንቅርት በሽታ ምርመራ) ብቃት ማረጋገጫ ነው፡፡

አዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ደግሞ በኬሚካል የፍተሻ መስክ፣ የሥጋ ተረፈ ምርት፣ የአጥንትና የውሻ ምግብ ውስጥ ያሉ የፕሮቲንና የእርጥበትና የስብ መጠንን መፈተሽ በሚያስችል የጥናት መስክ ዕውቅና አግኝቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለሳሙና ፋብሪካዎች የሚውል ኖራ በማቅረብም ዕውቅና እንደተሰጠው ተገልጿል፡፡

ጽሕፈት ቤቱ በኢንስፔክሽን ዘርፍ ዕውቅና የሰጠው የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በቅባት እህሎች አወሳሰድ፣ በቅባት እህሎች ውስጥ ያሉ ባዕድ ነገሮችን ለመለየትና እንዲሁም በሰብልና በጥራጥሬ እህሎች ናሙና አወሳሰድ ደረጃ አሰጣጥ ዕውቅና አግኝቷል፡፡

በአጠቃላይ ጽሕፈት ቤቱ የአሁኑን ጨምሮ እስካሁን ለ22 ተቋማት ዕውቅና የሰጠ ሲሆን፤ ዕውቅና ያገኙት አራት ተቋማትም በየስድስት ወራት ዕውቅና በተሰጣቸው መስኮች በአግባቡ መሥራታቸውን እንደሚያረጋግጥ ገልጿል፡፡ በተያዘው ዓመት ለሌሎች ስምንት ተቋማት ዕውቅና ለመስጠት እየሠራ መሆኑን መሥሪያ ቤቱ አሳውቋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው የኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሪዲቴሽን ጽህፈት ቤት በተቋማት መካከል ያለምንም መድሎ የእውቅና አገልግሎት እየሰጠ ነው ብሏል

ጽህፈት ቤቱ በሕክምና ቤተሙከራና በፍተሻ ቤተሙከራ በውስን የፍተሻ ወሰኖች አክሬዲት የሆኑና በሰርቲፈኬሽን አገልግሎት የተሰማራ አንድ ተቋም የእውቅና ሰርተፊኬት ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት፣ ቤቴል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል፣ ሳንቴ ሜዲካል ማዕከልና የኢትዮጵያ ተስማሚነትና ምዘና ድርጅት የእውቅና ሰርቴፊኬቱን የወሰዱ ተቋማት ናቸው።
የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ጽህፈት ቤቱ ከተሰጠው አገራዊ ተልዕኮ አንጻር የግልም ሆነ የመንግስት የህክምና ተቋማት የቤተሙከራ ምርመራ እንዲሁም የፍተሻ አገልግሎት ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የእውቅና ሰርተፊኬት እየሰጠ ይገኛል።

በዛሬው እለት ሰርተፊኬት ያገኙ ተቋማትም በውስን የህክምና የቤተሙከራና የፍተሻ ቤተሙከራ ዘርፍ ጽህፈት ቤቱ ያስቀመጠውን ዓለም ዓቀፍ ደረጃ በማሟላታቸው ነው።
አቶ አርአያ እንደሚሉት ለተቋማት የሚሰጠው እውቅና በተለይ በህክምናው ዘርፍ ያለውን የዜጎች ደህንነት ከማረጋገጥ አኳያ የማይተካ ሚና ይጫወታል።

በተጨማሪም በአገሪቱ ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በማስቻል ለውጭ አገር የሚላኩ ምርቶች በገበያ ተፈላጊ በማድረግና ተወዳዳሪነትን በመጨመር ለአገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋልም ብለዋል።
የአክሬዲቴሽን ሰርተፊኬቱ ከተሰጠ በኋላ ተቋማት በመስፈርቱ መሰረት እየሰሩ መሆናቸውን በየ6 ወሩ ክትትል ይደረጋል ነው ያሉት አቶ አርአያ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ አክሪዲቴሽን ጽህፈት ቤት እስካሁን ወደ 22 ለሚጠጉ ተቋማት የእውቅና ሰርተፊኬት የሰጠ ሲሆን ሦስቱ በልዩ ልዩ ምክንያት እውቅናቸው እንዲነሳ ተደርጓል፡፡

