Ethiopian Public Health Association (EPHA)

Ethiopian Public Health Association (EPHA) EPHA is an association of public health professionals of varying categories and levels of training.

to promotes better health services to the public and high professional standards through advocacy, professional competence, relevant policies, and effective networking. EPHA is committed to improve the health and living status of the people of Ethiopia through the dedicated and active involvement of the organization and its members and through collaboration with stakeholders. EPHA members are distributed all over the country occupying positions at different levels of health care and management from woreda (district) health office and health facilities to the level of a minister. EPHA members are also in private, government and non-government organizations as are its Executive Board members EPHA is among the strongest professional associations in Ethiopia with a current membership of more than 8600. EPHA has its head quarter in Addis Ababa, Ethiopia, and chapters in different regions of the country. The Association is working closely with its partners and collaborators to facilitate and accelerate activities on the country’s priority public health issues and has over 30 years of experience and success in implementing national as well as continental projects.. EPHA has good working relationship with governmental and non-governmental organizations, and universities within the country and abroad.

"ዘላቂ ኢንቨስትመንት እና ኢኖቬሽን ለጠንካራ የጤና ስርአት” በሚል መሪ ቃል በጅማ ከተማ በተካሄደው 27ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በልዩ ልዩ መስክ የተሸለሙ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማ...
27/10/2025

"ዘላቂ ኢንቨስትመንት እና ኢኖቬሽን ለጠንካራ የጤና ስርአት” በሚል መሪ ቃል በጅማ ከተማ በተካሄደው 27ኛው የጤና ዘርፍ ዓመታዊ ጉባዔ በልዩ ልዩ መስክ የተሸለሙ የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር አባላትን እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን!

ዶ/ር አህመድ መሐመድ
በህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
****
አቶ ሰለሞን ከበደ
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
****
ፕ/ር ቢኒያም ጫቅሉ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
****
ዶ/ር አበበ መገርሶ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
****
አቶ ሰይድ የሱፍ
በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት ተሸላሚ
****
ዶ/ር ሰለሞን አሊ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ
****
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር!

27/10/2025

ዶ/ር አህመድ መሐመድ
በህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት

**************

በሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሐረር ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ከተማ ቤተልሄም ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወንጂ ቁጥር 2፣ በአዳማ አፄ ገልውዲዎስ እና በሐረር ተከታትለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ እና የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊቲ ትምህታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ለ35 አመታት በዋርዴር ጤና ጣቢያ፣ በቀብሪ ደሀር ሆስፒታል፣ በጎዴ ሆስፒታል በባለሙያነትና በሃላፊነት እንዲሁም በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ ቁጥጥር እና የመከላከል ክፍል እንዲሁም በካራማራ ሆስፒታል በሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስትነት ሰርተዋል፡፡ አሁን በጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ ሼኽ ሀሰን የቤሬ ቲቺንግ ሆስፒታል በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር አህመድ መሐመድ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/10/2025

አቶ ሰለሞን ከበደ
የህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ

************

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሃረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ግራዋ ከተማ ተወለዱ፡፡ ግራዋ ከተማ እስከ 8ኛ ክፍል ተምረዋል፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሃረር ከተማ መድሃኒዓለም ት/ቤት አጠናቀቁ፡፡

ከአዲስ አበባ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጤና ረዳትነት፤ ከአሰላ ነርሲግ ትምህርት ቤት በክሊኒካል ነርስ በዲፕሎማ እንዲሁም ከአማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሳይካትሪ ነርስ በዲፕሎማ የተመረቁ ሲሆን በሃሮማያ ዩንቨርስቲ ደግሞ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በነርሲንግ አግኝተዋል፡፡

