Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) I feel I am still a student, a beginner journalist with a great zeal to learn more.

I am climbing up the ladder and register remarkable achievement in my profession. This page is dedicated to serve you with reliable news and voice for voiceless.

ለአውሮፕላን ቲኬት እና ለአበል የወጣው ወጪ በ10 ክልሎች ስታዲየም መገንባት ያስችል ነበር:-ኢሳያስ ጅራ  | የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 17ኛ መደበኛ ጠቅላለ ጉባኤውን በአፍሪካ ኢኮኖሚ...
30/10/2025

ለአውሮፕላን ቲኬት እና ለአበል የወጣው ወጪ በ10 ክልሎች ስታዲየም መገንባት ያስችል ነበር:-ኢሳያስ ጅራ

| የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 17ኛ መደበኛ ጠቅላለ ጉባኤውን በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዛሬ አካሂዷል።

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በ2017 በጀት ዓመት ለዋልያዎቹ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ውድድር ከ91 ሚሊየን በላይ ብር ወጪ መሆኑን ገልፀዋል።

ለዚህ የዳረገን ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሀገሪቱ አለመኖሩ ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ ለጉዞ እና አበል የወጣው ወጪ በ10 ክልሎች ስታዲየም መገንባት ያስችል ነበር ብለዋል።

በዓለም፣ አፍሪካ እና ሴካፋ ዞን ላደረግናቸው የማጣሪያ ጨዋታዎች ሞሮኮ ድጋፍ ባታደርግልን ወጪያችን ከ300 ሚሊየን ይሻገር ነበር ነው ያሉት።

ebc sport

11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት  ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ   | የአፍሪካ የቆዳ፣ ጨርቃጨርቅ፣ አልባሳት ኢንዱስትሪን ለማነቃቃት ታስቦ የሚሰናዳው የአፍሪካ የፋሽን ሳምንት(ASFW)  በአዲስ ...
30/10/2025

11ኛው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ኤግዚቢሽን በይፋ ተከፈተ

| የአፍሪካ የቆዳ፣ ጨርቃጨርቅ፣ አልባሳት ኢንዱስትሪን ለማነቃቃት ታስቦ የሚሰናዳው የአፍሪካ የፋሽን ሳምንት(ASFW) በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ተከፈተ።

የአፍሪካ ገበያ ሰፊ እንደመሆኑ በርካታ ከአፍሪካ ውጭ ባሉ ሀገራት የተመረቱ ምርቶች መዳረሻ ናት።

ሆኖም በፋሽን ገበያው ዘርፍ መሪ ሆኖ ለመቀጠል ጥራት ያላቸው አልባሳት ከውጭ እንዲገቡ ማስቻል እጅግ ጠቃሚ ነው።

ከ210 በላይ ተቋምት የተሳተፉበት ከ 6000 በላይ ጎብኚዎች እንደሚያስተናግድ የሚጠበቀው የአፍሪካ ፋሽን ሳምንት ቀሪው ዓለም በቴክስታይል ጨርቃጨርቅ እና በቆዳ ምርት ኢንደስትሪ የደረሠበትን የቴክኖሎጂ ልህቀት ለመገንዘብ እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ASFW 2025 ከጨርቃ ጨርቅ እና ቆዳ አልባሳት እንዲሁም የቤት ማስጌጫ ዘርፎች፣ የጅምላ እና ችርቻሮ ሽያጭ ዓላማ ላላቸው ሁሉ ሁነኛ አማራጭ መሆኑ ተገልጿል።

የASFW መስራች የሆኑት አቶ እስክንድር ነጋሲ ይህ ኤግዚቢሽን ለገበያ ትስስር ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን ከጅምራችን አንስቶ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥረናል ብለዋል።

በኤግዚቢሽኑ ላይ ለመታደም ከፈለጉ ዛሬን አንስቶ ለተከታታይ አራት ቀናት በሮች ክፍት ናቸው ተብሏል።

     | ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቀይ ባህርን በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሀሳብ የኢትዮጵያን ዘላቂ ህልውና የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊና ኢኮኖሚያዊ እ...
30/10/2025



| ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቀይ ባህርን በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሀሳብ የኢትዮጵያን ዘላቂ ህልውና የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ነው። ይህን መሰረታዊ ሀቅ በተለያዩ መመዘኛዎች ለማሳየት እሞክራለሁ :-

የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ ግዴታ፦ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት በፍጥነት እያደገች ያለች ሀገር ናት።የዓለም አቀፉ የንግድና ልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) መረጃ እንደሚያሳየው፣ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት (Landlocked Countries) ከባህር በር ካላቸው ሀገራት በአማካይ ሁለት እጥፍ የበለጠ የትራንስፖርት ወጪ ይሸከማሉ። ይህም የሀገሪቱን ምርት ተወዳዳሪነት በመቀነስ፣ የዋጋ ግሽበትን በማባባስ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ይገድባል። ለአንድ ትልቅ ኢኮኖሚ የባህር በር ወሳኝ መሠረታዊ መብት ነው።

ጂኦ-ፖለቲካዊ እና የንግድ ደህንነት፦የቀይ ባህር መስመር ለዓለም ንግድ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ደህንነት ከሌሎች ሀገራት ወደቦች ጋር መያያዝ በፖለቲካዊ እና ሎጂስቲካዊ ውሳኔዎች ላይ ጥገኛ ያደርጋታል።የራሷን የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የንግድ መስመሯን አደጋ የመከላከል እና የብሔራዊ ጥቅሟን የማስጠበቅ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አለው።

የታሪክና የህግ እውነታ፦ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የባህር በርዋን በህጋዊና ተቋማዊ ውሳኔ አለማጣቷ፣ ለጉዳዩ ፍትሃዊ እና ዘላቂ መፍትሄ የመፈለግን የታሪክ ግዴታ ያሳያል። የኢትዮጵያ ጥያቄ የጦርነት ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነትና የሰላማዊ ድርድር ነው።

ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሁሉን ስልት እና አቅም በማየት ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ ማሳካት አለባት። ይህ የህልውና ጥያቄ ከፖለቲካ በላይ፣ የኢኮኖሚ ፍትህና የልማት መብት ጉዳይ ነው ።

የዚህ ዘመን ትውልድ( Politically Active Person )እንዲሆን እና ትናንት በተለያየ ፖለቲካዊ ምክንያት እና ሁኔታ ለውይይት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይቀር ለማሰብ የተገታን ጉዳይ እንደገና ለንግግር መነሻ እና የብሔራዊ የልማት አጀንዳ አድርጎ ማቅረብ ኢትዮጵያ በቀጣይነት እና በዘላቂነት ለማሳካት ከምትፈልጋቸው የልማት ትልሞች መሰረት የሚጥል ነው ። የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል እና ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ እንዲህ አይነት ጉዳዬችን በድፍረት ወደ ፖለቲካ መድረክ መምጣታቸው ሊደነቅ ይገባል ።

#ኢትዮጵያ #ቀይባህር #ሰላምናልማት

በሀብታሙ ደባሱ አዲሱ

Oldies Night - Friday Bar and Restauranthave fun after work✌️✌️✌️✌️Address: Bole Behind Mega Bulg.Dress to impressFor Re...
30/10/2025

Oldies Night - Friday
Bar and Restaurant
have fun after work✌️✌️✌️✌️
Address: Bole Behind Mega Bulg.
Dress to impress
For Reservation
Call +251-968- 626262

የወርቃማው ፖሊስ ሙዚቀኞች3ኛ ዓመት - የምሥረታ በዓልአዲስ አበባ
30/10/2025

የወርቃማው ፖሊስ ሙዚቀኞች
3ኛ ዓመት - የምሥረታ በዓል
አዲስ አበባ

የዱባይ ስምምነት 🇦🇪 #ዜና | የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የተለያዩ የከተማ ማልማት ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የዱባይ ስምምነት መፈራረማቸውን ከንቲባ ከድር ጁሀር አስ...
30/10/2025

የዱባይ ስምምነት 🇦🇪

#ዜና | የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የተለያዩ የከተማ ማልማት ሥራዎች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የዱባይ ስምምነት መፈራረማቸውን ከንቲባ ከድር ጁሀር አስታወቁ

የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣የከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ፥ የከተማ አመራር ፣ የኢኮኖሚ አስተዳደር፥የኑሮ ጥራት እንዲሁም የአካባቢ መፍትሄዎች እና የከተማ መልሶ ማቋቋም ላይ በጋራ ትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የዱባይ ስምምነት መፈራረማቸውን ከንቲባ ከድር ጁሀር አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት በ15ኛው እስያ ፓስፊክ የከተሞች ጉባኤ እና የከንቲባዎች ፎረም ላይ በነበራቸው ተሳትፎ፥ ለድሬዳዋ አስተዳደር ቀጣይ የእድገት ጉዞ በእጅጉ የሚያግዙ ጥሩ ተሞክሮዎችን አግኝተናል ብለዋል ።

በዱባይ ኤክስፖ ሲቲ የተካሄደው ይህ የ2025ቱ ጉባኤ በመካከለኛው ምስራቅ፣ በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ እና ሌሎች አካባቢዎች የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎችን ለሚፈልጉ ከተሞች ዘለቄታዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ከ350 በላይ ከተሞች የተውጣጡ ከ150 የሚበልጡ ከንቲባዎች እና ተወካዮች በተሳተፉበት በዚህ ታላቅ መድረክ፥ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና የከተማ የወደፊት ዕጣ ፈንታ፥ የከተማ አመራር እና የኢኮኖሚ አስተዳደር፥ የኑሮ ጥራት እንዲሁም የአካባቢ መፍትሄዎች እና የከተማ መልሶ ማቋቋም ላይ በጋራ ትብብር መስራት የሚያስችለንን የዱባይ ስምምነት ፈርመናል ሲሉ ከንቲባው ስምምነት መፈራረማቸውን አስታውቀዋል። #

ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ ተከፈተ  | የእንስሳት ልማትና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ተከፈተ።ከ5 ሺህ ...
30/10/2025

ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች የተሳተፉበት አውደ ርዕይ ተከፈተ

| የእንስሳት ልማትና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ ተከፈተ።

ከ5 ሺህ በላይ የምስራቅ አፍሪካና ዓለም አቀፍ ሀገራት ጎብኚዎች የሚሳተፉበት የእንስሳት ልማትና የእንስሳት ተዋጽዖ ላይ ያተኮረ አውደ ርዕይ በሚሊኒየም አደራሽ ተከፍቷል።

ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው አውደ ርዕይና ጉባኤ ከ14 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ የእንስሳት ሃብት ዘርፍ ተዋናዮች፣ የሀገራት አምባሳደሮችና የዘርፉ ባለሙያዎችም ይሳተፉበታል።

ሁሉን አቀፍ የእንስሳት እርባታ ቴክኖሎጂ፣ ግብዓትና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት የሚያደርገው አውደ ርዕይ፤ የእንስሳት ሀብት የገበያ ሰንሰለቶችን እና የኢንቨስትመንት እድሎች ለማስተዋወቅም የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም በዘርፉ ውጤታማ ከሆኑ ሀገራት ልምድ ለመለዋወጥና ተሞክሯቸውን ለመቅስም እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

መንግስት በሰጠው ትኩረትና በሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ የአራት ዓመት ፕሮግራም የወተት፣ የእንቁላል፣ የዶሮ ስጋ እና የማር ምርቶችን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ግብ አስቀምጦ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ይህ አዉደ ርዕይ በእንስሳት መኖ፣ የእንስሳት ጤና፣ የዶሮ እርባታ ፣ በወተት፣ በስጋ እና እንቁላል እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ዘርፎች ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነም ሰምተናል።

በተያያዘም 10ኛው የአፍሪካ የእንስሳት እርባታ ኤግዚቢሽንና ኮንግረስ የአሳ ሀብት፣ የንብ እርባታና የባዮ ኢነርጂ ዘርፍ አውደ ርዕይ እንደሚኖርም ተገልጿል።

ለ3ቀናት በሚካሄደው ዓውደ ርዕይና ጉባኤ አጠቃላይ መሰረታቸውን በኢትዮጵያ፣ቻይና፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ታንዛኒያ፣ ግብጽ፣ ጣሊያን፣ ብራዚል፣ ኬኒያ፣ ኔዘርላንድስ፣ ቱርክ እና ሶሪያ ያደረጉ አለምአቀፍ የዘርፉ መሪዎች እና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንደሚገኙም ተገልጿል።

ኤክስፖዉ ከጥቅምት 20 እስከ 22 ለሶስት ቀናት በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድም ተገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ፈርስት አዲስ ኢንቨስችመንት ባንክ ወደ ገበያ መግባቱን አበሰረ  | ኢትዮጵያ  ከአፍሪካ ስድስት ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን፤ በአጠቃላይም ከ 2.2 ሚሊዮን በላይ የንግ...
30/10/2025

ፈርስት አዲስ ኢንቨስችመንት ባንክ ወደ ገበያ መግባቱን አበሰረ

| ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ስድስት ትልቅ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገሮች ውስጥ አንዷ ስትሆን፤ በአጠቃላይም ከ 2.2 ሚሊዮን በላይ የንግድ ተቋማት እና ወደ 32 የሚጠጉ የንግድ እና የ ልማት ባንኮች አሏት።

ሆኖም ግን እንደ ሃገር በፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትም ሆነ በካፒታል ገበያ እድገት ገና ብዙ መንገድ ይቀራታል።

ማህበረሰቡም ከመሰረታዊ የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት ዉጪ የተጨማሪ የፋይናንስ አገልግሎቶች፣ ለምሳሌ የግለሰብ ኢንቨስትመንት አካዉንቶችን የመከፈት እና የመጠቀም እድል አልነበረዉም።

የካፒታል ገበያን ማስፋፋት እና ማጠናከር የኢኮኖሚውን ዕድገት ለማስቀጠል ብሎም የዜጎችን ተጠቃሚነት ከማስፋት አንጻር አስትማማኝ፤ ቀልጣፋ እና ተደራሽ የሆነ የካፒታል ገበያ ስርዓት አስፈላጊ ነው። ካፒታልን ልከ እንደ አንዱ የምርት ግብአት (Factor of Production) አድርጎ ማየት ይቻላል፡፡

በአፍሪካ ዉስጥ ወደ 29 የሚጠጉ አገሮች ከ 35 በላይ የሰነደ ሙዐለ ንዋይ ገበያዎች ሲገኙ በኢትዮጲያም በቅርቡ መንግስት እየተገበረ ካለው የኢካኖሚ የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ማሻሽያዎች አንዱ ካፒታል ገበያ ሥርዓቱን የሚቆጣጠር አካል (Ethiopian Capital Market Authority) እንዲሁም የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) እንዲቋቋሙ ማድረጉ ነው፡፡

ይህንንም ተከትሎ የኢ/ካ/ገ/ባ በካፒታል ገበያ ውስጥ ተሰማርተው አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ብቃት በማጣራት እና በማረጋገጥ በመመሪያ ቁጥር 980/2016 አማካኝነት ፈቃድ እየሰጠ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ፈርስት አዲስ ኢንቨስትመንት ባንከ የመጀመሪያው ኢንዲፔንደንት ኢንቨስትመንት ባንክ በመሆን ፈቃዱን ጥቅምት 20, 2018 ዓ.ም ተቀብሎ ሌሎች የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ተቀላቅሏል።

ባንኩ ፍላጎት ተኮር የሆኑ የኢንቨስትመንት መፍትሄዎችን ለግለሰቦች፣ ለድርጅቶች እና ለመንግስት በማቅረብ የካፒታል ተደራሽነትን ማጎልበት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለማምጣት ይሰራል ተብሏል።

የባንኩ ቦርድ አባላት እና ባለሙያዎቹ በኢትዮጵያ እና በተለያዩ የውጪ ሀገራት የፋይናንስ ፣ የኢኮኖሚ ፣ የሕግ እና የልማት ዘርፍ ውስጥ ከ20 ዓመት በላይ ልምድ ያካበቱ እና በብቃት ያገለገሉ ናቸው ተብሏል።

