Yekatit 12 Hospital Medical College

Yekatit 12 Hospital Medical College Yekatit 12 Hospital was founded in 1923 and one of the 1st modern hospitals in the country.

Yekatit 12 Hospital started providing medical education in 2011 and changed its name to Yekatit 12 Hospital Medical College.

የከንቲባ አዳነች አቤቤ  የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት :- ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰ...
11/04/2026

የከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሣኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት :-

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

የትንሣኤ በዓል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ መዳን ያለውን ፍቅር እስከ መስቀል ሞት የገለጸበትና የሞት ድል የተበሰረበት ታላቅ ዕለት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በታላቅ ፍቅር፣ በትሕትና እና በመተሳሰብ ሊሆን ይገባል።

ድጋፍ ለሚሹ ወገኖቻችን ያለንን አጋርነት በተግባር የምንገልጽበት፣ አንዳችን ለሌላችን የደስታ፣ የሰላም እና የአብሮነት ምክንያት የምንሆንበት በዓል እንዲሆንልን እመኛለሁ።

መልካም በዓል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገ...
11/04/2026

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!

የትንሣኤ በዓል በክርስቲያኖች ዘንድ ልዩ ቦታ ያለው በዓል ነው። ሞት የተሻረበትና ሕይወት ዋስትና ያገኘበት ነው። ከሞት ባሻገር ሕይወት፣ ከመቃብር ባሻገር ትንሣኤ መኖሩ የታወጀበት ነው። ሞት መጨረሻ መቃብር መዳረሻ አለመሆናቸው የተረጋገጠበት ነው። በአዳም ምክንያት ወደ ምድር የወረደው ሰው፣ በክርስቶስ ምክንያት ወደላይ የወጣበት ነው።

የዘንድሮውን ትንሣኤ የምናከብረው ሀገራችን ኢትዮጵያ በሚያልፍ ፈተና ውስጥ እንዳለች እያሰብን ነው። መንገዳችን ረጅም፣ ጉዟችን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። ብርሃን እንዳናይ የሚጋርዱ፣ በጥልቁ ጨለማ ጠፍተን እንድንቀር አሥረው ለመያዝ የሚሞክሩ ወጥመዶች ብዙ ናቸው። ወደ ተስፋ ምድር እንዳንሻገር የሚጎትቱ ሰበቦች ሞልተዋል። ዳሩ ግን ከሕማማቱ ወዲያ ትንሣኤ፣ ከዕንቅፋቱ ባሻገር ስኬት እንደሚጠብቀን አምነን እንታገላለን።

በትንሣኤው ዋዜማ - ርግጠኞች፣ ተስፈኞች፣ ተስፋ ቆራጮች፣ ወሬኞች፣ ተስፋ አስቆራጮች፣ ተጠራጣሪዎች ነበሩ። ርግጠኞቹ የሕማማቱ ፈተና እንደሚያልፍ ርግጠኞች ነበሩ። የዕለተ ስቅለት መከራ፣ለዕለተ ትንሣኤ ዋዜማ ለመሆኑ ርግጠኞች ነበሩ። የድንጋዩ በር፣ የበሩ ማኅተም እና የመቃብሩ ጠባቂዎች ትንሣኤውን እንደማያስቀሩት ርግጠኞች ነበሩ። የሚናፈሰው ወሬ እና የሚሠራጨው አሉባልታ እድሜው አጭር መሆኑን ርግጠኞች ነበሩ። ርግጠኞችም ስለሆኑ መሥዋዕትነትን ለመክፈል ዝግጁዎች ነበሩ። እውነቱን ለመመስከር ቆራጦች ነበሩ። በመስቀሉ ሥር ለመገኘት ደፋሮች ነበሩ።

ተስፈኞቹ የርግጠኞቹን ያህል ሳያዩ የሚያምኑ አልነበሩም። ግን አንዳች መልካም ነገር ይጠብቁ ነበር። የተሰጠውን ትምህርት፣ የተደረገውን ተአምራት ሰምተዋል፤ አይተዋል፤ አንዳች ነገርም ጠብቀዋል። ነገር ግን ተገቢውን መሥዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁዎች አልነበሩም። እውነትን ለመድፈር ቆራጦች አልነበሩም። ሐሰቱን ለመጋፈጥ ዐቅም አላገኙም። ቢያንስ ግን አንደበታቸውን ከክፉ ከልክለዋል።