በቀብሪ ደሃር ደጃዝማች ገብረማርያም ሆስፒታል የጤና ረዳት በመሆን ነው ስራ የጀመሩት። በወቅቱ በነበረው የሶማልያ ጦርነት ሳቢያ ተይዘው ወደ ሶማልያ ሞቃድሾ ተወስደው ለ11 ዓመት ታስረዋል፤ እዛው እስር ቤት በነበሩበት ወቅትም በሙያቸው ከ3 እስከ 4 ሺ ለሚሆኑ እስረኞች በነፃ ያገለገሉ ሲሆን ለዚህም እዉቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ከ11 ዓመት በኃላ ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በድሬዳዋ ዋሂል ጤና ጣብያ ለ1 ዓመት ከዚያም በደወሌ ከተማ ጤና ጣቢያ ተመድበው ለ4 አመት ሠርተዋል። በመቀጠልም በድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ለ13 ዓመታት የስነ አዕምሮ ህክምናን ጨምሮ በተለያ ዘርፎች ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን ከ2002 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም በጡረታ እስከተገለሉበት ውቅት በሳቢያን ሆስፒታል ባላቸው ሞያ ህዝባቸውን አገልግለዋል፡፡ ከመደበኛ ስራቸው ጎን ለጎን በሚሺነሪ ኦፍ ቻሪቲ የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ለ7 ዓመት በትጋት አገልግለዋል።

አቶ ሰለሞን ከበደ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ የሙያ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/10/2025

ፕ/ር ቢኒያም ጫቅሉ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት ተሸላሚ

************

በወጣትነታቸው ሙሉ ፕሮፌሰር ለመሆን በቅተዋል። በአማራ ክልል ማእከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በታች አርማጭሆ፣ 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጎንደር ከተማ በፋሲለደስ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡

የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፐብሊክ ሄልዝ ኢንፎርማቲክስ እንዲሁም ተጨማሪ ማስተርስ ዲግሪያቸው በስፔን፤ ፖርቹጋል እና ጀርመን ሀገሮች ተዘዋውረው ተምረዋል። በጀርመን ሀገር ሙኒስተር ዩኒቨርሲቲ የዶከትሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከዚያም የፖስት ዶክትሬት ትምህርታቸውን ወደ ሰሜን አሜሪካ በማቅናት በብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀዋል፡፡

ከ10 ዓመታት የአውሮፓና የሰሜን አሜሪካ ቆይታ በኋላ “በወጣትነቴ ሀገሬን ማገልገል አለብኝ” ብለው ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ ጎንደር ዩኒቨርስቲን ከመምህርነት እስከ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ ሲሆን ከ200 በላይ የምርምር ውጤቶችን በተለያዩ ጆርናሎች አሳትመዋል፡፡

ወጣቱ ፕሮፌሰር የኢትዮጵያን የጤና ስርዓት ለማሻሻልና የinformation revolution አጀንዳ ለማሳከት CBMP የተባለ የአቅም ግንባታ ፕሮግራም በ2010 ዓም በመቅረፅ 6 ዩኒቨርስቲዎች አንድ ላይ በማቀናጀት በየአካባቢያቸው የሚገኙ 36 ወረዳዎችን በመደገፍ ስራ እንዲጀምሩ አድርገዋል።

የሀገራችንን የጤና ዲጂታላይዜሽን፤ የጤና መረጃ ጥራት ማሻሻያ መንገዶች፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ለአጠቃቀም ቀላል ማድረጊያ መንገዶችን እና አጠቃላይ ለሀገራዊ የጤና ፓሊሲና ስትራቴጂ የሚጠቅሙ ስራዎችን አበርክተዋል።

ባላቸው ልምድም ከአፍሪካ ሲዲሲ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከGates foundation, ከዓለም ባንክ እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን የጤናውን ዘርፍ ዲጂታላይዜሽን ለማሳደግ እየሰሩ ይገኛሉ።

ፕ/ር ቢኒያም ጫቅሉ፤ በሙያ መስክ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/10/2025

ዶ/ር አበበ መገርሳ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት

************

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን ዝዋይ ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በምስራቅ ሸዋ ዞን ዝዋይ ከተማ ተምረዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በማህበረሰብ ጤና ከዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የሁለተኛ ድግሪያቸውንና የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በህብረተሰብ ጤና አግኝተዋል፡፡

