Amanuel mental specialized hospital

Amanuel mental specialized hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Amanuel mental specialized hospital, Addis Ababa ethiopia Addis ketema subcity at the vicinity of Mesalemeya, Addis Ababa.

Emmanuel mental specialized hospital is apionner one which provides mental health care and treatment for about people who are from all corners of the nation and mental health rehabilitation services since it has been established in 1938

11/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የጤና የፍቅር የአንድነት የመረዳዳትና የመተሳሰብ ይሆንላችሁ ዘንድ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል መልካም ምኞቱን ያስተላልፋል። መልካም በዓል!

09/04/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ

የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ3ኛው ሩብ ዓመት የመድሃኒትና የህክምና መሣሪያዎች ቆጠራ አካሄደ​አዲስ አበባ ፦ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) የአማኑኤል አእም...
04/04/2026

የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ3ኛው ሩብ ዓመት የመድሃኒትና የህክምና መሣሪያዎች ቆጠራ አካሄደ
​አዲስ አበባ ፦ መጋቢት 26/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) የአማኑኤል አእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የ2018 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የመድሃኒትና የህክምና መሣሪያዎች ቆጠራ አከናውኗል።
​ይህ በየሦስት ወሩ የሚካሄደው መደበኛ ቆጠራ ዋነኛ አላማ የሆስፒታሉን የንብረት አያያዝ ግልጽነት ለማረጋገጥና ለታካሚዎች የሚቀርቡ መድሃኒቶችና የህክምና ግብዓቶች ያለምንም መቆራረጥ ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ለማድረግ ያለመ ነው።
በቆጠራው ወቅት በፋርማሲና በመድሃኒት ማከማቻ ክፍል የሚገኙ መድሃኒቶችና የህክምና መሣሪያዎች በዝርዝር ተቆጥረው ከመዝገብ ጋር የማመሳከር ስራ እና የመድሃኒቶች የአገልግሎት ጊዜ በጥንቃቄ ተፈትሾ የአገልግሎት ዘመናቸው ሊያበቃ የተቃረቡ መድሃኒቶች ተለይተው አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል።እንዲሁም በቆጠራው በተገኘው መረጃ መሠረት ለቀጣይ ወራት የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን አስቀድሞ በመለየት የአቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት አቅጣጫ ተቀምጧል።
በመጨረሻም የአእምሮ ጤና አገልግሎት ልዩ ትኩረትና ያልተቋረጠ የመድሃኒት አቅርቦት የሚፈልግ በመሆኑ ወቅታዊና ቀጣይነት ያለው የቁጥጥር ስራዎች መኖር የአገልግሎት ጥራቱን ለማስጠበቅና ብክነትን ለመቀነስ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል።

የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድሃኒቶች ምንድን ናቸው?ናርኮቲክ (Narcotics) እና ሳይኮትሮፒክ (Psychotropic) መድኃኒቶች ሁለቱም በማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓታችን (አንጎል እና የነርቭ...
02/04/2026