ተጠራጣሪዎች አጥር ላይ የነበሩ ናቸው። በጥብርያዶስ ይበላሉ፣ በጎልጎታ ይክዳሉ። በሆሳዕና ይዘምራሉ፣ በሊቶስጥራ ይሸሻሉ፡፡ ተአምር ለማየት ይመጣሉ፣መከራ ለማየት ይሳቀቃሉ፡፡ ከደስታው አውጡልኝ፣ ከመከራው ጦመኛ ነኝ የሚሉ ናቸው።

ተስፋ ቆራጮች በሚያዩትና በሚሰሙት ቶሎ የሚወሰዱ ናቸው። በእውነትና በሐሰት፣ በፍርሃትና በጽናት መካከል ያለው ድንበር የጠፋባቸው ናቸው። ሕማማቱ ሲመጣ በቶሎ ወደ ትዝታ ገቡ። ሁሉንም ነገር የትናንት ታሪክ ብቻ አድርገው ወሰዱት። ሁሉንም ነገር “ልጡ የተራሰ፣ መቃብሩ የተማሰ” አድርገው ቆጠሩት። ከግራ ከቀኝ የሚሰሙት አሉባልታ፣ ከፊት ከኋላ የሚመጣው ጫጫታ፤ ከወዲህ ከወዲያ የሚማጣው እሳት፣ ከዚህም ከዚያም የሚያዩት መዓት አስፈራቸው። ነገን አስረሳቸው። በዚህ የተነሣ ተስፋ ቆርጠው ወደ ኋላ ተመለሱ።

ወሬኞች ድሮም ወሬ ስቧቸው የመጡ ናቸው። ምን አለ ምን ተባለ ብለው የተሰባሰቡ ናቸው። የሰሙትንም ያልሰሙትንም፤ የሚያውቁትንም የማያውቁትንም፤ እውነቱንም ሐሰቱንም እያደባለቁ ኢየሩሳሌምን በወሬ ሞሏት። ቢያንስ ከትንሣኤው 15 ዓመት በኋላ ወንጌሉን የጻፈው ማቴዎስ፣ እስከዚያ ዘመን ድረስ ወሬው ብዙ ተቀባይ እንደነበረው ገልጧል።

ተስፋ አስቆራጮች ዓላማቸው ሰውን ሁሉ ከትንሣኤ መንገድ ማራቅ ነበር። እነርሱም አይሄዱ፣ ሰውም አያስኬዱ። ከመጀመሪያው አልተቀበሉትም፤ በኋላም አልፈለጉትም። ብዙ ሰዎች እንደተከተሉት ሲያውቁ ደግሞ ቅናት አቃጠላቸው፤ ክፋት አንገበገባቸው። ክርስቶስን ከሰሱ፤ ራሳቸው ምስክር ሆኑ፤ በመጨረሻም ራሳቸው ፈረዱ። መቃብሩን ዘጉ፤ ጠባቂ አስቀመጡ። በማኅተም አሸጉ። ነገር፣ ያለቀና የተቆረጠ መሰላቸው።

የትንሣኤ በዓል የእነዚህን ሁሉ እውነተኛ ማንነት የገለጠ ነው። ርግጠኞች የቆራጥነታቸው ውጤት በትንሣኤ አገኙ። ተስፈኞች እንዲህ ለሚያልፍ ጊዜ ባለመጽናታቸው አዘኑ። ተስፋ ቆራጮች አሻግሮ ማየት አቅቷቸው ከቦታቸው በመጥፋታቸው ተፀፀቱ። ወሬኞች በትንሣኤው እውነት የተነሣ ያ ሁሉ ወሬ እንደ ናቡከደነፆር ሐውልት ሲፈረካከስ አዩት። ተስፋ አስቆራጮች የገደሉት ክርስቶስ ሲነሣ፣ የዘጉት መቃብር ሲከፈት፣ ያተሙት ማኅተም ሲቀደድ፣ የመደቧቸው ጠባቂዎች ሲሸሹ በዓይናቸው በብረቱ አዩ። ትንሣኤው የሚነገር ሐቅ፣ የሚታይ እውነት ሆነ። ተጠራጣሪዎች ግን አሁንም አጥራቸው ላይ ሆነው ከግራም ከቀኝም ሳይሆኑ ቀሩ።

የኢትዮጵያችንም ነገር እንዲሁ ነው። በኢትዮጵያ ለውጥ ርግጠኞች የሆኑት ዋጋ ይከፍላሉ፤ ርግጠኝነትን ፈርተው ተስፈኞች የሆኑት ቢያንስ አንደበታቸውን ከክፉ ይጠብቃሉ፡፡ ተስፋ ቆራጮች ነገን ማየት ስለሚሳናቸው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ወሬኞች አውርቶ አዳሪዎች በመሆናቸው የወሬ እንጀራ ይጋግራሉ። ተስፋ አስቆራጮች “ወተቱን አጥቁረው፣ ማሩን አምርረው” የዋሖችን አታለሏቸው፡፡ ተጠራጣሪዎች አንዴ ትኩስ አንዴ ቀዝቃዛ ሲሆኑ፣ ለብ ብለው ቀሩ።

ኢትዮጵያችን ግን ትንሣኤዋን እያየች ነው። መግነዙን ፈትታዋለች፣ መቃብሩን ከፍታዋለች፤ ማኅተሙን ቀዳዋለች። ወሬኞች ከመቃብር ጠባቂዎች ጋር ተማክረው የሚያወሩትን ወሬ የምትሰማበት ጆሮ የላትም። ትንሣኤዋን አይለውጠውምና። እሷ ከዚህ በኋላ የምትጠብቀው ዕርገትን ነው። የምትጓዘው ኃይል እንደሚወርድላት አረጋግጣ ነው። ወደኋላ መመለስ የለም። ሕማማት አልፏል፤ዓርብም አልፏል፤ ቅዳሜም አልፏል። ትንሣኤ መጥቷል። በትንሣኤ ሌሊት የተኙ አልሰሙ ይሆናል። በተስፋ አስቆራጮች ተታለው የሄዱ ዜናው አልደረሳቸው ይሆናል። ትንሣኤ ግን እውን ሆኗል።

ከቻላችሁ አጥር ላይ ያላችሁ ውረዱ። ተስፈኞች ርግጠኞች ሁኑ። ተጠራጣሪዎች እመኑ። ወሬኞች ከአፍ ወደ መዳፍ ተለወጡ። ምክንያቱም - ኢትዮጵያ ወደ ትንሣኤ ተቃርባለች።

የኢትዮጵያ ትንሣኤ ከሚበሰርባቸው ምዕራፎች አንዱ ግንቦት ላይ የሚካሄደው ምርጫ ነው። ትንሣኤን ያለ ሕማማት እንደማናስበው ሁሉ ዴሞክራሲንም ከውጣ ውረድ ነጥሎ ማየት አይቻልም። በዓለም ላይ በደልዳላ መንገድ ተጉዞ ዴሞክራሲን የገነባ ሀገር የለም። ዴሞክራሲና ብልጽግና ያለ ጽናት አይሳኩም። ከእኛ በፊት ዐመጻውን በትዕግሥት የመከቱ ተሻግረዋል፤ ሑካታውን በጽናት ያለፉ አሳክተዋል። ብንመኝም ፈተናውን አናስቀርም፤ መጽናት ግን እንችላለን። ከድህነት መውጫው ብርታታችን፣ ወደ ዴሞክራሲ መድረሻችው ትዕግሥታችን እንደሆነ አምነን ለኢትዮጵያ ትንሣኤ በሙሉ ልባችን እንትጋ!!

በድጋሚ መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የማኔጅሜንት አባላት እና ሰራተኞች የትንሳኤን በዓል አስመልክተው በተቋሙ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞች የበዓል ማዕድ በመጋራት አደረጉ።የካቲት 12...
09/04/2026

በየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የማኔጅሜንት አባላት እና ሰራተኞች የትንሳኤን በዓል አስመልክተው በተቋሙ ውስጥ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሰራተኞች የበዓል ማዕድ በመጋራት አደረጉ።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ ሚያዝያ 1/2018 ዓ.ም

ይህ ድጋፍ በተቋሙ ውስጥ ያለውን የመተሳሰብ እና የአብሮነት ባህል በግልጽ ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን፣ ሰራተኞች በበዓል ወቅት በደስታ እንዲያከብሩ የሚያግዝ አስፈላጊ ድጋፍ መሆኑ ተገልጿል። ተቋሙ ለሰራተኞቹ ያለውን አጋርነት በተግባር እየገለፀ መሆኑም ተጠቅሷል።

የተቋሙ ኃላፊዎች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ዓይነት ድጋፎች ለበዓላት ብቻ ሳይሆን በሌሎች ጊዜያትም መቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል።


በሌላ በኩል ድጋፉን ያገኙ ሰራተኞች በተቋሙ ኃላፊዎችና በሌሎች ሰራተኞች ላሳዩት አጋርነት እና ደግነት ከልብ አመስግነው፣ ይህ ድጋፍ ለእነርሱ ታላቅ መነሳሳት እና የሥራ መንፈስ መጨመር እንደሆነ ገልፀዋል።

ተቋሙ እንደሚያሳየው ይህ ዓይነት ተግባር የአብሮነትን መንፈስ በማጠናከር ብቻ ሳይሆን፣ በማህበረሰብ ውስጥም መልካም ምሳሌ የሚሆን ነው። ወደፊትም እንዲህ ያሉ የማህበራዊ ድጋፎች እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

International Pediatric Surgery Day Celebrated at Yekatit 12 Hospital Medical College📍Yekatit 12 Hospital Medical Colleg...
07/04/2026

International Pediatric Surgery Day Celebrated at Yekatit 12 Hospital Medical College

📍Yekatit 12 Hospital Medical College

📅Addis ababa April 7/2016

🌎"Bringing surgical care closer to every Ethiopian child"

Yekatit 12 Hospital Medical College proudly celebrated World Pediatric Surgery Day in a colorful and engaging program that brought together healthcare professionals and partners dedicated to improving surgical care for children.

The program was officially opened by the Yekatit 12 Hospital Medical College Provost, Dr. Anteneh Mitiku, who delivered welcoming remarks and emphasized the importance of strengthening pediatric surgical services and continuing to build capacity in child health care.

The event was successfully organized through the collaboration of Yekatit 12 Hospital Medical College, the Association of Ethiopian Pediatric Surgeons, and the Ministry of Health. Dr. Mekdelawit mesfin a Pediatric Surgeon, played a key role in the success of the program through her outstanding organization and coordination.

During the celebration: Professor Miliard Derbew, former President of the Pediatric Surgery Association, delivered an inspiring speech highlighting the importance of collaboration among health professionals and the need to expand pediatric surgical services to better serve children across the country.

Dr. Woubedil Kiflu, Pediatric Surgeon, provided a detailed overview of the Pediatric Surgery Association, explaining its mission, ongoing initiatives, and its role in supporting healthcare professionals and improving the quality of surgical care for children.

Dr. Addisu Andarge, Pediatric Surgeon, presented the significant five-year journey of pediatric surgery services at Yekatit 12 Hospital Medical College, showcasing key achievements, service improvements, and the growing impact of the department in saving lives and enhancing child health outcomes.

Together, we reaffirm our commitment to ensuring safe, timely, and quality surgical care for every child.

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

Pediatric surgery is more than an operation,  it is the difference between disability and ability, between illness and a...
04/04/2026

Pediatric surgery is more than an operation, it is the difference between disability and ability, between illness and a healthy future, between losing a child and saving a life. Every year, thousands of children require safe, timely surgical care, and together, we can make that care more accessible in Ethiopia.

The Association of Ethiopian Pediatric Surgeons warmly invites healthcare professionals, academic institutions, partners, and stakeholders to join us in celebrating World Pediatric Surgery Day at Yekatit 12 Hospital Medical College.

Join us as we come together to recognize the importance of pediatric surgical care and strengthen our shared commitment to improving surgical services for children across Ethiopia.

Theme: Bringing Surgical Care Closer to Every Ethiopian Child
Date: April 7, 2026
Time: 9:00 AM – 12:00 PM
Venue: Yekatit 12 Hospital Medical College

General Surgery graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026.
03/04/2026

General Surgery graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026.

Ob/gyn graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026.
03/04/2026

Ob/gyn graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026.