በባሌ ዞን ጤና መምሪያ በባለሙያነት፣ በምዕራብ አርሲ ዞን ጤና መምሪያ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ አስተባባሪና የክፍል ኃላፊነት፣ በኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የጥናትና ምርምር አስተባባሪ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን አሁንም በአዳማ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በረዳት ፕሮቮሰትነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
በስራ ቆይታቸው የእናቶች ጤና አገልግሎት እንዲሻሻልና የድንገተኛና ወረርሽኝ በሽታዎችን መቆጣጠርንና ምላሽ አቅምን በማጠናከር በብቃት አመራር ሰጥተዋል፡፡

የኤች.አይ.ቪ በሽታን በመከላከልና በመቆጣጠር ሂደት ቅንጂታዊ አሰራርን በማጠናከር የምክክር፣ የምርመራና የህክምና አገልግሎትን እንዲሻሻል ሰርተዋል፡፡

በአኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የጥናትና ምርምር አሰራሮችና የጤና ሳይንስ ተቋማትን በማጠናከር ብቃት ያላቸውን የጤና ባለሙያዎችን በማፍራት አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡ ከ22 በላይ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን በማሳተምም የተለያዩ ሽልማቶችን እና እውቅናን አግኝተዋል፡፡

ዶ/ር አበበ መገርሳ፤ በሙያ መስክ የላቀ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/10/2025

አቶ ሰይድ የሱፍ
በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት

***********

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወረባቦ ወረዳ ሀራ በምትባል የገጠር ቀበሌ ነው የተወለዱት፡፡ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ ትምርታቸውን በአርድቦ፣ በቢስቲማና በሀይቅ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተከታትለዋል፡፡ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን በጎንደር ዩኒቨርስቲ በህብረተሰብ ጤና የተመረቁ ሲሆን ሁለተኛ ድግሪያቸውን ደግሞ ከጅማ ዩኒቨርስቲ በጤና አገልግሎት አስተዳደር አግኝተዋልል፡፡

በጠቅላላው ለሃያ አንድ ዓመታት በጤናው ዘርፍ በባለሙያነትና በአመራርነት አገልግለዋል፡፡ ለአብነትም የወረባቦ ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ወረዳዋ በተደጋጋሚ ከዞኑ ካሉ ወረዳዎች በጤናው ዘርፍ 1ኛ እንዲወጣና የተሞክሮ ማዕከል እንዲሆን አበክረው ሰርተዋል፡፡

የቦሩ ሜዳ ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ፣ የደሴ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ፣ የደሴ ሪፈራል ሆስፒታል ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን አሁንም የደሴ ከተማ አስተዳደር በም/ከንቲባ ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የጤና መምሪያ ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

በቆይታቸውም የጤና ተቋማትን የመሰረተ ልማት ችግሮችን በመቅረፍ፣ ማህበረሰቡን በማስተባበር በከፍተኛ ወጪ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርመራና የህክምና ማዕከላትን፣ ጤና ጣቢያዎችንና ጤና ኬላዎችን አስገንብተዋል እንዲሁም የከተማውን ማህበረሰቡን በማስተባር በ65 ሚሊዮን ብር ህንጻ አስገብተው አምስት የከተማ የፋርማሲዎችና አንድ አቅራቢ ድርጅት እንዲቋቋም ሚና ተጫውተዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ጤና መምሪያ እና ሌሎች የማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት በ2017 በጀት ዓመት በአማራ ክልል ካሉ ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር ተወዳድረው በሁሉም 1ኛ በመሆን ተሸላሚ እንዲሆኑ የማስተባበር ሚናቸውን ተወጥተዋል፡፡

አቶ ሰይድ የሱፍ፤ በጤናው ዘርፍ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች የላቀ አገልግሎት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዎ ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27/10/2025

ዶ/ር ሰለሞን አሊ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት

***********

የተወለዱት በደሴ ከተማ ነው፡፡ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ በወርቅ ሜዳልያ የተመረቁ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማይክሮ ባዮሎጂ እንዲሁም ፒ.ኤች.ዲያቸውን በጀርመን ሀገር አግኝተዋል።