25/12/2014

የእንግሊዝ የሀኪሞች ቡድን በአዲስ አበባ ነፃ የማህፀን ዕጢና የማህፀን አፍ ካንሰር ህክምና ሰጠ

ዊንግስ ኦፍ ሂሊንግ የተሰኘ የእንግሊዝ የሀኪሞች ቡድን በማህፀን ዕጢና በማህጸን አፍ ካንሰር ህመም ለሚሰቃዩ እናቶች አዲስ አበባ ውስጥ ነፃ የሕክምና አገልግሎት አበረከተ።

ቡድኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በሰጠው ነፃ የህክምና አግልግሎት ባለፉት ሦስት ዓመታት ከ700 የሚበልጡ እናቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሴቶችን ለህልፈት ከሚዳርጉ በሽታዎች መካከል የማህፀን አፍ ካንሰር በሁለተኛነት መቀመጡን የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።

በየዓመቱ ከ270 ሺህ በላይ ሞት በበሽታው ይከሰታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው ሞት በታዳጊ አገራት የሚደርስ እንደሆነ ነው መረጃው የሚያስረዳው።

የማህፀን አፍ ካንሰር በሽታ ሥር ሳይሰድ በሚሰጥ የሕክምና አገልግሎት ሙሉ በሙሉ መፈወስ እንደሚችል ነው የዓለም የጤና ድርጅት የሚገልጸው።

በኢትዮጵያ ከሥነ-ተዋልዶ ጤና ጋር በተያያዘ ለሴቶች ሞት በምክንያትነት ከተለዩት በሽታዎች መካከል የማህፀን አፍ ካንሰር ተጠቃሽ ነው።

በአገር አቀፍ ደረጃ አብዛኞቹ የማህፀን አፍ ካንሰር ታማሚዎች ወደህክምናው የሚመጡት በሽታው ሥር ከሰደደና ከተሰራጨ በኋላ በመሆኑ በቀላሉ ለማከምና ለማዳን ፈታኝ እንደሚያደርገው ነው ህሙማንና የመስኩ ባለሙያዎች የሚገልጹት።

በእንግሊዝ የኃኪሞች ቡድን እየተሰጠ ባለው የሕክምና አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል ወይዘሮ ማርታ ዘለቀ አንዷ ናቸው።

ወይዘሮዋ ለሁለት ዓመታት በማህፀን አፍ ካንሰር በሽታ ቢሰቃዩም በሽታውን ለመታከም በሚጠይቀው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን መታከም እንዳልቻሉ ነው ያስረዱት።

የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱን ካገኙ ታካሚዎች መካከል ወይዘሮ ሸዋዬ አበበ ህክምናውን ለማግኘት ሆስፒታል ቢሄዱም ለስድስት ወር ቀጠሮ እንደተሰጣቸውና አሁን ግን ነፃ ህክምና በአጭር ጊዜ አግኝተው መታከማቸውን ተናግረዋል።

ሌላ የቀዶ ሕክምና አገልገሎቱ ተጠቃሚ የሆኑት ወይዘሮ ትዕግስት በዙ በበኩላቸው ህክምናውን ለማግኘት የሆስፒታል ቀጠሮ ይዘው በመጠባበቅ ላይ እንደነበሩና አሁን ግን ህክምናውን በነፃ ማግኘታቸው ከህመሙ እንዲፈወሱ እንዳስቻላቸው ገልጸዋል።

የእንግሊዝ የኃኪሞች ቡድን መሪና የጽንስና ማህፀን ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ኦንሲ ሉካን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ቡድኑ ወደ ኢትዮጵያ በዓመት ሁለት ጊዜ በመምጣት ለማህፀን ዕጢና ለማህፀን አፍ ካንሰር ህሙማን በነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

"ቡድኑ በቀን ለስምንት ሴቶች አገልግሎት ይሰጣል" ያሉት የቡድን መሪው በቆይታውም አንድ መቶ የሚሆኑ ሴቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

