Al-Afdel Medium Clinic And Health Care Councling

Al-Afdel Medium Clinic And Health Care Councling አል-አፍደል መካከለኛ ክሊኒክ እና የማማከር አገልግሎት

19/12/2025

✍️የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ምንነትና ሕክምናው …

የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ምንነት፣ መንስዔው እና አጋላጭ ምክንያቶቹን በተመለከተ በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የሕጻናት ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር አበበ የኔዋ (ረ/ፕ) ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል።

በዚሁ ወቅትም ሕጻናት ከተወለዱ እስከ 28 ቀናት ባለው ጊዜ በደማቸው ውስጥ ባክቴሪያ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ሲዛመት የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ይባላል ብለዋል።

✍️ ለመሆኑ የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን መንስዔ ምንድን ነው?

• የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን የሚመጣው በአብዛኛው በባክቴሪያዎች መሆኑን ገልጸው፤ ከእነዚህ ባክቴሪያዎች መካከልም በዋናነት Escherichia coli, Group B streptococcus እና Listeria monocytogenes የተሰኙት እንደሚገኙበት ለማሳያነት ጠቅሰዋል።

✍️ ለጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን አጋላጭ የሆኑ ምክንያቶች ይታወቃሉ?

• የእንሽርት ውኃ ከምጥ 18 ሠዓት እና ከዛ በላይ ቀድሞ መፍሰስ (prolonged premature rupture of membrane)፤

• የመውለጃ ጊዜያቸው በተቃረበበት ወቅት የሚከሰት የእናቶች ኢንፌክሽን (chorioamnionitis፣ Urinary tract infection)፤

• የተራዘመ ምጥ (prolonged labor)፤

• በቂ የእርግዝና ክትትል አለመኖርና ከጤና ተቋም ውጭ (በቤታቸው) መውለድ ወ.ዘ.ተ. እንደ ኢንፌክሽን አጋላጭ ተደርገው ይጠቀሳሉ ብለዋል ዶክተር አበበ።

የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን በታዳጊ ሀገራት ላይ በብዛት እንደሚስተዋል ጠቁመው፤ ጾታ፣ ዘርና ቀለምን እንደማይለይም አስገንዝበዋል።

✍️ የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽንን መከላከል ይቻላል?

የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽንን ለመከላከል በዋናነት አጋላጭ ምክንያቶችን በመለየት እነሱ ላይ ቀድሞ መሥራት ነው።

በዚህም መሠረት፤ ምጥ ሳይኖር የእንሽርት ውኃ ቀድሞ ከፈሰሰ ቶሎ በሐኪም መታየት እና ሕክምና መውሰድ፣ በእርግዝና ጊዜ የሚከሰት የእናቶች ኢንፌክሽን (የማህፀን፣ የሽንት ቱቦ፣ የሳንባ ወዘተ ካለ) በአግባቡ መታከም፣ የተራዘመ ምጥ ማስወገድ፣ በቂ የእርግዝና ክትትል ማድረግና በጤና ተቋም መውለድ እንደሚገባ መክረው፤ ይህም ህመሙን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚረዳ አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም ከተወለዱ በኋላ በአራስ ቤታቸው እያሉ ሳል ወይም ሌላ ተላላፊ ህመም ያለበት ሰው እንዳይቀርብ ማድረግና መጠንቀቅ፣ በቤት ውስጥ ጭስ እንዳይኖር ማድረግ እንዲሁም የጨቅላ ሕጻናት አደገኛ ምልክቶችን በየጊዜው መከታተል ያስፈልጋል ሲሉ መክረዋል።

የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ምልክቶችን ያሳየ ጨቅላ ሕጻን በቶሎ ወደ ጤና ተቋም ከተወሰደና በተገቢው ሁኔታ ከታከመ የመዳን እድሉ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

✍️ የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ምልክቶች ምንድን ናቸው?