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተባባሪ ፕሮፌሰርነትን ጨምሮ በተለያዩ የትምህርት እና የአመራር ቦታዎች አገልግለዋል። በኢትዮጵያ እና በሌሎችም ሀገራት በህክምና ጥናትና ምርምር የላቀ አስተዋፅዖ ያደረጉ የማይክሮባዮሎጂ ባለሙያ፣ ተመራማሪ እና አስተማሪ ናቸው።

በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ በሆኑ ጆርናሎች ከ54 በላይ ሳይንሳዊ አርቲክሎችን ያሳተሙ ሲሆን የሚሊኒየም ጆርናል ኦፍ ሄልዝ መስራች እና ዋና አዘጋጅ ናቸው። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስታልን የመጀመሪያውን ሞለኪውላር ምርምር እና ልማት ላቦራቶሪ፣ ዘመናዊ የባዮ ባንክ ስርዓት፣ በጀርመን እና ህንድ ከሚገኙ ተቋማት ጋር በሆስፒታል የሚመጡ ኢንፌክሽኖችን እና የአንቲባዮቲክ መድኃኒቶችን ለመቋቋም የሚያስችል የትብብር ፕሮግራሞችን ለማቋቋም አግዘዋል።

ዶ/ር ሰለሞን አሊ፤ በጤና ሙያ መስክ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ በማድረግ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

27ኛው የጤናው ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ የ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የጤና ዘርፍ እቅድ ማስፈጸሚያ የጋራ ስምምነት  ሠነድ በመፈራረምና ቀጣይ አቅጣጫን በማስቀመጥ ተጠናቋል።____________የእ...
26/10/2025

27ኛው የጤናው ዘርፍ አመታዊ ጉባኤ የ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የጤና ዘርፍ እቅድ ማስፈጸሚያ የጋራ ስምምነት ሠነድ በመፈራረምና ቀጣይ አቅጣጫን በማስቀመጥ ተጠናቋል።
____________

የእቅድ ማስፈጸሚያ የጋራ ስምምነት ሰነዱን የተፈራረሙት የጤና ሚኒስትር የተጠሪ ተቋማት እንዲሁም የክልልና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎች ሲሆኑ በመድረኩም አዲሱ የጤና ፖሊሲ አስተዋዉቀዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ ውይይት ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከአጀንዳ ወደ ትግበራ የገባንበት ጊዜ ነው ያሉ ሲሆን የተሻሉ አፈጻጸሞችን ለማስቀጠል ክፍተቶችን በግብአትነት ለመወሰድ ያስቻለን ውጤታማ ጉባኤ ነበር በማለት ስራዎቻችን በተከታታይ በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል።

ዶክተር መቅደስ የጤና አኢንፈስትመንትና ፋይናንስ ማሳደግ፣ የመጀመሪያ ጤና ክብካቤ ማሻሻል እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስምረውበታል።

የጤና ባለሞያዎች የደሞዝ ጥያቄና የጤና ኢንሹራንስ ምላሽ የተሰጠ እንደሆነ ያነሱት ሚኒስትሯ የባለሞያዎች ብቃት ምዘና ስርአት መዘርጋትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅም በተሟላ መልኩ በአሰራር ለመመለስ፣ በየደረጃዉ ካለዉ አካላት ጋር በመሆን በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል።

በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ 27 ኛ ዉ የጤናው ዘርፍ የምክክር ጉባኤ ከ 1000 በላይ ተሳታፊዎች በአካል እንዲሁም ከ100 ሺህ በላይ በጤና ተቋማት ደረጃ በተመቻቸዉ በየነ መረብና ጎንዮሽ መድረክ ላይ ተሳትፈዉበታል።

The Ethiopian Public Health Association (EPHA)  would like to extend its warmest congratulations to Professor Afework Mu...
24/10/2025

The Ethiopian Public Health Association (EPHA) would like to extend its warmest congratulations to Professor Afework Mulugeta Executive Board member of EPHA for being awarded the Lifetime Achievement Award at the 27th Annual Review Meeting of Ethiopian Ministry of Health held in Jimma, Oromia Region.

Congratulations!

24/10/2025

ፕሮፌሰር አፈወርቅ ሙሉጌታ
በሙያ መስክ የላቀ የሙያ አገልግሎት

***********

በትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አክሱም ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ የገጠር ቀበሌ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በዳዕሮ ሓፋሽ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአክሱም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፤ የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን ደግሞ በጌንት ዩኒቨርስቲ ቤልጂየም እንዲሁም የፒ.ኤች.ዲ ትምህርታቸውን በኦክላሆማ ስቴት ዩኒቨርስቲ አሜሪካ ተከታትለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ጤናና ስነምግብ ምርምር ኢንስቲትዩት፣ በትግራይ ጤና ቢሮና በመቐለ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ከ30 ዓመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን በኑትሪሽን ድህረ ምረቃ ስርዓተ ትምህርቶችን በመቅረፅ፣ ከ190 በላይ የምርምር ፅሁፎችን በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተም፣ የተለያዩ የምርምርና የማማከር አገልግሎቶች በመስጠት፣ በምግብና ኑትርሽን ፖሊሲና ስትራተጂ ቀረፃ ላይ በመሳተፍና በማስተባበር እንዲሁም በተለያዩ የጤና ተቋማት በቦርድ አባልነት በማገልገል ጉልህ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ በመቐለ ዩኒቨርስቲ በኑትሪሽን ዲፓርትመንት ፕሮፌሰርና ተመራማሪ ፣ በህብረተሰብ ጤና ትምህርት የPHD ፕሮግራም ኣስተባባሪ እና የEast African Journal of Health Sciences ቺፍ ኤዲተር ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር አፈወርቅ ሙሉጌታ፣ በሙያ መስክ ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል፡፡

Website: moh.gov.et
Facebook: facebook.com/EthiopiaFMoH
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

20/10/2025

Call for Membership Registration

The Ethiopian Public Health Association (EPHA) is a not-for-profit, voluntary, and multidisciplinary association of professionals from diverse sectors.
Established in 1989, EPHA has been promoting better public health services and upholding professional standards in Ethiopia for over 36 years. Through advocacy, active engagement, and networking, EPHA continues to support the advancement of public health in the country. EPHA collaborates with both local and international partners to address Ethiopia’s top public health priorities.

We are pleased to invite you to become a member of EPHA a dedicated Association to advancing public health through research, policy engagement, capacity building, and professional networking.

Types of Membership (Individual and Institutional)
Regular Membership – for health professionals
Associate Membership – for non-health professionals
Honorary Membership – for individuals who have made outstanding contributions to public health or the community and
Lifetime Membership

Note: Anyone holding at least a first degree is eligible to become a member of the association.

How to Register
Submit a membership request via email to: ephamembers1@gmail.com.
Fill out the Membership Registration Form (can be emailed upon request)
Pay the membership fee using the Commercial Bank of Ethiopia (CBE):
Account Name: EPHA
Account Number: 1000000992357

Send the following documents via email:

* Completed registration form
* Copy of your recent academic credentials
* Scanned bank payment slip and
* A soft copy of 3x4 photograph

Membership Fees
Ethiopian Regular/Associate Member 300 ETB annually
Ethiopian Lifetime Member 3,000 ETB (one-time)
Foreign Regular/Associate Member 50 USD annually
Local Institutional Membership 5,000 ETB annually
International Institutional Membership 300 USD annually

Why Join EPHA?
You will benefit from:
- Opportunities to network with Ethiopia’s top public health professionals.
- Participation in national and international scientific conferences and workshops.
- Access to the latest research, policy updates, and public health publications.
- Opportunities to contribute to thematic working groups and health policy dialogues.
- Regular updates on training, scholarships, job opportunities, and collaborative projects.

For More Information
📞 Call us at: +251 11 416 6083 / 41
Email: ephamembers1@gmail.com

Join EPHA today and be part of Ethiopia’s public health transformation!

ማስታወቂያ
17/10/2025

ማስታወቂያ

Address

Ethiopian Public Health Association, 2QMG+PFX, Addis Ababa Via Queen Elizabeth II St. , Ethiopian Public Health Association, For The Best Route In Current Traffic Visit Https://maps. App. Goo. Gl/bwQb
Addis Ababa
7117

Opening Hours

Monday 02:30 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251114166083

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Public Health Association (EPHA) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Public Health Association (EPHA):

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram