Medical Information

Medical Information በዚህ ገጽ ጤናን የተመለከቱ የሥራ ማስታወቂያዎች፤ ሕይወታዊ ቁም-ነገሮችና አጠቃላይ መረጃዎችን እንለዋወጥበታለን! Medical Media
(1)

Jimma University proudly announces and congratulates its first batch of Orthopedics and Trauma Surgery graduates --- Cla...
19/04/2026

Jimma University proudly announces and congratulates its first batch of Orthopedics and Trauma Surgery graduates --- Class of 2026!
CONGRATULATIONS 👏 ✔️

18/04/2026

በየካቲት ወር የተሰጠው የመውጫ ፈተና አኃዛዊ መረጃዎች፦

➫ 213,676 ተፈታኞች የ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተናውን ወስደዋል።

➫ 49,664 ተፈታኞች (23.24%) 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት አምጥተዋል (ቅሬታ አቅርበው የተስተካከለላቸውን ጨምሮ፡፡)

➫ የ12,166 ተማሪዎች ውጤት ተሰርዟል፡፡

● 2074 ተማሪዎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እና አካላዊ ነገር በመጠቀም ፈተና ክፍል ከገቡ በኋላ ለማጭበርበር የሞከሩ፡፡

● 817 ተፈታኞች የተለያዩ ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶችን የያዙና በተፈቀዱ ኮምፒውተሮች ላይ ያልተፈቀዱ ድርጊቶችን የማድረግ ሥራ ሲሰሩ እጅ ከፍንጅ የተያዙ፡፡

● 8645 ሌላ ሰው እንዲፈተንላቸው ያደረጉ ተማሪዎች ውጤት ተሰርዟል (ለመፈተን አጭበርብረው የገቡ ሰዎች አቴንዳንስ አይፈርሙም ነበር፡፡)

● 630 ከአንድ ግዜ በላይ ደግመው ለመፈተን የሞከሩ ተማሪዎች ውጤት ተሰርዟል (ፈተናው በሦስት ዙር መሰጠቱ ይታሳል፡፡)

(መረጃው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለፓርላማ ካቀረቡት ሪፖርት የተወሰደ ነው።)

የጠዳ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - Teda Health Science College በጤና ዘርፍ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 445 ተማሪዎች አስመረቀ።በጎንደር ከተማ የሚገኘው...
18/04/2026

የጠዳ ከፍተኛ ትምህርት ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - Teda Health Science College በጤና ዘርፍ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 445 ተማሪዎች አስመረቀ።
በጎንደር ከተማ የሚገኘው ኮሌጁ ለ21ኛ ጊዜ በፋርማሲ ቴክኒሽያን፣ በሜዲካል ላብራቶሪ እና በሚድዋይፈሪ እና በጤና መረጃ ቴክኒሽያን በአራት የመካከለኛ ደረጃ የጤና ሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 445 ተማሪዎች ዛሬ አስመርቋል።
የኮሌጁ ዲን አቶ ዘመነ ሐብቱ ተመራቂዎቹ በተለያዩ የጤና የሙያ ዘርፎች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸውን ገልጸዋል ።
ኮሌጁም ባለፉት 21 ዓመታት ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የጤና ዘርፎች በማሰልጠን ማስመረቁን ጠቅሰው፣ አሁን ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተሸጋገረበት ወቅት የተካሄደው ምረቃ ልዩ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 339 ሴቶች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ወንዶች መሆናቸውን ተናግረዋል ።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኘው የጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ማደጉ ለከተማው ማህበረሰብ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል
ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ ከመማር ማስተማር ባለፈ በማህረሰብና በምርምር ስራዎች ኮሌጁ አበረታች ስራ ማከናወኑንም ተናግረዋል ።
ክልሉ ለኮሌጁ እያደረገ ያለው አስተዋጽኦ በከተማ አስተዳደሩ ስም ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ምስጋና አቀርበዋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊና የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ አብዱልከሪም መንግሥቱ እንደገለጹት ውድ ተመራቂዎች የህብረተሰብ አገልጋዮች እንድትሆኑ ዛሬ እያበሰረንበት ቀን ነው።
ጤና ሙያ ልዩ ነው የምንለው በቀጥታ ሰው ህይወት የሚነካ በመሆኑም ነው ያሉት ቢሮ ኃላፊው ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባ አስረድተዋል ።
የክልሉ መንግስት የጤና ሽፋንና ጥራት ለማሳደግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።
ተመራቂዎች ለገጠር እና ተጋላጭ ለሆኑ ህብረተሰብ መድረስ እንደሚገባም አመላክተዋል ።
የመረጃ ስርዓትን ድጅታል በማድረግ ሳቢና ማራኪ ማድረጉ ኮሌጁ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው በቢሮው ስም ምስጋና አቅርበዋል ።
ተመራቂዎች ያላቸውን እውቀትን ማዳበር እና ቴክኖሎጂ መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

Notice from Teda Health Science College 🫵
18/04/2026

Notice from Teda Health Science College 🫵

17/04/2026

16/04/2026

በተለያዩ ሙያዎች ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ለመማር የተፈተናችሁ የፈተና ውጤት፣ የምትማሩበት ኮሌጅና መግቢያ ቀን በቴሌግራም ቻነል ለጥፈናል።
18/08/2018

ውል ይዛችሁ ወደ ትምህርት እንድትገቡ እናሳስባለን!ሼር አድርጉት፤ እንዳያልፋቸው!የሥም ዝርዝር በቴሌግራም ቻነል!
16/04/2026

ውል ይዛችሁ ወደ ትምህርት እንድትገቡ እናሳስባለን!

