Fikreselam General Hospital

Fikreselam General Hospital " Heartfelt Care and Serving Hands "

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጎን።📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6ለበለጠ ...
21/10/2025

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጎን።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

የደም ማነስ/Anemia      የደም ማነስ በሽታ የሚከሰተዉ በሰዉነታችን ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሳት ሲያንሱ ወይም የሄሞግሎቢን መጠን ሲያንስ ነዉ::🔹ምክንያቶቹ🔸ሰዉነታችን በቂ የደም ...
20/10/2025

የደም ማነስ/Anemia

የደም ማነስ በሽታ የሚከሰተዉ በሰዉነታችን ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሳት ሲያንሱ ወይም የሄሞግሎቢን መጠን ሲያንስ ነዉ::

🔹ምክንያቶቹ

🔸ሰዉነታችን በቂ የደም ህዋሳት ሳያመርት ሲቀር
🔸ቀይ የደም ህዋሳት ቶሎ ቶሎ የሚሞቱ ከሆነ
🔸የደም መፍሰስ
🔸ሌሎች ተጓዳኝ ህመሞች

🔹ምልክቶቹ

•የድካም ስሜት
•አቅም ማጣት
•የትንፋሽ ማጠር
•መገርጣት
•የማዞር ስሜት
•ራስ ምታት
•ትኩረት ማጣት

🔸ህክምና
የደም ማነስ ህክምና እንደ ምክንያቱ ይለያል::በምግብ እንዲሁም በእንክብል የአይረን ንጥረ ነገር ማግኘት አስፈላጊ ነዉ::

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጎን።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

የማድያት ህመም ምልክቶችማድያት በፊት ላይ ግራጫና ቡናማ መካከል ያለ በጣም የተለመደ የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚያመጣ ሲሆት ብዙውን ጊዜ የሚታየው ወይም የሚከሰተው በሚከትሉት ቦታዎች ላይ ነው።-...
15/10/2025

የማድያት ህመም ምልክቶች

ማድያት በፊት ላይ ግራጫና ቡናማ መካከል ያለ በጣም የተለመደ የቆዳ ቀለም ለውጥ የሚያመጣ ሲሆት ብዙውን ጊዜ የሚታየው ወይም የሚከሰተው በሚከትሉት ቦታዎች ላይ ነው።

- በጕንጭ ላይ፣
- በአፍንጫ፣
- ከላይኛው ከንፈር ከፍ ብሎና
- አገጭ ላይ

ማድትን ሊያስነሱ የሚችሉ ነገሮች

- ለጸሀይ ብርሃን መጋለጥ
- የሆርሞን መለዋወጥ
- አንዳንድ ኮስሞቲክስ

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡

☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

Facebook: https://www.facebook.com/p/Fikreselam-General-Hospital-61555841617995/

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

HAPPY SundayDon't forget the importance of regular exercise. Studies show that just 30 minutes of physical activity per ...
12/10/2025

HAPPY Sunday

Don't forget the importance of regular exercise. Studies show that just 30 minutes of physical activity per day can help reduce the risk of chronic illnesses like heart disease and diabetes. Take a brisk walk, or try a new workout - your body will thank you!

የመደበኛ አካል ብቃት እንቅስቃሴን አስፈላጊነት አይርሱ ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በቀን h30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እንደ ልብ ህመም እና የስኳር በሽታ ያሉ ሥር የሰደዱ በሽታዎችን ተጋላጭነት ለመቀነስ ይረዳል።

ፈጣን የእግር ጉዞ ያድርጉ ወይም አዳዲስ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይሞክሩ!

ጤናማ እና ንቁ እሁድ እንመኛለን።🌞

📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡

☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

Facebook: https://www.facebook.com/p/Fikreselam-General-Hospital-61555841617995/

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል አነስተኛ የሆነ የቀዶ ጥገና ስልትን በመጠቀም ህክምና የሚሰጥ የላፓሮስኮፒ ቀዶ  ህክምና አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ። 🔻ይህ የላቀ ቴክኖሎጂ ለታካሚዎቻችን🔸 ፈ...
09/10/2025

በፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል አነስተኛ የሆነ የቀዶ ጥገና ስልትን በመጠቀም ህክምና የሚሰጥ የላፓሮስኮፒ ቀዶ ህክምና አገልግሎትን ማግኘት ይችላሉ።

🔻ይህ የላቀ ቴክኖሎጂ ለታካሚዎቻችን
🔸 ፈጣን የማገገም ጊዜ
🔸 አነስተኛ ህመም
🔸 ትናንሽ ጠባሳዎች እና
🔸 አጭር የሆስፒታል ቆይታ እንዲኖራቸው ያስችላል።

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

የጡት ካንሰርየጡት ካንሰር ማለት ምንድነዉ?•  የጡት ካንሰር ማለት በጡት ሕብረ ሕዋስ ውስጥ ያልተለመዱ ህዋሳት በቁጥር በማያስፈልግ መጠን እና ሁኔታ መራባት ነው።• በጡት ካንሰር ብዙውን ጊ...
06/10/2025

የጡት ካንሰር

የጡት ካንሰር ማለት ምንድነዉ?

