20/11/2019
ባለንጀሮችዋና ጎሮቤቶችዋን በማማት ጊዜዋን የምታባክን ኣንዲት ሴት ነበረች። የቤተ ክርስትያኒቱ ሰባኪ በዚህ ክፉ ስራዋ በብዙ ኣስቦበት ኣንድ ቀን ሊገስጻት ቤቷ ድረስ ሄደ። ቤቷም አንደ ደረሰ በ ከረጢት ቋትሮ የወሰደውን የደሮ ላባዎች ብሜዳ አንድትበትን ነገራት። አርሷም በነገሩ በመደመም አንዳላት ኣደረገች። የዶሮ ላባዎች ለነፋስ ሰጠች። ነፋሱም ላባዎችን በየስፍራው ኣሰራጨ። ከዚያም ቀጥሎ መምህሩ ላባዎችን አንድትሰበስብ ጠየቃት።ሴቲቱም የማይቻል መሆኑን ገለጸች ። ሰባኪውም በዚህ ጊዜ ኪያስተምራት የፈለገውን አንዲህ ሲል ተናገረ። በየስፍራው የተሰራጩ ላባዎች መሰብሰብ አንድማይቻል ሁሉ አንዲሁም በ ሐሜት የፈጸምሽው ጉዳት መመለስ ኣይቻልም። ሴቲቱም ከመጀመርያ ጊዜ ምላሷ ክፉ አንደሆነ ለመገንዘብ በቃች ። ኣንባቢ ሆይ ኣንተም ሰው ኣምተህ አንደሆን ኣስታውስ። በሐሜትህ ሌላውን ሰው ጎድተህ ኣታውቅምን? በወዳጆች መካከል መለያየት ፈጥረህ ኣታውቅምን? አርስ በአርሳችን አንዳንፈራረድ አንዳንተማማ አግዚኣብሔር ብዙ ተአዛዛት ሰቶናል።