ህክምናው እየተሰጠበት ያለው የቤተል ሆስፒታል ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶክተር ይገረሙ አስፋው ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳሉት በአገሪቱ የማህፀን ዕጢና የማህፀን አፍ ካንሰር ህሙማን ቁጥር እያደገ ነው።

ህሙማን የህክምና አገልግሎቱን ለማግኘት በተራዘመ ቀጠሮና በገንዘብ እጥረት ምክንያት መንገላታት ብሎም የሞት አደጋ እንደሚጋረጥባቸው አስረድተዋል።

ይህን ሁኔታ ለመቅረፍ ሆስፒታሉ ከእንግሊዝ የመስኩ የህክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ውስጥ የህክምና አገልገሎቱን በነፃ እንዲሰጥ መደረጉን ነው የተናገሩት።

የቡድኑ አባላት ከሚሰጡት ነፃ የሕክምና አገልግሎት ባሻገር ለኢትዮጵያውያን የመስኩ ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር እያስገኙ እንደሚገኙም አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የእናቶች ሞትን ለመቀነስ የህክምና አገልግሎቱን በስፋት ማዳረስ አማራጭ የሌለው በመሆኑ ለጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት ይገኛል።

ከዚህ አኳያ የኢፌዴሪ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በብሄራዊ ደረጃ 118 በሚሆኑ የጤና ተቋማት በማህፀን በር ካንሰር ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው።

25/12/2014

Wings of Healing Provides Free Medication to Women

A medical group drawn from Wings of Healing, a UK-based charity organization, gave free medical service to women suffering from cervical cancer of uterine cancer at Bethel Teaching General Hospital in Addis Ababa.

More than 700 mothers have benefited from the free medication service the group provided during the past 3 years as ENA disclosed.

Cervical cancer is the second killer of women internationally, according to World Health Organization. Over 85 percent of the 270,000 women who die from the disease annually occur in developing country.

In Ethiopia too cervical cancer is among the reproductive health diseases that kills many women.

According to the leader of the medical group, Dr. Onsy Loukan, the group comes to Ethiopia twice in a year to provide free medication for victims of cervical cancer and uterine cancer.

The group, Dr. Loukan said, treated one hundred women during its stay.

04/11/2014

ቤቴል ቲቺንግ ጠቅላላ ሆስፒታል የምሥራች ይላችኋል

ሆስፒታላችን ‹‹ዊንግ ኦቭ ሂሊንግ›› ከተባለ የእንግሊዝ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር ከኅዳር 1 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ቀናት የነፃ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል፡፡ስለዚህ የመክፈል አቅም የሌላችሁና የማሕፀን ዕጢ፣ ካንሰርና ኦፕሬሽን የሚያስፈልገው ችግር ያለባችሁ ወገኖች ማስታወቂያውን ካወቃችሁ ጀምሮ ከወይራ ሠፈር ከፍ ብሎ በሚገኘው በቤቴል ቁጥር 1 እና አዋሽ ወይን ጠጅ ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው ቤቴል ቁጥር 2 ሆስፒታል በመምጣት መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

ቤቴል ለኅሙማን የሚሰጠውን አገልግሎት የላቀ ለማድረግ ምንጊዜም ይተጋል

02/09/2014

Bethel Medical College graduates health professionals

Bethel Medical College (BMC) graduated 105 health professionals
in degree and diploma.

The graduates are trained in clinical nursing, pharmacy, public health (HO) & level 4 clinical nursing.

BMC dean professor Legesse Zeryihun said during the ceremony held last Saturday the college graduated near 2000 students since its establishment 10 years ago.

The college has planned to build community hospital which has 70 beds, dormitories for students & various facilities.

BMC is providing training for almost 900 students among them 350 are medicine students (MD).

Certificates & medals for high grade scored students handed over by the dean & the college president Dr. Yigeremu Asfaw representative Dr. Tesfaye Mullat.

Address

Addis Ababa
9011

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bethel Teaching General Hospital & its Sister Companies posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category