31/12/2025
የፓራታይሮይድ ካንሰር
የፓራታይሮይድ ካንሰር እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኝ የኤንዶክራይን ካንሰር አይነት ሲሆን፣ ከመጀመሪያ ደረጃ የፓራታይሮይድ በሽታ (primary hyperparathyroidism) መካከል ከ1% በታች ይሆናል። ይህ ካንሰር ከፓራታይሮይድ ግላንዶች ይመነጫል፤ እነዚህም በአካል ውስጥ የካልሲየም መጠንን በፓራታይሮይድ ሆርሞን (PTH) በመመራት የሚቆጣጠሩ አነስተኛ የኤንዶክራይን አካላት ናቸው።
የፓራታይሮይድ ካንሰር ብዙ ጊዜ በራሱ እብጠት ሳይሆን በሚያስከትለው ከባድ ፓራታይሮይድ ቅመም መብዛት ይገለጣል። ታካሚዎች እጅግ ከፍ ያለ የደም ካልሲየም እና PTH መጠን ሊኖራቸው ይችላል፣ ይህም የአጥንት ህመም፣ ስብራት፣ የኩላሊት ጠጠር፣ የጡንቻ ድካም፣ የአእምሮ ለውጦች እና የአንጀት ችግር እንዲታዩ ያደርጋል። ከተለመዱ የፓራታይሮይድ እብጠቶች በተለየ፣ የፓራታይሮይድ ካንሰር በአንገት ላይ የሚታይ እብጠት፣ የድምፅ ነርቭ (recurrent laryngeal nerve) መጎዳት ሊታይበት ይችላል።
ምርመራው አስቸጋሪ ሲሆን፣ ከቀዶ ጥገና በፊት የፓራታይሮይድ ካንሰርን መለየት አስቸጋሪ ነው። የምስል ምርመራዎች እብጠቱን ለመፈለግ ይረዳሉ፣ ነገር ግን ካንሰር መሆኑን መለየት ብቻቸውን አይችሉም። የመጨረሻ ምርመራ ብዙውን ጊዜ ከቀዶ ጥገና በኋላ በፓቶሎጂ ላይ ይመሰረታል።
ዋና የሕክምና መንገድ ቀዶ ጥገና ነው። እብጠቱን ከተጎዳው ፓራታይሮይድ ግላንድ እና ከአጎራባች ክፍሎች ጋር በአንድነት (en bloc resection) ማስወገድ ለፈውስ ከፍተኛ እድል ይሰጣል። ከሌሎች ብዙ ካንሰሮች በተለየ፣ የፓራታይሮይድ ካንሰር ለኬሞቴራፒ እና ራዲዮቴራፒ ዝቅተኛ ምላሽ ይሰጣል፤ ስለዚህ ቀድሞ መለየት እና ሙሉ ቀዶ ጥገና እጅግ አስፈላጊ ናቸው።
በቅርቡ ይህን እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኝ በሽታ የፓራታይሮይድ ቀዶ ሕክምና በተደረገላት ሴት ታካሚ ላይ ሰሞኑን ተገኝቷል፡፡ ዶር ይሰሀሐቅ እና ባልደረቦቻቸው ባደረጉላቸው ቀዶ ሕክምና ታካሚዋ በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ይገኛሉ፡፡
ምንም እንኳን እጅግ አልፎ አልፎ ቢሆንም፣ የፓራታይሮይድ ካንሰር በጊዜው ካልታወቀ ወይም በተገቢ መንገድ ካልታከመ ከፍተኛ ጉዳት ሊያመጣ ይችላል።
ስለዚህ፣ በሕክምና ባለሙያዎች እና ለዜጎች በህመሙ ዙሪያ ግንዛቤ ማሳደግ አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ቀድሞ ምርመራ እና ተገቢ የቀዶ ሕክምና ና በዚህ እጅግ አልፎ አልፎ የሚገኝ ነገር ግን ከባድ በሽታ ውጤትን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሻሽል ይችላል።
Parathyroid Carcinoma: A Rare but Important Diagnosis
Parathyroid carcinoma is an exceptionally rare endocrine malignancy, accounting for less than 1% of all cases of primary hyperparathyroidism and for less than 0.005% of all malignancies worldwide. It arises from the parathyroid glands, which are small endocrine organs responsible for regulating calcium homeostasis through the secretion of parathyroid hormone (PTH).
Clinically, parathyroid cancer most often presents not because of the tumor itself, but due to severe hyperparathyroidism. Patients may develop markedly elevated serum calcium and PTH levels, leading to symptoms such as bone pain, fractures, kidney stones, muscle weakness, neurocognitive changes, and gastrointestinal complaints. Unlike benign parathyroid adenomas, parathyroid carcinoma may present with a palpable neck mass, recurrent laryngeal nerve involvement, or persistent disease after surgery.
Diagnosis is challenging and is rarely made preoperatively. Imaging studies help localize the lesion but cannot reliably distinguish carcinoma from benign disease. Definitive diagnosis is usually established postoperatively based on histopathological features such as capsular and vascular invasion, local tissue infiltration, or metastasis.
Surgical excision remains the cornerstone of treatment. En bloc resection of the tumor with the involved parathyroid gland and adjacent tissues offers the best chance for cure. Unlike many other cancers, parathyroid carcinoma responds poorly to chemotherapy and radiotherapy, making early recognition and complete surgical management critical.
We recently encountered this rare entity in a woman who underwent parathyroidectomy, highlighting the importance of maintaining a high index of suspicion in patients with severe or atypical hyperparathyroidism. Although uncommon, parathyroid carcinoma carries significant morbidity if unrecognized or inadequately treated.
Raising awareness among clinicians and the wider community is essential, as early diagnosis and appropriate surgical management can significantly improve outcomes in this rare but serious disease.