የናርኮቲክና ሳይኮትሮፒክ መድሃኒቶች ምንድን ናቸው?
ናርኮቲክ (Narcotics) እና ሳይኮትሮፒክ (Psychotropic) መድኃኒቶች ሁለቱም በማዕከላዊ የነርቭ ሥርዓታችን (አንጎል እና የነርቭ ሴሎች) ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ቢሆኑም የየራሳቸው የሆነ የተለየ ባህሪ እና ተግባር አላቸው። እነዚህ መድኃኒቶች በጤናው ዘርፍ እጅግ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሹ መድኃኒቶች ናቸው።
1 ናርኮቲክ መድኃኒቶች (Narcotics)
​"ናርኮቲክ" የሚለው ቃል የግሪክ ሲሆን ትርጉሙም "ማደንዘዝ" ወይም "እንቅልፍ መጣል" ማለት ነው። እነዚህ መድኃኒቶች በዋነኛነት ለከባድ ሕመም ማስታገሻነት ያገለግላሉ።
•​ምንነታቸው: በአብዛኛው ከኦፒየም (O***m) ተክል የሚገኙ ወይም በቤተ-ሙከራ ውስጥ ተመሳሳይ በሆነ መንገድ የሚመረቱ (Opioids) ናቸው።
• ​ተግባራቸው: አንጎል የሕመም ስሜትን የሚቀበልበትን መንገድ በመቀየር ከፍተኛ የሆነ የሕመም ማስታገስ ሥራ ይሠራሉ።
ናርኮቲክ መድኃኒቶች (Narcotics) ለማን ይታዘዛሉ?
​ዓላማቸው በዋነኝነት የሚታዘዙት ከባድ ሕመምን (Severe Pain) ለማስታገስ በመሆኑ እነዚህ መድኃኒቶች ​ለካንሰር ሕመምተኞች፣ ከከባድ ቀዶ ጥገና በኋላ ላለ ሕመም፣ ወይም ሌሎች መለስተኛ ማስታገሻዎች ላልረዷቸው ታካሚዎች ይታዘዛሉ።
ለምሳሌ: ሞርፊን (Morphine)፣ ፔቲዲን (Pethidine)፣ ትራማዶል (Tramadol)።
ናርኮቲክ መድኃኒቶች ዋነኛ ባህሪያቸው
በጣም ኃይለኛ ናቸው። ለሱስ (Addiction) የማጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ በመሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የሕግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ።
ለምሳሌ: ሞርፊን (Morphine)፣ ኮዴን (Codeine)፣ ፔቲዲን (Pethidine) እና ትራማዶል (Tramadol)።
​2 ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች (Psychotropic Drugs)
​"ሳይኮትሮፒክ" የሚለው ቃል ማንኛውንም በአእምሮ አሠራር፣ በስሜት፣ በባህሪ እና በአስተሳሰብ ላይ ለውጥ የሚያመጣ መድኃኒት የሚገልጽ ሰፊ መጠሪያ ነው።
ዓላማቸው በአእምሮ ውስጥ ያሉ የኬሚካል መልዕክተኞችን (Neurotransmitters) በማስተካከል የአእምሮ ጤና ሁኔታንና ስሜትን ለመቆጣጠር ነው።
•​ተግባራቸው: እንደ ጭንቀት፣ ድብርት፣ እንቅልፍ ማጣት፣ መቅበዝበዝ እና ከእውነታው ዓለም ጋር መራቅ (Psychosis) ፤ለሚጥል በሽታ (Epilepsy) ያሉ ሁኔታዎችን ለማስተካከል ይረዳሉ።
ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች (Psychotropic Drugs) ባህሪያቸው
እነዚህ መድኃኒቶች የግድ ለሕመም ማስታገሻነት አይውሉም ይልቁንም የአእምሮን ጤናማ ሚዛን ለመጠበቅ ነው የሚታዘዙት
ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች (Psychotropic Drugs) ለማን ይታዘዛሉ
ለጭንቀት (Anxiety)፣ ለድብርት (Depression)፣ ለእንቅልፍ ማጣት፣ እና ለተለያዩ የአእምሮ ሕመሞች ሊታዘዙ ይችላሉ።
• ​ለምሳሌ: ዲያዜፓም (ለጭንቀት)፣ አሚትሪፕቲሊን (ለድብርት) ሊታዘዙ ይችላሉ።
​በድንገት ማቆም የሚያስከትለው ጉዳት (Withdrawal)
​እነዚህን መድኃኒቶች ያለ ሐኪም ትዕዛዝ በድንገት ማቆም ከባድ የጤና ቀውስ ሊያስከትል ይችላል
• ​ናርኮቲክስ መድሃኒቶችን በድንገት ማቆም ከፍተኛ የሰውነት መቆጥቆጥ፣ ማስመለስ፣ ላብ፣ እንቅልፍ ማጣት፣ እና ከባድ የጡንቻ ሕመም ያስከትላል።
• ​ሳይኮትሮፒክስ መድሃኒቶችን በድንገት ማቆም የሚታከሙት በሽታዎች (ለምሳሌ ድብርት ወይም ጭንቀት) በከፍተኛ ሁኔታ ተመልሰው መምጣት፣ መንቀጥቀጥ፣ ከፍተኛ መረበሽ እና አልፎ ተርፎም ራስን እስከመሳት ሊያደርሱ ይችላሉ።
እነዚህ መድኃኒቶች ሁልጊዜም መቀነስ ያለባቸው በሐኪም ክትትልና ትዕዛዝ ቀስ በቀስ መጠን እየቀነሰ መሆን አለበት።
​የአቀማመጥ ሁኔታ እና የአወጋገድ ሥርዓት
​ሁለቱም መድኃኒቶች ለሱስ የመዳረግ እና ያለአግባብ የመጠቀም (Abuse) ዕድላቸው ከፍተኛ ስለሆነ ልዩ ጥበቃ ይፈልጋሉ
ከሌሎች መድሃኒቶች ተለይተው (Quarantine ) መቀመጥ አለባቸው
​መቆለፊያ ባለው ቁምሳጥን ውስጥ መቀመጥ አለባቸው።
​ከልጆች እና መድኃኒቱ ካልታዘዘላቸው ሰዎች እጅ ራቅ ባለ ቦታ መቀመጥ ይኖርባቸዋል።
​አወጋገድ
​ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች በቆሻሻ መጣያ ውስጥ መጣል የለባቸውም። ወደ ፋርማሲ ወይም የጤና ተቋም በመመለስ በልዩ ሁኔታ እንዲቃጠሉ መደረግ አለበት።
​የሕክምና ማዘዣ (Prescription)
​እነዚህ መድኃኒቶች የሚታዘዙት በልዩና ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግበት ማዘዣ (Special Prescription Paper) ብቻ ነው።
​በመደበኛ የሕክምና ማዘዣ ወረቀት አይታዘዙም።
​ማዘዣው ላይ የሐኪሙ ስም፣ ፊርማ፣ የታካሚው ሙሉ መረጃ እና የመድኃኒቱ ትክክለኛ መጠን በግልጽ መስፈር አለበት።
​ከሌሎች መድኃኒቶች ጋር ያላቸው መስተጋብር (Drug Interaction)
​እነዚህ መድኃኒቶች ከሌሎች ነገሮች ጋር ሲወሰዱ አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ ሁለቱም መድኃኒቶች ከአልኮል ጋር ከተወሰዱ የልብ ትርታንና አተነፋፈስን በማዘግየት ለሞት ሊዳርጉ ይችላሉ።
​እርስ በእርስ: ናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶች በአንድ ላይ ሲወሰዱ ከፍተኛ የሆነ ራስን መሳትና የመተንፈስ ችግር ያመጣሉ።
​ከዕፅዋት ውጤቶች ጋር: እንደ "St. John's Wort" ያሉ የባህል መድኃኒቶች የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶችን ሥራ ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ።
ማሳሰቢያ፤ ይህ ፅሁፍ ለማስተማሪያነት ብቻ የቀረበ ነው

01/04/2026
በግቢ ደህንነትና በህሙማን አያያዝ ዙሪያ ለጥበቃ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ​አዲስ አበባ ፦ መጋቢት 23/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል)  በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክ...
01/04/2026

በግቢ ደህንነትና በህሙማን አያያዝ ዙሪያ ለጥበቃ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
​አዲስ አበባ ፦ መጋቢት 23/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) በአማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ጥራትና ኢኖቬሽን ዳይሬክቶሬት የሆስፒታሉን የደህንነት ጥበቃ ስርዓት ይበልጥ ለማጠናከርና ሰብአዊነት የተሞላበት የህሙማን አያያዝ እንዲሰፍን ለማስቻል ለጥበቃ (Security) ባለሙያዎች ከ22 -23/7/2018 ዓ.ም ለ2ቀናት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
​ የስልጠናው ዋና አላማ የጥበቃ ባለሙያዎች የሆስፒታሉ የመጀመሪያው የክብር በር መገለጫዎች በመሆናቸው ከደህንነት ስራቸው ጎን ለጎን ከህሙማንና ከደንበኞች ጋር ያላቸው ግንኙነት የሰለጠነና ስነ-ምግባርን የተላበሰ እንዲሆን ያለመ ነው። የስልጠናው ዋነኛ ትኩረት ማንኛውንም የደህንነት ስጋት አስቀድሞ መከላከልና የሆስፒታሉን ንብረት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ በሚቻልባቸው ስልቶች ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ህሙማን በስነ-ልቦናም ሆነ በአካል ድጋፍ የሚሹ በመሆናቸው የጥበቃ ባለሙያዎች በደግነትና በትዕግስት ሊያስተናግዷቸው እንደሚገባ ያትታል።
በዚህም ከአገልግሎት ፈላጊዎች ጋር የሚደረግ የሰላማዊ ተግባቦት አስፈላጊነትና በስራ ወቅት ሊታዩ የሚገባቸው የባለሙያ ስነ-ምግባሮች ላይ ሰፊ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል።

9851 የአእምሮ ጤና ለሁሉም!"የአእምሮ ጤናን በተመለከተ ሆስፒታሉ የሚሰጣቸውን የህክምና እና የማማከር አገልግሎቶች ወደ ደንበኞቹ ለማድረስ አዲሱን 9851 አጭር የስልክ መልዕክት መቀበያ  ...
28/03/2026

9851 የአእምሮ ጤና ለሁሉም!"
የአእምሮ ጤናን በተመለከተ ሆስፒታሉ የሚሰጣቸውን የህክምና እና የማማከር አገልግሎቶች ወደ ደንበኞቹ ለማድረስ አዲሱን 9851 አጭር የስልክ መልዕክት መቀበያ ቁጥር ስራ ላይ አውለናል። በመሆኑም ስለ አእምሮ ጤና ህክምና፣ የምክር አገልግሎትና ተያያዥ ጉዳዮች መረጃ ለማግኘት በዚሁ ቁጥር በኩል ደውለው ያድርሱን። እኛ ሁልጊዜ ለናንተ ዝግጁ ነን!

የዕለቱ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት
27/03/2026

የዕለቱ የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ መልዕክት

የአእምሮ ጤና አጠባበቅየአእምሮ ጤና ልክ እንደ አካላዊ ጤንነት ሁሉ የእለት ከእለት እንክብካቤ እና ትኩረት የሚሻ የሕይወታችን ክፍል ነው። የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅና ለማጎልበት የሚረዱ ዋና ...
24/03/2026

የአእምሮ ጤና አጠባበቅ
የአእምሮ ጤና ልክ እንደ አካላዊ ጤንነት ሁሉ የእለት ከእለት እንክብካቤ እና ትኩረት የሚሻ የሕይወታችን ክፍል ነው። የአእምሮ ጤናን ለመጠበቅና ለማጎልበት የሚረዱ ዋና ዋና ዘዴዎች
​1. የግል የአኗኗር ዘይቤ (Self-Care)
​የአካል ጤንነት ለአእምሮ ጤና መሰረት ነው። በመሆኑም አእምሮዎ በተገቢው ሁኔታ እንዲሠራ የሚከተሉትን መተግበር ተገቢ ነው
በቂ እንቅልፍ ማግኘት፦ በቀን ውስጥ ከ 7-8 ሰዓት መተኛት አእምሮ እራሱን እንዲያድስ እና ስሜትን የመቆጣጠር አቅሙ እንዲጨምር ይረዳዋል።
• ​አካላዊ እንቅስቃሴ፦ ስፖርት በሚሰሩበት ጊዜ አእምሮ ኢንዶርፊን (Endorphins) የሚባሉ የደስታ ኬሚካሎችን ያመነጫል። ይህ ደግሞ ጭንቀትንና ድብርትን ይቀንሳል።
• ​የተመጣጠነ ምግብ፦ እንደ አትክልት፣ ፍራፍሬ እና ኦሜጋ-3 ያላቸው ምግቦች ለአእምሮ ንቃትና ለተረጋጋ ስሜት ወሳኝ ናቸው።
• ​ከሱስ መራቅ፦ አልኮል፣ ሲጋራ እና ሌሎች አነቃቂዎች ለጊዜው ደስታና ዕረፍት የሰጡ ቢመስልም በረጅም ጊዜ ግን የአእምሮን ኬሚካላዊ ሚዛን ያዛባሉ።
​2. የስነ-ልቦና ጥንካሬን ማዳበር
​አእምሮአዊ ጫናዎችን (Stress) ለመቋቋም የሚከተሉትን ልምዶች ማዳበር ይገባል፦
• ​ሀሳብን መግለጽ፦ የሚሰማዎትን ስሜት ለታመነ ሰው ማካፈል ወይም በወረቀት ላይ መጻፍ የውስጥ ውጥረትን ይቀንሳል።
• ​ማሰላሰል (Meditation)፦ በአሁኑ ሰዓት ላይ ትኩረት ማድረግ (Mindfulness) እና ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ አእምሮ ከልክ በላይ እንዳይጨነቅ ያደርጋል።
• ​የጊዜ አጠቃቀም፦ ሥራዎችን በቅደም ተከተል ማከናወንና ከልክ በላይ ራስን አለማድከም። ከአቅም በላይ ለሆነ ነገር "አይሆንም" ማለት መልመድም ለአእምሮ ሰላም አስፈላጊ ነው።
​3. ማህበራዊ ትስስር እና ድጋፍ
​ሰው ማህበራዊ ፍጡር በመሆኑ ከሌሎች ጋር ያለው ግንኙነት በአእምሮው ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ አለው
• ​ከቤተሰብና ጓደኞች ጋር መገናኘት፦ ብቸኝነት ለአእምሮ ጤና ጠንቅ ነው። ከሰዎች ጋር መሳቅና መጫወት የመጽናናት ስሜት ይሰጣል።
• ​እርዳታ መጠየቅ፦ ከአቅም በላይ የሆነ የጭንቀት፣ የሐዘን ወይም የባህሪ ለውጥ ሲታይ ወደ ባለሙያ (ሳይኮሎጂስት ወይም ሳይኪያትሪስት) መሄድ የጥንካሬ እንጂ የድክመት ምልክት አይደለም።
​የአእምሮ ጤና ችግር የፈጣሪ ቁጣ ወይም ደካማነት ሳይሆን እንደ ማንኛውም የሰውነት ሕመም በሕክምናና በማማከር ሊድን የሚችል ህመም ነው።

የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ የዕለቱ  መልዕክት
23/03/2026

የስነምግባርና ፀረ-ሙስና ስራ አስፈፃሚ የዕለቱ መልዕክት

አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ከታካሚዎች ጋር በልዩ ሁኔታ አከበረ​አዲስ አበባ ፦መጋቢት 11/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) አማኑኤል የአእምሮ ስፔ...
20/03/2026

አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዒድ አል-ፈጥር በዓልን ከታካሚዎች ጋር በልዩ ሁኔታ አከበረ
​አዲስ አበባ ፦መጋቢት 11/2018 ዓ.ም (አማ/አእ/ስፔ/ሆ/ል) አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 1447ኛውን የዒድ አል-ፈጥር በዓል "መካፈል ደስታ ነው" በሚል መሪ ቃል በሆስፒታሉ ውስጥ ከሚገኙ ታካሚዎች ጋር በጋራ በማክበር አሳልፏል።
​በበዓሉ አከባበር ላይ የሆስፒታሉ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሕክምና ባለሙያዎችና ታካሚዎች የተገኙ ሲሆን የበዓሉ ዝግጅት ዋና ዓላማ ታካሚዎች ከህብረተሰቡ የተገለሉ እንዳልሆኑ እንዲሰማቸውና በስነ-ልቦናዊ ሁኔታ እንዲበረታቱ ለማድረግ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
​በዕለቱም ለታካሚዎች የበዓል ምግብና መጠጥ በማቅረብ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ተደርጓል።
የተሃድሶና ሳይኮሶሻል ህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አያሌው አባተ በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የዒድ አል-ፈጥር በዓል መገለጫ የሆኑትን መረዳዳትና መተሳሰብን በተግባር በማሳየት ታካሚዎች ከቤተሰቦቻቸው ርቀውም ቢሆን የበዓሉ ድባብ እንዲሰማቸው ለማድረግ ነው ብለዋል። አክለውም ታካሚዎች የተሟላ የሕክምናና የማህበራዊ ድጋፍ እንዲያገኙ የሆስፒታሉ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

​ይህ መሰሉ የበዓል አከባበር በአእምሮ ሕክምና ሂደት ውስጥ ታካሚዎች የማህበራዊ ትስስር እንዲኖራቸው በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ይታመናል።
​ዒድ ሙባረክ!

Address

Addis Ababa Ethiopia Addis Ketema Subcity At The Vicinity Of Mesalemeya
Addis Ababa

Telephone

251944199174

Website

http://WWW.amsh.gov.et/

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amanuel mental specialized hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share