28/12/2018
እባክዎን ሼር በማድረግ ከተመሳሳይ ጎጂ ምርቶች ለመከላከል የበኩላችንን እናበርክት
ድርጅታችን ቨርጂኒያ ፋርማሲዩቲካልስ በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ ከሚያመርታቸው ምርቶች አንዱ የሆነውና ዴንት ፕላስ(dentplus)(teeth whitening mouth wash) የሚባለውን የድድና የጥርስ ጤና ና ንፅህና መጠበቂያ ምርት በውጤታማነቱ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለው ተቀባይነትና ተወዳጅነት እየጨመረ መምጣቱን በመመልከት አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸውና ከህብረተሰቡ ጤና ይልቅ የራሳቸውን ኪስ ማዳበር ላይ ያተኮሩ ግለሰቦች ዴንት ፕላስን አመሳስለው በመስራት በየመንገዱና መድሃኒት ሊሸጥ በማይገባቸው ስፍራዎች ሲሸጡ በደረሰን ጥቆማ ከቁጥጥር ባለስልጣኑ ና ከህግ አስከባሪዎች ጋር በመተባበር እነዚህን ምንነቱ ያልታወቀ ግን ተመሳስሎ የተሰራ ምርት ለገበያ ሲያቀርቡ የነበሩ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።
ከዚህም ትምህርት በመውሰድ ህብረተሰቡ መድሃኒት ነክ ነገሮችን ከተገቢው ቦታ ብቻ ገዝቶ እንዲጠቀም እየመከርን፣ ከደንበኞች በተደጋጋሚ በቀረበልን ጥያቄ መሰረት ትክክለኛውን (original) ምርት ተመሳስሎ ከተሰራው (counterfeit) የምንለይበትን ነጥቦች ከታች እንገልፃለን።
በኢትዮጵያ የምግብ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው ትክክለኛ ምርት ስም (brand) ዴንት ፕላስ (dentplus) የሚል ሲሆን ከምርቱ በፊት በኩል በጉልህ ይታያል። ተመሳስሎ የተሰራው ምርት ግን ሀርባል ኮልጌት( herbal colgate) የሚል ነው።
ትክክለኛው ምርት ዴንት ፕላስ ፎቶው ላይ እንደምናየው የባች ቁጥርና(batch number) የመጠቀሚያ ጊዜ ማብቂያ(expiry date) ሲኖረው ተመሳስሎ የተሰራው ግን የባች ቁጥርም ኤክስፓየርም የለውም።
ትክክለኛው ምርት ዴንት ፕላስ ለደንበኞች ደህንነት ሲባል ክዳኑ የታሸገ ወይም safety seal ያለው ነው።
ትክክለኛውን የዴንት ፕላስ ምርት ከፋርማሲዎችና ህጋዊ ወኪሎቻችን ብቻ በመግዛት ጤናችንን እንጠብቅ ስንል ደንበኞቻችን ስለሆናችሁ እጅግ እያመሰገንን ነው።
ለበለጠ መረጃ +251 911 18 23 46፣ +251 923 00 00 ይደውሉልን