በኢትዮጵያ በየሰአቱ 25 ያህል ዜጎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህይወታቸው ያልፋል(CORHA)  | ይህ የሰማነው የሲቪል ማህበራት የመራቢያ ጤና ማህበራት ጥምረት (CORHA)፣ የኢትዮጵያ የል...
30/10/2025

በኢትዮጵያ በየሰአቱ 25 ያህል ዜጎች ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ህይወታቸው ያልፋል(CORHA)

| ይህ የሰማነው የሲቪል ማህበራት የመራቢያ ጤና ማህበራት ጥምረት (CORHA)፣ የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣ የኢትዮጵያ የስኳር በሽታ ማህበር እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ማህበር የታሸጉ ምግቦችን ለመከላከል በተዘጋጀው አዋጅ ዙርያ በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።

የጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ቁጥጥር አዋጅ እንዲጸድቅ የሲቪል ማህበረሰቡ ከፍተኛ ድጋፍ ሰጠ

በኢትዮጵያ ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ የሚያስከትለው የጤና ቀውስ እየተባባሰ በመምጣቱ፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ላይ ቁጥጥር የሚያደርገው አዋጅ በጠንካራ ይዘት እንዲጸድቅ ጠንካራ ድጋፋቸውን አሳውቀዋል።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአሁኑ ወቅት በአገር አቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱ ሞት ውስጥ ከግማሽ በላይ (52%) የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ።

በየሰዓቱ፣ ወደ 25 የሚገመቱ ኢትዮጵያውያን በስኳር በሽታ፣ በኩላሊት፣ በጉበት እና በልብና የደም ዝውውር በሽታዎች ምክንያት ህይወታቸውን ያጣሉ።

የተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ኢኮኖሚያዊ ሸክም ከባድ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስትን በየዓመቱ 31.3 ቢሊዮን ብር እንደሚያስወጣ ይገመታል።

ይህ አሳሳቢ ሁኔታ የሀገሪቱን የህዝብ ጤና እና የኢኮኖሚ የወደፊት ዕጣ አደጋ ላይ ከመጣሉ በፊት 'የጤናማ ያልሆነ አመጋገብ ቁጥጥር አዋጅ' በአስቸኳይ መጽደቅ እንዳለበት የሲቪል ማህበራት ጥምረት ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ የምግብ አቅርቦት ሁኔታ በፍጥነት እየተለወጠ፣ በፋብሪካ የተዘጋጁ ምግቦች በስፋት እየተበራከቱ ነው።

ዓለም አቀፍ የምግብ ኩባንያዎች ጤናማ ያልሆኑ ምርቶቻቸውን በተለይም ለህጻናት በኃይል እያስተዋወቁ ይገኛሉ።

የሲቪል ማህበራት የመራቢያ ጤና ማህበራት ጥምረት (CORHA)፣ የኢትዮጵያ የልብ ማህበር፣ የኢትዮጵያ የስኳር በሽታ ማህበር እና የኢትዮጵያ የኩላሊት ማህበር የአዋጁ የመጨረሻ ረቂቅ የሚከተሉትን ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎች እንዲያካትት አጥብቀው አሳስበዋል፡፡

ከእነዚህም መካከል ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ምክረ ሃሳብ ጋር በሚስማማ መልኩ የኢንዱስትሪ ትራንስ-ፋቶችን ማስቀረት እንዲሁም ሸማቾች ስለ ምግቦች የንጥረ ነገር ይዘት (ስኳር፣ ጨው፣ ስብ) ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችል መረጃ እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል፡፡

ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ለህጻናት እንዳይተዋወቁ ሙሉ በሙሉ መከልከል እና ጠንካራ የቁጥጥር ስልቶችን መዘርጋት እንደሚያስፈልግ የተመላከተ ሲሆን፤ የመንግስት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች የጤና መስፈርቶችን የሚያሟሉ እና ከአገር ውስጥ የሚመነጩ የተመጣጠኑ ምግቦችን ብቻ እንዲያቀርቡ ማድረግ ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

የተጠቀሱት ማህበራት አዋጁ እንዲጸድቅ በሚያቀርቡት ጥሪ፣ የፖሊሲ አውጪዎች፣ የህግ አውጭዎች፣ ሚዲያዎች እና የሲቪል ማህበረሰብ አባላት ሁሉ ለጋራ ጤንነት እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሁለቱም ብሔራዊ ቡድን ከ123ሚሊዮን ወጪ አዉጥቻለሁ አለ   | የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ እያካሄ...
30/10/2025

የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሁለቱም ብሔራዊ ቡድን ከ123ሚሊዮን ወጪ አዉጥቻለሁ አለ

| የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤዉን በአፍሪካ ኢኮኖሚክ አዳራሽ እያካሄደ የሚገኝ ሲሆን በ2017 በጀት አመት ፌዴሬሽኑ ለወንዶች ብሔራዊ ቡድን ከ91ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ለስሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከ32 ሚሊዮን ብር በላይ በድምሩ ፌዴሬሽኑ ከ123 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንዳደረገ በቀረበዉ የፋይናንስ ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል።

የኢትዮጲያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለሁለቱ ብሔራዊ ቡድን ይህን ያክል ወጪ ለማዉጣቱ ዋና ምክንያት የሜዳ ዕጦት እንደሆነ ሲገለፅ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑን የፋይናንስ ቀዉስ ዉስጥ እየከተተዉ ነዉም ተብሏል ሲል ብስራት ኤፍ ኤም ዘግቧል።

የዛሬ 40 ዓመት አንደኛ ክፍል ስንገባ ስም የምንጠራበትን ሮስተር አገኘሁት                      ከዕዝራ እጅጉ( ተወዳጅ ሚድያ)   | እኔ ዕዝራ እጅጉ እና 69 የአንደኛ ክፍል ...
30/10/2025

የዛሬ 40 ዓመት አንደኛ ክፍል ስንገባ ስም የምንጠራበትን ሮስተር አገኘሁት

ከዕዝራ እጅጉ( ተወዳጅ ሚድያ)

| እኔ ዕዝራ እጅጉ እና 69 የአንደኛ ክፍል ጓደኞቼ ስማችን የሚጠራበትን መዝገብ ከሰሞኑ ስመለከት እየተገረምኩና በትዝታ እየነጎድኩ ነበር።

ጊዜው 1978 ዓ.ም ደርግ 10ኛውን የአብዮት በዓል ባከበረ በአመቱ ነበር።በወቅቱ 6 ዓመቴን ካከበርኩ 6 ወሬ ነበር። ጥቅምት 1978።አንደኛ ቢ፣ ቦሌ ህብረተሰብ ፣ የክፍል ኃላፊ መምህር በለጠ አወቀ።ያኔ በክፍላችን እነማን እንደነበሩ ዝርዝሩ ላይ ሳነብ ብዙ ልጆች ታወሱኝ። ለካ ስም ሲጠራ የሆነ ትውስ የሚለን ነገር አለ።

ለማንኛውም አንደኛ ክፍል ለኛ የትምህርት መጀመሪያ ብቻ ሳይሆን ከተማሪ ጋር መላመድን አንድ ያልንበት ዘመን ነበር። መምህራችን ቲቸር በለጠ ዐወቀ ፀጉራቸው ሉጫ ነበር። እንደሰማሁት ትምህርት ሚኒስቴር ከትልቅ የኃላፊነት ቦታ ለቀው ጡረታ ሲወጡ ነው እኛ ጋር በእንግሊዝኛ አስተማሪነት የተቀጠሩት። ረባሾችን የሚመዘግቡ የክፍል አለቆች ደግሞ ኢሽራቃ አህመድና ሲሞኒታ ጌታቸው ነበሩ። ኢሽራቃ ጠይም ስትሆን ሲሞኒታ ደግሞ የጣሊያን ክልስ ነበረች።

ሁለቱም ተደምረው እንዴት ያስፈራሩን እንደነበር አልዘነጋውም። አስተማሪ ሁሉ እየመሰሉን በፍርሀት እንርድ ነበር። እና ወደ ስም መጥሪያ መዝገቡ ስመጣ መዝገቡ ስም መጥሪያ ብቻ ሳይሆን ዓመታዊ ሰርተፊኬት ለማዘጋጀት የሚረዳ ሮስተር ነበር። በዓመት ውስጥ ስንት ቀን እንደቀረን፣ አንደኛ ክፍል ስንገባ ዕድሜያችን ስንት እንደነበር፣ ፀባያችን በA በ B,እና በC ሲገለፅ እናያለን። ባለ ምርጥ ፀባዮች "ኤ "ሲያገኙ በጥባጩ ደግሞ "ሲ "ን ይከናነባል። "ሲ "እንኳን ያለ አይመስለኝም። በዓመት ውስጥ ያገኘነው ውጤትም በአንደኛ ሴሚስተር፣በሁለተኛ ተብሎ ከእነ ጭማቂው ወረቀቱ ላይ ሰፍሯል።በዛን ወቅት አንደኛ ክፍል 11 ትምህርት እንማር እንደነበር ሮስተሩን ከማየት መረዳት ይቻላል።እነርሱም ፦ አማርኛ፣እንግሊዝኛ፣ሒሳብ፣ህብረተሰብ፣ሳይንስ፣ እርሻ፣ባልትና፣ስዕል፣ስፖርት፣ሙዚቃ፣እና እጅ ሥራ ናቸው።መቼም ሁላችሁም ትዝታ ውስጥ እንደገባችሁ እገምታለሁ።11 ደብተር ከነ መፅሐፍ ይዞ መጓዝ ግዴታችን ነበር።

ከክፍላችን በአንደኛ ሴሚስተር አንደኛ የወጣው ጥበበ ሰሎሞን አላምረው ሲሆን አሁን በአሜሪካ በምህንድስና የራሱን ተቋም ከፍቷል። ሁለተኛ የወጣው ደግሞ የሀያሲው የሥዩም ወልዴ የበኩር ልጅ ራምሴ ስዩም ወልዴ ነው። ራምስ በአሁኑ ሰዓት በሜካኒካል ምህንድስና ዘርፍ ተሠማርቶ ይገኛል።ሦስተኛ የወጣችው ደግሞ ብሌን ማንደፍሮ ስትሆን ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ ተማሪ ቤቱን ለቃ ወጥታለች።

ሁለተኛ ሴሚስተር ላይ ራምሴ ጥበበን ገልብጦ አንደኛ ሲወጣ ዮናታን ታፈሰ ደግሞ ከ24ኛ በአንድ ጊዜ ሁለተኛ ሆነ። አንደኛ ሴሚስተር አንደኛ የነበረው ጥቤ 3ኛ ደረጃን ያዘ። የክፍል አለቃችን ኢሽራቃ አህመድ ደግሞ አራተኛ ሆነች- አጫሎ ኩማ በ5ኛነት ተከተላት። አጫሎ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ቅዱስ ዮሴፍ የተማረ ጓደኛችን ነው። 6ኛ ሀውልቲ ገብረእግዚአብሔር ፣7ኛ ቁምላቸው መቻል(ኢጣሊያ ነው)፣8ኛ የክፍል አለቃ ሲሞኒታ ጌታቸው፣9ኛ የመዝሙር አቀናባሪው ንፁህ ይልማ 10ኛ ሔኖክ ዓለም ነበሩ። ከ1-10 በአንደኛ ሴሚስተር የአንደኛ ክፍል የክፍላችን ጎበዝ ተማሪዎች እነዚህ እንደነበሩ የዛሬ 40 ዓመት የተሰነደው ሮስተር ይመሰክራል።

ከ10ሩ ውስጥ ጥበበን፣ዮናታንን፣ራምሴን፣ንፁህን፣ሔኖክ ዓለምን፣አጫሎን ላገኛቸው ስለምችል ተጨማሪ ትዝታ እንዲያወጉኝ አደርጋለሁ። ቁምላቸው መቻል፣ ብሌን ማንደፍሮ፣ሀውልቲ ገብረእግዚአብሔር እና ሲሞኒታ ያሉበትን የሚያውቅ ይጠቁም።

በነገራችን ላይ ይህን ፅሁፍ በግሩፖች እና ማህበራዊ ገጼ ላይ ፖስት ካደረግኩ በኃላ ብሌን ማንደፍሮ ተገኝታለች። ዕድሜ ለንፁህ ይልማ። በአጋጣሚ በሥራ በስልክ ተዋውቀን ነበር- ከ10 ቀን በፊት። የግጥምጥሞሽ ነገር ድንቅ ብሎኛል። አንደኛ ክፍል 3ኛ የወጣችው ብሌን ማንደፍሮ አንድ ሴሚስተር ቦሌ ኮምዩኒቲ ተምራ በቀጣይ መገኛዋ ናዝሬት ስኩል ሆነ። ከዛም ሀይስኩል ሳንፎርድ ተምራ ዲግሪዋ አሜሪካ ሆነ። ከደቂቃዎች በፊት ከብሌን ጋር ብዙ ተጨዋወትን። በጣም መልካም ፀባይ ያላት ቀና ሴት ናት። ስለ ብሌን ወደፊት በዚህ ገፅ የምለው ይኖራል።

በሰነድ አያያዜ ላይ የበለጠ ዕምነት እንዲያድርባችሁ ስማችሁ ያለበትን ወረቀት ውጤታችሁን ብቻ ሸፍኜ ፖስት አድርጌዋለሁ። ስንት ቀን እንደቀራችሁ፣ፀባያችሁን ያኔ ምን እንደነበር 40 ዓመት ወደ ኃላ ተመልሳችሁ መገምገም ትችላላችሁ ። የእኔን በተመለከተ ግን የደነቀኝኝ ላካፍል።

እኔ አንደኛ ክፍል አማርኛ ከ100፣ 30 ማግኘቴን ሮስተሩ ላይ ስመለከት ድንቅ አለኝ። እንግሊዝኛ ደግሞ 92 ማለት ነው። እንግዲህ በአማርኛ 20 መፅሐፍ ያሳተምኩት እኔ ከ40 ዓመት በፊት አማርኛ ራሴን አዙሮት እንደነበር በቲቸር በለጠ አወቀ የተሰናዳው ሮስተር ይናገራል። እንግሊዝኛ በምን ተአምር እንደቀለለኝም ሚስጥር ሆኖብኛል።

እናላችሁ ትዝታ ጥሩ ነው። መንፈስን አድሶ ያሞቃል። ትዝታ ደግ ነው። መልካም ቀኖችን እያስታወሰ መንፈስን ያፍታታል። ወደ ኃላም መልሶ የረሳነውን ሁሉ ዳግም ትዝታ ይቀሰቅስብናልደ እርስዎስ የአንደኛ ክፍል ትዝታዎን ከሰነድ ጋር አያይዘው ዕውነተኛ ታሪክ ሊያካፍሉን ይችላሉ ?

Address

Gabon Avenue (Washington DC Square/Sterling Buildg)
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን):

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

GETU TEMESGEN - (ጌጡ ተመስገን)

ጌጡ ተመስገን ውልደቱና እድገቱ አዲስ አበባ ነው። በጋዜጠኝነት ሙያው፤ ለአገር እና ለሕዝብ በሠራቸው አይረሴ ሥራዎቹ በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል። የፈረንሳይ ቴሌቪዥን ባሰባሰበው የተመልካቾች ምዘና መሠረት ‹‹ባለንሥሩ ጋዜጠኛ ~ A Journalist with an eagle eye›› የሚል ስያሜ አግኝቷል።

Getu Temesgen was born and raised in Addis Ababa. As a result of his unforgettable journalistic works/TV productions, he has won various recognitions. He was named “The Journalist with an eagle eye” in an audience poll conducted by French TV.

ሦስት ሥራዎቹም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ቀርበውለታል። በአዘጋጁቹ ግብዣ አውሮፓ ፤ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ፈረንሳይና ቤልጅየም ተጉዞ፤ ትምህርታዊ ጉብኝት በማድረግ አገር ቤት ተመልሷል።

His three TV productions were also presented for European audience in French language and as a result was invited by the producers to visit France, Germany, Italy and Belgium.”