• የጡት ካንሰር ማለት በጡት ሕብረ ሕዋስ ውስጥ ያልተለመዱ ህዋሳት በቁጥር በማያስፈልግ መጠን እና ሁኔታ መራባት ነው።
• በጡት ካንሰር ብዙውን ጊዜ ሴቶች ቢጠቁም ወንዶችም አንዳንድ ጊዜ በበሽታው ሊያዙ ይቻላል ::

የጡት ካንሰር ምልክቶች

🔷 የጡት ዉስጥ ወይም ብብት ስር እብጠት
🔷በጡት ጫፍ አካባቢ ህመም
🔷በእርግዝና እና በማጥባት ወቅት ካልሆነ በስተቀር ከጡት ጫፍ የሚታይ ፈሳሽ (ደምን ጨምሮ )
🔷በአንዱ ወይም በሁለቱም የጡት ጫፎች ቅርጽ መለወጥ
🔷 የጡት ቀለም ለዉጥ
🔷በአጭር ግዜ ዉስጥ የጡት መጠን እና ቅርፅ መጨመር
🔷የጡት ጫፍ ቆዳ መሰርጎድ
🔷የጡት ቆዳ መቅላት ወይም መላጥ ልክ እንደ ብርቱካን ቆዳ

ለጡት ካንሰር የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

🔸ሴት መሆን ፣ እድሜ
🔸አንዳንድ በዘር ዉስጥ የሚመጡ የዘረመል ለውጦች
🔸ከወለዱ በኃላ ጡት አለማጥባት
🔸ከ 12 ዓመት እድሜ በፊት የወር አበባ መምጣት እና ከ 55 ዓመት እድሜ በኋላ የወር አበባ መቆም
🔸የጡት ካንሰር ከዚህ በፊት ከተያዙ
🔸የጡት ካንሰር የቤተሰብ ታሪክ
🔸ጡትን በጨረር በተደጋጋሚ መታከም
🔸የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እጥረት
🔸አልኮል መጠጣት

የጡት ካንሰር ምርመራ

🔹ማሞግራም፣ የጡት ራጅ (X-Ray)

መከላከያ መንገድ

ጡት በማጥባት ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፣ ክብደታችንን በመቀነስ ፣ ተገቢ የሆነ የህክምና ክትትል በማድረግ

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

📌 የቫሪኮስ ቬይንስ (Varicose Veins)🔻 የቫሪኮስ ቬይንስ በሽታ ምንነትቫሪኮስ ቬይንስ የምንለው የሕምም ዓይነት በማንኛውም የሰውነት ክፍላችን ቬይኖች (የደም መልስ) ቱቦዎች ሊከሰት ...
03/10/2025

📌 የቫሪኮስ ቬይንስ (Varicose Veins)

🔻 የቫሪኮስ ቬይንስ በሽታ ምንነት

ቫሪኮስ ቬይንስ የምንለው የሕምም ዓይነት በማንኛውም የሰውነት ክፍላችን ቬይኖች (የደም መልስ) ቱቦዎች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው የሚያጠቃውና የተለመደው በእግር ላይ የሚከሰተው ነው፡፡

🔻 ለቫሪኮስ ቬይንስ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች

🔸 ዕድሜ ፡- ዕድሜ መጨመር ለህመሙ ያጋልጣል
🔸 ፆታ፡- በሴቶች ላይ በአብዛኛው ይከሰታል ይህም የሚሆነው በሰውነታቸው ላይ ከሚከሰቱ ሆርሞን ለውጦች እና በእርግዝና ጊዜ ነው፡፡
🔸 በቤተሰብ፡- ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ አንድ የቤተሰብ አባል ተጠቂ ከሆነ ለሌላው የቤተሰብ አባል የመያዝ ዕድሉን ይጨምራል፡፡
🔸 ከልክ ያለፈ ውፍረት፡- የሰውነት ክብደት መጨመር በቬኖች የደም መመለስ ሥራ ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡
🔸 ለብዙ ሰዓታት መቆም ወይንም መቀመጥ፡- ደም ከእግራችን ወደ ልብ የሚመላለስበት ሁኔታ በማዛባት ለብዙ ሰዓታት መቆምም ሆነ መቀመጥ ለቫሪኮስ ቬን ሕመም ተጋላጭ ያደርገል።