በአጠቃላይ የጨቅላ ሕጻናት ምልክቶች አደገኛ ተብለው እንደሚጠሩ የገለጹት ዶክተር አበበ፤ ከታች የተጠቀሱት ምልክቶች የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን ጠቋሚዎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

• ቶሎ ቶሎ መተንፈስ፣ ረጅም ሠዓት የሚቆይ ማቃሰት፣ የሰውነት ትኩሳት (መቀዝቀዝ)፣ የሰውነት መንቀጥቀጥ፣ ጡት አለመሳብ፣ መፍዘዝና አለመንቃት፣ ራስን መሳት፣ በጣም ተከታታይና ኃይለኛ ትውከት፣ የዐይንና የሰውነት ቢጫ መሆን፣ የሆድ ከመጠን በላይ መወጠር፣ የከንፈርና የምላስ መጥቆር።

✍️ የጨቅላ ሕጻናት ኢንፌክሽን እንዴት ይታከማል?

እንደ ዶክተር አበበ ገለጻ፤ ከላይ የተጠቀሱት አደገኛ ምልክቶች ከታዩ በቶሎ ወደ ጤና ተቋም መውሰድ ያስፈልጋል።

በሕክምና ወቅትም፤ የአተነፋፈስ ሁኔታ ታይቶ ለአተነፋፈሱ እገዛ (ኦክስጅን) ሊሰጥ ይችላል ብለዋል።

ትኩሳት ካለም የትኩሳት ማስታገሻ፣ የሰውነት ሙቀቱ ዝቅ ያለ ከሆነ በማሞቂያ (Radiant warmer) እንዲስተካከል ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

የስኳር መጠናቸው ዝቅ ካለም ግሉኮስ (dextrose) እንደሚሰጣቸው አስረድተዋል።

ከደም የሚወሰዱ ምርመራዎች እና ከጀርባ የሚወሰድ ምርመራ (Cerebro spinal fluid analysis & Culture) ማድረግም እንደ ህመሙ ዓይነት የሕክምናው አካል መሆኑን ነው ያስረዱት።

በዋናነትም በመርፌ የሚሰጡ ፀረ-ተኅዋስያን መድኃኒቶችን እንዲወስዱ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

#ኢዜአ

14/12/2025

የፖሊዮ (Poliomyelitis) በሽታ
************

▪️ ፖሊዮ/የልጅነት ልምሻ በፖሊዮ ቫይረስ አማካይነት የሚመጣ ተላላፊ በሽታ ሲሆን በአብዛኛው ልጆችን የሚያጠቃ በሽታ ነዉ፡፡
▪️ ቫይረሱ ለዕድሜ ልክ አካል ጉዳተኝነት የሚያጋልጥ እና አልፎ ተርፎም በሰዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ የሚችል ነዉ።

የፖሊዮ ኢንፌክሽን ዓይነቶች

1️⃣ ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳይ (Asymptomatic)

በፖሊዮ ቫይረስ ከተያዙ ሰዎች 90-95% የሚሆኑት ምንም ዓይነት የሚታይ ምልክት አያሳዩም። ነገር ግን ቫይረሱን ማሰራጨት እና ሌሎችን መበከል ይችላሉ።

2️⃣ መጠነኛ (Minor) ፖሊዮ

ከተያዙ ሰዎች 4-8% ያህሉ መለስተኛ ምልክቶች ያጋጥማቸዋል። እነዚህም ምልክቶች ለ2–5 ቀናት የሚቆዩ ሲሆን ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ህመም እና ማስታወክን ያካትታሉ። እነዚህ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ይጠፋሉ።

3️⃣ ከባድ የአካል ጉዳት የሚያስከትል (Paralytic) ፖሊዮ

ከ1% ያነሱ ኢንፌክሽኖች ወደ ከባዱ የፖሊዮ አይነት ያመራሉ። ቫይረሱ የነርቭ ሥርዓትን በመጉዳት፤ የጡንቻ ህመም እና ድንገተኛ የጡንቻ መልፋስፋስ እና መዛል (Acute Flaccid Paralysis) ያስከትላል። ይህም በአብዛኛዉ የእጅና የእግር ጡንቻዎችን የሚጎዳ ሲሆን ከ5%–10% በሚሆኑት ላይ የአተነፋፈስ ጡንቻቸውን በመጉዳት ለሞት ይዳርጋል።