🩸 ደም በመለገስ ህይወትን እንታደግ! 🩸​የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በላብራቶሪና እና ማይክሮባዮሎጂ ክፍል አስተባባሪነት ያዘጋጁት ደም የመለገስ መርሃ ግብር በስኬት ተከናውኗል።​በ...
03/04/2026

🩸 ደም በመለገስ ህይወትን እንታደግ! 🩸
​የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በላብራቶሪና እና ማይክሮባዮሎጂ ክፍል አስተባባሪነት ያዘጋጁት ደም የመለገስ መርሃ ግብር በስኬት ተከናውኗል።

​በዚህ በጎ ተግባር ላይ በአጠቃላይ 22 ዩኒት ደም የተሰበሰበ ሲሆን ይህ ለወገን ደራሽነት የታየበት ተግባር ለብዙዎች ተስፋ የሚሆንና ህይወት የሚያድን ነው። በቅርቡ ለሚዘጋጀው ለዚህ ዝግጅት ላይ ሁሉም አካላት እንዲሳተፉ ጥሪ ተላልፏል።

📍 የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን

📅 መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
📍
📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE

​🔖 💛✨
#የካቲት12 #ደምልገሳ 💉✨

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እና በስዊድን ሀገር የሚገኝ ኢኤንቲ ፕላስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር  የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል። የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ ...
03/04/2026

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ እና በስዊድን ሀገር የሚገኝ ኢኤንቲ ፕላስ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነድ (MoU) ተፈራርመዋል።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ አዲስ አበባ መጋቢት/25/2018 ዓ.ም

በፕሮግራሙ ላይ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶ/ር አንተነህ ምትኩ እና የኢኤንቲ ፕላስ ተወካይ አቶ ዘውዱ መላኩ ሰነዱን በይፋ ተፈራርመዋል።

የዚህ የመግባቢያ ሰነድ ዋና ዓላማ በእውቀት ሽግግር፣ በህክምና መሳሪያ ድጋፍ እና በህክምና መማርና ማስተማር ክህሎት ማጠናከር ሲሆን ይህም ለታካሚዎች የሚሰጠውን የህክምና አገልግሎት ጥራት ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ዶ/ር አንተነህ ምትኩ እንደሰጡት አስተያየት
"ይህ ስምምነት ተቋማችን ከአለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመስራት የህክምና ጥራትን ለማሻሻል የምንወስደውን ቀጣይ እርምጃ ያመለክታል። በተለይም በእውቀት ልውውጥ እና በሙያ ክህሎት ልማት የሚደረገው ትብብር ለህብረተሰባችን የተሻለ እና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት ለማቅረብ ይረዳናል" ብለዋል።

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ከአጋሮቹ ጋር በመተባበር ለህብረተሰቡ የተሻለ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። 🌍

📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE/

🔖

Oral & Craniomaxillofacial surgeon  graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026
02/04/2026

Oral & Craniomaxillofacial surgeon graduates of Yekat 12 Hospital Medical College, 2026

🔵🧩 World Autism Awareness Day Observed at Yekatit 12 Hospital Medical CollegeYekatit 12 Hospital Medical College marked ...
02/04/2026

🔵🧩 World Autism Awareness Day Observed at Yekatit 12 Hospital Medical College

Yekatit 12 Hospital Medical College marked World Autism Awareness Day with a formal awareness initiative aimed at promoting understanding, early identification, and inclusive care for individuals with Autism Spectrum Disorder.

🧠 The observance highlighted autism as a complex neurodevelopmental condition that affects communication, behavior, and social interaction, requiring early diagnosis and multidisciplinary intervention.

👨‍⚕️ Health professionals emphasized the importance of:
Early screening and diagnosis
Family-centered care and support
Reducing stigma and misconceptions
Strengthening inclusive healthcare services

🏥 As a teaching and referral institution, Yekatit 12 Hospital Medical College reaffirmed its commitment to advancing pediatric and mental health services, enhancing professional capacity, and promoting community awareness on developmental conditions.

📢 The hospital calls upon the public and stakeholders to support inclusive environments and ensure access to appropriate care and education for children with autism.

🤝 This observance aligns with global efforts to foster acceptance, dignity, and equal opportunities for individuals living with autism.

📍 Yekatit 12 Hospital Medical College Communication

📅 April 2, 2026
📍
📌 Follow Us on Social Media
👉 Facebook:
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063650457050

👉 Telegram: Join Our Channel https://t.me/Y12HMCC

👉 Follow us on tiktok
https://vm.tiktok.com/ZMHWJyPGKQmQp-dftjE

🔖 💛✨

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yekatit 12 Hospital Medical College posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Yekatit 12 Hospital Medical College:

Share