ሼር አድርጉት፤ እንዳያልፋቸው!

የሥም ዝርዝር በቴሌግራም ቻነል!

16/04/2026

Happy follow-versary to my awesome followers. Thanks for all your support! Ayalew Arage, Esayas Mamo, Amare Takele, እማያለፍ ዘመን

16/04/2026
Vacancy AnnouncementOzone Primary Hospital in Assosa is seeking a qualified General Practitioner to join our team.Requir...
15/04/2026

Vacancy Announcement

Ozone Primary Hospital in Assosa is seeking a qualified General Practitioner to join our team.

Requirements:
Minimum of 1 year experience (preferably in a private health facility)
Ability to start immediately

Salary:
80,000 ETB per month

Apply: Interested applicants can send their CV via
or
call: 📞 0915962878 (Dr. Fikiru)

Telegram

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ መዋቅራዊ ሂደት አስታውሳለሁ በ2011 አ.ም JEG (Job Evaluation & Grading) በጠቅላላ ሀገሪቱ ሲተገበር አማራ ክልል ላይ በልዩነት ጤናው ሴክተር ላይ ...
15/04/2026

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ መዋቅራዊ ሂደት

አስታውሳለሁ በ2011 አ.ም JEG (Job Evaluation & Grading) በጠቅላላ ሀገሪቱ ሲተገበር አማራ ክልል ላይ በልዩነት ጤናው ሴክተር ላይ ብቻ ለምን አልተተገበረም ብለን አንዳንድ ሰዎችን ከጤና ቢሮ እና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለመጠየቅ ሞከርን መልሱ በጊዜው የሚያስቅም የሚያናድድም ነበር።
መልሱ ጤና JEG አያስፈልገዉም ምክንያቱም ጤና ሴክተር ላይ እየሰራ ያለው አካል አሁን ባለበት ቦታ ላይ በአንድም በሁለትም ለብዙ አመት ስለሰራና እየሰራ ስለሆነ ከዚያም በተጨማሪ ብዙ ስልጠናዎችን ስለወሰደ ማንቀሳቀስ አይቻልም በሚል የጤና ቢሮ ማናጅመንት ስለወሰን ከዚያም በተጨማሪ የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይህንን ሃሳብ ስለተቀበለ የአማራ ክልል በልዩነት ጤና ሴክተር ላይ ያሉ አስተዳደር ሰራተኞች ላይ ብቻ ተሰርቶ ክልል ጤና ቢሮ፣ ዞን ጤና መምሪያ፣ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና ጤና ተቋማት ላይ ያሉ የጤና ባለሙያዎች ላይ ሳይሰራ ሁሉም ባለበት ይደልደል በሚል ተወስኗል የሚል መልስ ተሰጠን።
ይህ ማለት ደሞ Enviromental health ባለሙያ ሁኖ የእናቶች ባለሙያ ላይ፣ Nurse ባላሙያ ሁኖ የHygine ሙያ ላይ እንደዚህና ተመሳሳይ ሁነቶች በሁሉም ተቋማት ላይ ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ተከስቷል ማለት ይቻላል።
ይህ ማለት ደሞ አሁን ያለውን የበሽታና የህክምና አገልግልሎት ባላማከለ መልኩ ከ1997 አ.ም በፊት የነበረ አደረጃጀት ይቀጥል እንደማለት ነበር።

አሁን ላይ ደሞ BPR (Business processing reengineering) በሚል በ2018 አ.ም እንቅስቃሴዎች ማካሄድ እንደተጀመሩ ማየት ችያለሁ።

ስለ አሰራሩና እንዴት እንደነበረ ይህን ያህል ካልኩ JEG እና BPR ለምን መጡ አላማቸውስ ምን ነበር የሚለዉን ላንሳ፦

=>JEG (Job Evaluation & Grading) ዋና አላማ አድርጎ የተነሳው ሠራተኞችን በግልጸኝነት ፣ በፍትሀዊነትና በተጠያቂነት አወዳድሮ በመደልደል ሲቪል ሰርቪሱን ውጤታማ ማድረግ፣ በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ የተመዘኑና ደረጃ በወጣላቸው የሥራ መደቦች ላይ ተገቢውን ሠራተኛ
በተገቢው ቦታ መመደብ ነው።