ፖሊዮ የሚተላለፍባቸዉ መንገዶች

▪️ ፖሊዮ ቫይረስ በቀላሉ የማይጠፋ ቫይረስ ሲሆን ወደ ሰውነት የሚገባው በዋነኛነት በአፍ በኩል ነዉ፡፡
▪️ የሚተላለፋዉ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ሰገራ ውስጥ ያለው ቫይረስ ንጽህና ባልተጠበቀ መንገድ (ለምሳሌ በቆሸሸ እጅ፣ በተበከለ ውሃ ወይም ምግብ) ወደ ጤነኛ ሰው አፍ ሲገባ ነው።

የፖሊዮ በሽታ እንዴት መከላከል ይቻላል

▪️ ፖሊዮ መድኃኒት የሌለው በሽታ ሲሆን ክትባት ብቸኛ መከላከያዉ ነዉ።
▪️ ከ1988 ዓ.ም ወዲህ የፖሊዮ ክትባት በአለማችን ወደ 20 ሚሊዮን የሚጠጉ የአካል ጉዳት ክስተቶችን በተጨባጭ መግታት ችሏል።

የፖሊዮ ስርጭትን ለመግታት ምን ማድረግ አለብን?

▪️ የእጅ ንጽህና መጠበቅ: በተለይም መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ እና ምግብ ከመብላት በፊት እጅን በሳሙናና በውሃ ደጋግሞ መታጠብ
▪️ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ብቻ መጠቀም እና ምግብ በአግባቡ አዘጋጅቶ መመገብ



Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

13/12/2025
26/11/2025

ህፃናት እንደ ተወለዱ የሚሰጥ የጉበት በሽታ መከለከያ ክትባት
__________

ከወሊድ በኋላ የሚሰጥ የሄፐታይተስ ቢ ክትባት ወይም የጉበት በሽታ መከለከያ ክትባት ቫይረሱ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍና ሕፃናት ወደፊት እንደ የጉበት ጠባሳ እና የጉበት ካንሰር ያሉ ሥር ለሰደዱ የጤና ችግሮች እንዳይጋለጡ ይከላከላል።

በተለይም እናት የቫይረሱ ተሸካሚ ከሆነች፥ ከወሊድ በኋላ ክትባቱን መስጠት ኢንፌክሽኑን ለመከላከል በጣም ውጤታማው መንገድ ነው።

የሄፐታይተስ ቢ ክትባት ህፃናት ከተወለዱ በኋላ ባሉት የመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓታት ውስጥ ይሰጣል። በመጀመሪያዎቹ 24 ሰዓት ውስጥ ክትባቱ መስጠት አስተማማኝ እና ውጤታማ ነው ።

ከሆስፒታል ውጭ ለተወለዱ ህጻናት ክትባቱን ከተወለዱ በኋላ ባሉት 14 ቀናት ውስጥ መከተብ አለባቸው።

ክትባቱ በሁሉም የመንግስት ጤና ተቋማት እና በተወሰኑ የግል ጤና ተቋማት ውስጥ ይሰጣል!

Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VAB

25/11/2025
22/11/2025

THE HUB OF SUB-SPECIALTY CARE!
የሰብ ስፔሻሊስቶች መገኛ ማዕከል!

