09/11/2025
ራዲዮሎጂ ጥበብ ነው ፣ ፅድት ያለ ጥበብ ☢️🎭
ዛሬ ደሞ አለም አቀፍ የራዲዮሎጂ ቀን ነው። አምላክ ከአዕምሮ በላይ በሆነው ጥበቡ ያበጃጀውን የሰው ልጅ አካል ከውስጥ እስከ ውጭ በአይን ከሚታየው እስከማይታየው አብጠርጥረን የምናይበት ጥበብ።
የሰው ልጅ ከፅንሰቱ ጀምሮ እስኪወለድ ድረስ የዕድገት እና የሰውነት ለውጦችን የምንከታተልበት መነፅር
- ለሀኪሙ ጥርጣሬ ማረጋገጫ ሰጪ
- ለቀዶ ህክምና እስፔሻሊስቱ አስተማማኝ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ
- ለማህፀን እና ፅንስ እስፔሻሊስቱ ብርቱ አጋር
- ለተጨነቀች እናት እረፍት ሰጪ፣ የፅንሷን ሰለም መሆን አብሳሪ::
ጨረራን እንደ ጦር ፣ የድምፅ ሞገድን እንደ አጉይ መነፀር ፣ የመግነጢስ ኃይልን እና የራዲዮ ሞገድን እንደ ስንቅ በመጠቀም ይህን ድንቅ የህክምና ጥበብ የምንሰራ፣ የህክምና ራድዮሎጂ ባለሞያዎች ደሞ ዛሬ ቀናችን ነው 😊
In short, radiology professionals bridge technology and compassion, turning invisible energy into visible answers helping medicine see, decide, and heal with confidence.
መልካም አለም አቀፍ የራዲዮሎጂ ቀን ለሁላችን።
Happy world Radiography day. ☢️💪
Naol Geleta.
Medical Radiology Technologist , lecturer AMU
©Hakim
ጤና ይስጠን-Tena Yisten