ይህን አላማ ይዞ ሲነሳ የአብክመ ጤና ቢሮ የቱን ነበር የተገበረው ብዬ ላንስ፦
1. ሠራተኞችን በግልጸኝነት፣ በፍትሀዊነትና በተጠያቂነት አወዳድሮ ደልድሏልን?
አልደለደለም ምክንያቱም፦ JEG ተግባራዊ ስላልተደረግ
2. በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ የተመዘኑና ደረጃ በወጣላቸው የሥራ መደቦች ላይ ተገቢውን ሠራተኛ በተገቢው ቦታ መመደብ ተችሏል?
አልተቻለም ምክንያቱም፦
በጤና ሴክተር ከቢሮ እስከ ተቋማት በተለይ ክልል ጤና ቢሮ፣ ዞን ጤና መምሪያ፣ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ላይ ያሉ የስራ አመራር መደቦች ላይ ምንም አይነት የስራ ዝርዝር የለዉም (ሰው ስራዉን አያውቅም በደመ ነፍስ ነው የሚሰራው እየሰራም ያለው እስካሁን ድረስ) እና ምንም ተጠያቂነት የሌለው አሰራር ያለ መሆኑ ምክንያቱም እንደ ሃገር የወጣዉን የስራ ዝርዝር ተፈጻሚ ስላልሆነ ከዚህም በተጨማሪ ምንም አይነት ሂደትና የሜሪት አካሄድ ስለለለ ሁሉም በተቋማት ያሉ ሰዎች ባሉበት ቦታ ብቻ ስለተደለደሉ (እርስት እንደ ማለት ነው)?
3. በክልሉ ያሉ የጤና ስራ አመራር መደቦች የስራ ዝርዝር ተዘጋጅቷል?
አልተዘጋጀም ምክንያቱም፦ እንደ ሀገር በJEG የተጠኑት የስራ አመራር መደቦች ተግባራዊ ስላልተደረጉ

=>BPR (Business Process Reengineering) አላማውን ደሞ ስናይ የድርጅቱ ስራ ሂደቶችን በሙሉ እንደገና በመንደፍ ታላቅ እና ፈጣን ለውጥ ማምጣት ነው።
ከዚህ አንጻር ጤና ቢሮው ፈጣን ለውጥ ለማምጣት ከክልል ጀምሮ እስከ ተቋማት ያለውን በተመሳሳይ አደረጃጀት ለማስቀመጥ እየተሄደበት ያለው መንገድ ይበል የሚያሰኝ ነው።
ነገር ግን ሁሉም ሰው ባለበት ይቀጥል የሚለው አሰራር ትክክል ሊሆን አይችልም ምክንያቱም Nutrition MPH ያለው ሰው በNutrition ዙሪያ እያለ እንዴት Environmental ባለሙያ ይዞት ይቀጥል ይባላል? (ይህ ለምሳሌ ነው በጣም ብዙ ቦታ ብዙ የሙያ አቀማመጥ ችግር ስላል) ምክንያቱም ተፈላጊ ችሎታ የሚለዉን ስለማያሟላ።

ሳጠቃልል ትንሽ ጥያቄዎችን ለጤና ቢሮውና ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ላቅርብ በቅንነት አይታችሁ እንድትመልሱልኝ እፈልጋለሁ፦
1. JEG ሳይተገበር እንዴት BPR ሙሉ በሙሉ መተግበር ትችላላችሁ?
2. ድልድልን በተመለከት ሰው ያለበትን እንዳይለቅ ለምን ፈራችሁ?
(ስልጠና፣ የጊዜ ቆይታ፣ ስራዉን ያውቀዋል የሚል ምክንያት አሳማኝ ስለማይሆን) ምክንያቱም በህይወት ዘመኑ የተማረው የተሻለ መፈጸም ስለሚችል እና የተሻለ ለቦታው ቅርበት ስላለው ወይስ ቢሮ ላይ ያላችሁ ሰዎች ከቦታችሁ መንቀሳቀስ ስለምትፈሩ?
3. አሁንስ የስራ ዝርዝር በተለይ ለተቋማት (ከሙያ ዉጭ ላሉት ለተቋማት ፣ ለወረዳ፣ ለዞን ፣ለክልል ላሉ ስራ አመራር መደቦች አዘጋጅታችኋል ወይስ እንደስካሁኑ በደፈናው ነው የምትሄዱት?
4. ሰው ባለበት ይቀጥል ወይም ይመደብ የሚባል ከሆነ ከJEG እና BPR አላማ ጋርስ አይጋጭም ወይ?

"ስለዚህ እነዚህን መሰረታዊ ጥያቄዎች ይዛችሁ የክልሉ ጤና ቢሮ ከክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን JEG እንደ እዲስ በመተግበር BPR ጋር በማቀናጀት ዉጤታማነትን ከትክክለኛ ሰውና ከትክክለኛው መደብ ጋር ተፈላጊ ችሎታና ልምድን በማቀናጀት ወጥ የሆነ ከአድሎና ወገንተኝነት የራቀ አደረጃጀት ትሰራላችሁ ብለን አምናለሁ"

የጤና ባለሙያዎችስ ምን ትላላችሁ በሙያችሁም በጤና ስራ አመራር መደብ ላይም የምትሰሩ

አመሰግናለሁ
ሙሉቀን አበበ
ሰው ሀብት ልማት ባለሙያ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Medical Information posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Medical Information:

Share

Our Story

Feed Health Information