21/11/2025

🚨ኪንታሮት ህመም መዘዞችና ህክምናው🚨

የኪንታሮት ህመም ማለት በፊንጢጣ እና ሬክተም በተባለው የታችኛው የሰውነት ክፍላችን ላይ ያሉ የደም ስሮች ማበጥ ነው፡፡

ምልክቱም ሰገራ ስንቀመጥ ህመም መሰማትእንዲሁ የማሳከክ ስሜት መኖር ነው ይህም ያለመመቸት ስሜት የሚከሰተው የደም ስሮቹ ግድግዳዎች በጣምሲለጠጡ ሲሆን ማለትም በሚኮማተሩበት እንዲሁም በሚለጠጡበት ጊዜ የፊንጢጣችን እና ሬክተም የሚባለው የሰውነታችን ክፍል ብዙ የደም ስሮች ያሉት በመሆኑእነዚህም ስሮች የማበጥ እና ጎልቶ የመታየት ባህሪ ስላላቸው በዚህ አካባቢ ኪንታሮት የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ችግሩ ሲጀምር ከማሳከክ ይነሳና ሲብስ ደግሞ የሬክተም መድማት ሊያመጣ ይችላልየህመሙ ደረጃ ምንም ያክል ቢሆን በቀላሉ ማከም እና መቆጣጠር ይቻላል፡፡

ስለ ጉዳዩ አንስቶ መወያየት ምቾት የሚሰጥ ባይሆንም የህመሙ ምልክቶች መታየት እንደጀመሩ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ አስፈላጊ ነው በኪንታሮት ህመም ሴቶችም ሆኑ ወንዶች በእኩል ደረጃ የመጠቃት እድል ቢኖራቸውም እንደ እርግዝና የመሳሰሉ ተፈጥሮዊ ክስተቶች ደግሞ ይበልጥ ተጋላጭነቱን ይጨምራሉ፡፡

የኪንታሮት በሽታ መንስኤዎች፤
የጸና ተቅማጥ ህመም መኖር፣ የጸና የሆድ ድርቀት ህመም

#እርጅና

ከመጠን ያለፈ ውፍረት እና በፋይበር የበለጸጉ ምግቦችን በበቂ ሁኔታ ያለመውሰድ፣ በተደጋጋሚ ከባድ እቃዎችን ማንሳት፣ በፊንጢጣ በኩል የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት፣ የፊንጢጣ ቁስለት እንዲሁም በዘር የሚተላለፍ የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።

የኪንታሮት በሽታ አይነቶች

1.የውጪ ኪንታሮት

የሚፈጠረው በፊንጢጣ ቆዳ ስር ሲሆን የማበጥ የማሳከክ እንዲሁም በሽተኛው በሚጸዳዳበት ወቅት ደም መፍሰስ ምልክቶች ይኖሩታል ፡፡

2.የውስጥ ኪንታሮት

የሚወጣው በታችኛው የአንጀታችን ክፍል (Re**um) ላይ ሲሆን በአብዛኛው ህመም አልባ ነው፡፡ የህመሙ ተጠቂ በሚጸዳበት ጊዜ ወይም ከተጸዳዳ በኋላ ደም ስሮቹ ላይ ጫና የመፈጠር ነገር ስለሚኖር ደም መፍሰስ ሊታይ ይችላል፡፡

ቅድመ መከላከል

የፋይበር ይዘት ያላቸውን ምግቦች መውሰድ፣ በቂ ፈሳሽ መውሰድ፣ መደበኛ የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የምንጸዳዳበትን መደበኛ ሰዓት ማለማመድ

የህክምና አማራጮች

ወደ ህክምናው ስንመጣ የሀይድሮኮርቲሶን ይዘት ያላቸውን ክሬሞች እና በፊንጢጣ የሚገቡ የሰገራ ማለስለሻ መድኀኒቶችን መጠቀም የሚቻል ሲሆን እብጠቱ በወጣበት ቦታ ላይም በረዶ መያዝ እንዲሁ እብጠቱ እንዲቀንስ ይረዳል ህመሙ የሚብስ ከሆነ ደግሞ እንደ አስፈላጊነቱ ህመም ማስታገሻዎችን መውሰድ ሊያስፈልግ ይችላል ፡፡

HAL-HAR ማለት በአነስተኛ ቅድ የሚከናወን ህክምና ሲሆን በሁሉም ደረጃ ላለ የኪንታሮት ህመም የሚሆን የህክምና አማራጭ ነው ፡፡

ህክምናው የሚከናወነው ዶፕለር በሚባል መሳሪያ በመታገዝ ሲሆን ወደ ፊንጢጣ የሚሄዱትን የደም ስሮች ቋጥሮ በመስፋት የሚደረግ ነው፡፡

ከ HAL-HAR ህክምና በኋላ ህመምን ማስታገስ!