🔻 የቫሪኮስ ቬይንስ ህመም ምልክቶች

🔸 ጥቁር፣ ወይንጠጅ ወይንም ሰማያዊ ቀለም ያለው የደም ስር እብጠት በእግራችን ላይ መኖር
🔸 ጠመዝማዛ የሆኑና የአበጡ የደም ስሮች በእግሮ ላይ መታየት
🔸 እግርን የመክበድና የህመም ስሜት መሰማት
🔸 በታችኛው የእግር ክፍል የማቃጠል፣ የመጨምደድና የመርገብገብ ስሜት መሰማት
🔸 ለረጅም ሰዓታት ሲቆሙም ሆነ ሲቀመጡ የሚብስ የህመም ስሜት
🔸 የማሳከክ ስሜት

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል

📍አድራሻ - ሲኤምሲ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6

ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

ቤት ውስጥ መንቀሳቀስ የማይችሉ ሰዎችን እንዴት መንከባከብ እንችላለን 🔷መንቀሳቀስ የማይችሉ ወይም የሚከብዳቸው  ሰዎችን በቤታችን ልናረግላቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱ የቆዳ እንክብካቤ ነው:: ...
30/09/2025

ቤት ውስጥ መንቀሳቀስ የማይችሉ ሰዎችን እንዴት መንከባከብ እንችላለን

🔷መንቀሳቀስ የማይችሉ ወይም የሚከብዳቸው ሰዎችን በቤታችን ልናረግላቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱ የቆዳ እንክብካቤ ነው:: ይህም በሰውነታቸው ላይ ቁስለት (bedsore) እንዳይከሰትባቸው ያረጋል፡ ::

🛏ምን እናርግ

🔸በየ2ሰዓቱ አካላቸውን ማዞር
🔸ትራስ ከመገጣጠሚዎቻቸው ስር ማረግ
🔸የሚተኙበትን ቦታ ንጹህ እና ደረቅ ማረግ
🔸ሽንት እና ሰገራ ከተጠቀሙ በኃላ ቶሎ ማፅዳት
🔸ቆዳቸው እንዳይደርቅ ቅባት መጠቀም
🔸ተመጣጣኝ ምግብ እና ውሃ🥙💧መስጠት
🔸በየቀኑ ቆዳቸውን ማየት👀

ተረከዝ👣
ዳሌ
ክርን💪
ታችኛው ጀርባ

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

Fikreselam General Hospital · Behind GAST Entertainment, Fikreselam General Hospital, Addis Ababa, Ethiopia (https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6)
★★★☆☆ · Hospital

26/09/2025
26/09/2025

መተኪያ ለሌለው ውድ ህይወቶትዎ የጤና ምርመራን ያድርጉ!
የጤና ምርመራዎችን በማድረግ የሚያገኙት ጥቅሞች:
1. የጤና እክሎችን ቀድሞ መለየት
2. ወጪ መቀነስ
3. ደህንነት ላይ ትኩረት ማድረግ እና
4. በሽታን ቀድሞ መከላከል ላይ ትኩረት ማድረግ

ወርቃማ ልቦች አገልጋይ እጆች!
ፍቅርሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
+251 93 959 5960

25/09/2025

☀️ህጻናትን ፀሀይ እንዴት እናሙቅ?
ለምን ይጠቅማል?

🔷ጥቅሙ

🔸አካላቸው Vitamin D(ቫይታሚን ዲ) እንዲያመርት

🔸ጥሩ እንቅልፍ እንዲተኙ

🔸ደስተኛ እንዲሆኑ

🔷ፀሀይ እንዴት እናሙቅ ?

🔸ጠዋት 4 ሰአት አካባቢ

🔸በሳምንት ከ4-5 ቀናት

🔸ሙሉ ገላቸውን ለፀሀይ በማጋለጥ

🔸ምንም አይነት ቅባት ሳንቀባቸው

🔸ፀሀይ ቀጥታ በሚያገኙበት ቦታ

✨ይህን ለማድረግ የማይመችዎት ከሆነ ሀኪም በማማከር ቫይታሚን ዲ (Vitamin D)ለልጆ ይስጡ::

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል
📍አድራሻ - በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊትለፊት ከጋስት ሞል ጀርባ።
📍Location- https://maps.app.goo.gl/mc1ydidPRYfRJvjC6
ለበለጠ መረጃ ፡
☎️ +251-939-595-960 ላይ ይደዉሉልን።

✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

20/09/2025

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል!
✨ወርቃማ ልቦች ፤ አገልጋይ እጆች✨

Address

CMC
Addis Ababa

Telephone

+251939595960

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fikreselam General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category