ይህ ህክምና ዘዴ ህመም የለሽ እና በጣም አስተማማኝ የኪንታሮት ህክምና ማድረጊያ ዘዴ ነው ህክምናው ከተከናወነ በኋላ ታካሚው ምንአልባት ከ 1-2ቀናት ውስጥ የህመም ስሜት ሊኖረው ስለሚችል የቬጂታኒ ሆስፒታል ህመምን የመቆጣጠር ስፔሻሊስቶች ህመሙን ይቆጣጠራሉ ፡፡

በዚህ ህክምና ዘዴ ብዙ ታካሚዎች ከ 1ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያገግማሉ፡፡

21/11/2025

💜👄 የአፍ ካንሰር የግንዛቤ ማስጨበጫ ወር 🌍✨

በዚህ ዓመት "close the care gap" በሚል መሪ ቃል የአፍ ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር እየተከበረ ይገኛል።

⚠️ ችላ መባል የሌለባቸው ምልክቶች፡-

🩸 የማይድኑ የአፍ ቁስለቶች፣
⚪ ነጭ ወይም ቀይ ነጠብጣብ እብጠቶች፣
😣 በማኘክ ወይም በመዋጥ ጊዜ የሚሰማ ህመም
👄 በአፍ፣ አንገት ወይም መንጋጋ ላይ ያሉ እብጠቶች
🎤 የድምፅ ለውጥ
👅 የከንፈር ወይም የምላስ መደንዘዝ ስሜት
🩸 ምክንያቱ ያልታወቀ የአፍ መድማት

🔥ዋና ዋና መንስኤዎች፡-

🚬 ሲጋራ ማጨስ
🍷 የአልኮል መጠጥ በብዛት መጠቀም
🌞 ከንፈር ለፀሐይ መጋለጥ
🦠 የHPV ኢንፌክሽን
😬 በቂ ያልሆነ የአፍ ንፅህና አጠባበቅ
👴 እድሜ ከ40 በላይ መሆን ለአፍ ካንሰር ተጋላችነትን ይጨምራል

🏥 በኦንኮ አድቫንስድ የምርመራ ማእከል

🩺የባዮብሲ (ከአጠራጣሪ ቁስለቶች)
🔬 የሳይቶሎጂ እና
🧪 የኢሚኖሂስቶኬሚስትሪ ምርመራዎች
⚡ ከፈጣን እና አስተማማኝ አገልግሎት ጋር ያገኛሉ።

📞 0945606969 | 0949065555 | 0949045555
☎️8189


21/11/2025
19/11/2025

⚠️ ስለማርበርግ ቫይረስ ምን ማወቅ አለብን? ራሳችንንስ እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
በቅርቡ ሃገራችን ውስጥ ከባድ እና በጣም ተላላፊ በሽታ ተገኝቷል።
የጤና ባለስልጣናት እና የዓለም ጤና ድርጅት በፍጥነት ምላሽ እየሰጡ ቢሆንም፣ ስርጭቱን ለማስቆም የማህረሰቡ ግንዛቤ እና መከላከል ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

❗️ እንዴት ይሰራጫል
👉🏽 በመጀመርያ ከለሊት ወፍ ወደ ሰው ይተላለፋል።
👉🏽 በመቀጠል በበሽታው ከተያዘ ሰው (በህይወት ካለም ይሁን ከሞተ ሰው) ጋር በሚኖር የደም ወይም ማንኛውም ፈሳሽ ንክኪ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል።
👉🏽 በበሽታው የታመመ ሰው ፈሳሽ ያለበት ማንኛውም ነገር ለምሳሌ ልብሶች፣ ፎጣ፣ አልጋ ወዘተ መንካት በሽታውን ያስተላልፋል።

🛡 እንዴት ራስዎን እና ቤተሰብዎን መጠበቅ ይችላሉ?
✅ ከታመመ ሰው፣ በዚህ ህመም ከሞተ ሰው፣ እና ይህ ህመም ያለበት ሰው የተጠቀመበትን ማንኛውም ነገር አለመንካት ።
✅ እጅን አዘውትሮ መታጠብ ( በሳሙና ወይም አልኮል)
✅ ለጤና ባለሞያዎች ህክምና ሲሰጡ እንደ ኮቪድ ከላይ እስከ ታች የሚለበስ መከላከያ(PPE) ማድረግ
✅ በበሽታው ህይወቱ ካለፈ ሰው ቀብር ላይ ጥንቃቄ በማድረግ መከላከል ይቻላል።

🚨 ችላ ማለት የሌለብዎት የማስጠንቀቂያ ምልክቶች
👉🏽 ድንገተኛ ከፍተኛ ትኩሳት
👉🏽 ከባድ ራስ ምታት
👉🏽 የጡንቻ ህመም
👉🏽 ትውከት ወይም ተቅማጥ
👉🏽 ከድድ፣ ከአፍንጫ ወይም ከሰገራ/ትውከት ያልተለመደ ደም መፍሰስ
👉🏽 እርስዎ ወይም በአካባቢዎ ያለ ሰው ላይ ምልክቶችን ካዩ በአስቸኳይ ወደ ጤና ተቋም ይሂዱ። ቀደም ብሎ ሪፖርት ማድረግ ስርጭትን ለመከላከል ወሳኝ ነው።

💉በበሽታው መያዛችን ከተረጋገጠ ምን አይነት ህክምና ይደረጋል?
" እንዳስፈላጊነቱ ግሉኮስ ፣ ደም መስጠት ፣ የደም ህዋሶችን መስጠት፣ ህመም ማስታገስ፣ ኦክስጅን እንዲሁም መተንፈሻና የኩላሊት ህክምና እንደየ ክብደቱና አይነቱ ይደረጋሉ። "

📢 መረጃዎን በንቃት ይከታተሉ
ማርበርግ እስካሁን ምንም አይነት ህክምና ወይም ክትባት የለውም ነገር ግን በጊዜ አጋዥ ሕክምናዎችን ማግኘት ከበሽታው የመዳን እድልን ይጨምራል

📞 ለበለጠ መረጃ ወይም ቀጠሮ ለመያዝ 0935402078 ወይም በአጭር የስልክ መስመር 9000 ይደውሉ።

📍 አድራሻ፡- ሰፈረ ሰላም ወደ ከአውቶቢስ ተራ ወደ ኮልፌ በሚወስደው መንገድ ያገኙናል።

ኢትዮ-ጠቢብ ሆስፒታል
ሁሌም ለጤናዎ እንተጋለን!

19/11/2025
19/11/2025

የማርበርግ ቫይረስ መተላለፊያ እና መከላከያ

ኅዳር 9፣ 2018 (አራዳ ኤፍ ኤም) የበሽታው ምልክት ለቫይረሱ በተጋለጡከ2 እስከ 9 ባሉት ቀናት ውስጥ ይታያሉ።

ምልክቶች፦ ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ስር ደም መፍሰስ

ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፣

የጡንቻ እና የጀርባ ህመም፣ ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፣ ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ።

መተላለፊያ መንገዶች፦ ከበሽተኛ ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ንክኪ፣ በታመመ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች ጋር የሚ ኖር ንክኪ፣ በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎችይተላለፋል፤

መከላከያ መንገዶች፦ ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፣ ከታመመ ሰው ጋር ንክኪ እና ትኩሳት ካለ ወደ ጤና ተቋም መሄድ፣ ሞት በሚከሰትበት ጊዜ አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀት እና መቅበር፤ አላስፈላጊ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ፣ ከታመመ ሰው ደም እና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፣ ለታመመ ሰው እንክብካቤ በሚደረግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣ እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውሃ በአግባቡ መታጠብ

የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/.1
Tiktok:https://www.tiktok.com/.1offical

Telegram:-https://t.me/Arada_Fm

Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital

Facebook:-https://web.facebook.com/

aradafm

Address

Addis Ababa

Telephone

+251911466707

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Al-Afdel Medium Clinic And Health Care Councling posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Al-Afdel Medium Clinic And Health Care Councling:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram