የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር Mental Service Users' Association - Ethiopia

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር Mental Service Users' Association - Ethiopia

የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር Mental Service Users' Association - Ethiopia በአእምሮ ህመም ህክምና ላይ ባሉ ኢትዮጵያውያን የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡
Association of mental care users in Ethiopia

🧘‍♀️ The Art of Self-Care: Simple Practices for Inner Peace🧘‍♀️Self-care isn’t a luxury, it’s a necessity.🤩🧘‍♀️ራስን መንከባከ...
29/10/2025

🧘‍♀️ The Art of Self-Care: Simple Practices for Inner Peace

🧘‍♀️Self-care isn’t a luxury, it’s a necessity.🤩

🧘‍♀️ራስን መንከባከብ የቅንጦት ጉዳይ ሳይሆን መሰረታዊ ነገር ነው::🤩



👉Website :www.mhsua.org
👉Facebook: https://www.facebook.com/MentalSUA?mibextid=wwXIfr&mibextid=wwXIfr
👉Instagram: https://www.instagram.com/mhsua_eth?igsh=aXk5MjZmaHFxeGhl&utm_source=ig_contact_invite
👉Telegram : https://t.me/mhsua2023
👉youtube https://youtube.com/?si=rrVBTV45HEsmGEsU



26/10/2025

Lived experience drives innovation in peer-led crisis response, culturally rooted care, and rights-based advocacy.

24/10/2025
22/10/2025


21/10/2025

አህጉራዊ ተስፋ የተጣለበት ማዕከል
++++++++++++++

| ከዛሬ 40 ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ጎዳናዎች በብዙ ነዳያን የተሞሉ ነበሩ። በግቢው ውስጥ ከሰፈሩት ነዳያን መካከል አብዛኞቹ የአዕምሮ ሕሙማን መሆናቸው ደግሞ በራሱ ሌላ ተጨማሪ ችግር ሆነ።

አካባቢው በጩኸት መታወክ ጀመረ። ችግሩ መፍትሄ እንደሚያሻው ታምኖበት ለመፍትሄው ቅርብ ናቸው የተባሉት የዛን ጊዜው የአማኑኤል ሆስፒታል ዋና ዳይሬክተርና የአዕምሮ ሕክምና ባለሙያ የአሁኑ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተጠሩ።

ፕሮፌሰር መስፍንም በቦታው ደርሰው ሕሙማንን ከአጋሮቻቸው ጋር ለመርዳት ሞከሩ። በዚህ ወቅት ያዩት ነገር ግን ዛሬ ድረስ ከአዕምሯቸው አልጠፋም።

ሕሙማኑ የተለያየ አይነት ችግር ያለባቸው በመሆናቸው በእጅጉ ያስቸግራሉ ያሏቸውን ቀድመው ሕክምናውን ካደረጉና ከአረጋጉ በኋላ ነው በጭንቀትና በዝምታ ውስጥ ያሉትን ወደመርዳቱ የገቡት።

በዚህ ወቅት የተሸፈኑ ሰዎችም የዚህ ችግር ተጠቂ ናቸው ብለው አምነው ነበርና ወደ እነርሱ አመሩ። ሆኖም ያሰቡት ሳይሆን ያላሰቡት ነበር ገጠማቸው። ይህም ሰዎቹ ለመታከም ሳይሆን ለመቀበር የተዘጋጁ ነበሩ።

ይህንን አሳዛኝ ክስተት በዓይናቸው ያዩት ፕሮፌሰር መስፍን ችግሩ ቋሚ መፍትሄ እንደሚያሻው አመኑ።

ችግሩን ታሳቢ ባደረገ መልኩም ለመሥራት የዛሬውን የገፈርሳ የአዕምሮ ጤናና የሱስ ማገገሚያ ማዕከል በአማኑኤል ሆስፒታል ሥር ሆኖ ሥራ እንዲጀምር አስደረጉ።

የአዕምሮ ሕሙማንን በአንድ ላይ ማስቀመጥ ዜጎችን ማግለልና የተሻሉ አማራጮችን ማሳጣት እንደሆነ ያምናሉ ጥራት ያለው አገልግሎት ሊሰጥ በሚችል መንገድ እንዲሠራላቸው በማድረግ አገልግሎት እየሰጠ ዛሬ ላይ ደረሰ።

አሁን ማዕከሉ በርካታ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ከአዕምሮ ሕመም ሕክምና እስከ ሱስ ማገገሚያነት የሚደርሱ ሥራዎችን ያከናውናል። ከዚያም ተሻግሮ የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የአካል ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል።

በተጨማሪም በአዕምሮ ሕክምና ዙሪያ የተለያዩ ስልጠናዎችን ይሰጣል። ዛሬ ላይ ስያሜውን የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት የገፈርሳ የአእምሮ ጤና ማገገሚያ ማዕከል በሚል ይጠራል።

የአዕምሮ ጤና፣ የሱስ ማገገም ሕክምናንና የአካል ድጋፍ አገልግሎትን ለዜጎች ይሰጣል።

ትናንት ሲገነባ ለ250 ዜጎች ሕክምና ይሰጣል ተብሎ ቢታሰብም ዛሬ ላይ ከ400 በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ ህሙማንና በሱስ ችግር ፈተና ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ዘመኑን የሚመጥኑ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።

ተቋሙ አሁን ከዚያም ልቆ እንዲጓዝ የሚያስችለውን ዕድል አግኝቷል።

በሀገር ደረጃ የመጀመሪያ የሆነ የተቀናጀ አገልግሎት የሚሰጥበት ትልቅ ፕሮጀክት መተግበሪያ እንዲሆን መንግሥት 12 ቢሊዮን ብር ለመጀመሪያነት መድቦለት ግንባታው ተጀምሯል።

ይህ ደግሞ ለብዙዎች ተስፋ የጫረ እንደሆነና ድነው የራሳቸው ጌቶች እንዲሆኑ የሚያስችል ስለመሆኑ ፕሮፌሰር መስፍን ተናግረዋል።

በተለይም ለአዕምሮ ህሙማንና ሱስ ውስጥ ለገቡ ዜጎች እንዲሁም የአካል ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቀድሞ ደርሶ ተስፋቸውን የሚያለመልምላቸው እንደሚሆንም አስረድተዋል።


እንደዚህ ዓይነት በሕክምናው ዘርፍ በተለይም በአዕምሮ ጤና ላይ ሀገራዊ ፕሮጀክት ሆኖ እንዲሠራ መፈቀዱ ፋይዳው ዘርፈ ብዙ እንደሆነ ገልጸው፤ አሁን የተሰጠው ተስፋ የነበረ ተግባሩን አጠናክሮና የአገልግሎቱን ጥራት ጨምሮ እንደ አማኑኤል አይነት ትልቅ የአዕምሮ ህሙማን ማዕከልን ከማገዝ አንጻር የማይተካ ሚና እንደሚኖረውም አመላክተዋል።

ይህ ብስራት እንደ ሀገርም ድንቅ ድል በጤናው ዘርፍ የምናስመዘግብበት እንደሆነም ጠቁመው፤ ግንባታው ከሀገር ተሻግሮ በአፍሪካ ደረጃ ሕክምናን በጥራት በመስጠት በሕክምናው ዘርፍ አንድ ርምጃ የሚያሻግር እንደሚሆን አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የመከላከል እና አክሞ የማዳን አቅምን ከማሳደግ አንጻር እንዲህ አይነት ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ ሆስፒታሎችን መገንባት በእጅጉ ያስፈልጋልም ይላሉ።

ጤና ሚኒስቴርም ከዚህ አንጻር የአዕምሮ ሕሙማንና የሱስ ችግር ያለባቸውን ሰዎች እንዲያገግሙ ብሎም እንዲድኑ ለማድረግ ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ታሪኩ ታደሰ ናቸው።

እርሳቸው እንደሚሉት፤ አሁን እየተገነባ ያለው ፕሮጀክት በሀገር ደረጃ የመጀመሪያ የተቀናጀ ማገገሚያ ህክምና ማዕከል ነው።

13 አስተኝቶ ማከሚያ ብሎኮች፤ 19 የሚጠጉ ሕንጻዎች፤ አምስት ኪሎ ሜትር የአስፋልት የውስጥ ለውስጥ መንገድ፤ ሁለት ነጥብ ስድስት ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የእግረኛ መንገድ እንዲሁም ሰፋፊ የፓወር ሲስተሞችና ሰው ሠራሽ የሆኑ ሃይቆችና የአረንጓዴ ሥፍራዎች እንዲኖሩት ተደርጎ የሚገነባ ነው።

ማዕከሉ በሦስት ዓመት ውስጥ ግንባታው እንዲጠናቀቅ ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን የሚናገሩት ሥራ አስፈጻሚው፤ ግንባታው ሲጠናቀቅ የማገገሚያ ህክምና የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች መልሶ ለማቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

የአዕምሮ ህሙማንንም ሆነ የአካል ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ችግር በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚፈታ፤ ለሕክምናው ዘርፍ ተጨማሪ አቅም በመፍጠር ሕክምና የሚያገኙ ዜጎችን አክሞ የማዳንን እቅድ በማሳካት ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት አብራርተዋል።

በጽጌረዳ ጫንያለው
+++++++++++++
#አማኑኤል የአእምሮ ሆስፒታል

Miss it not!
21/10/2025

Miss it not!

Join Us for an Inspiring Finale!

The closing date of the art exhibition is extended for few days and it will end on Oct 24, 2025. On the closing day, there will be therapeutic art session, insightful individual discussion with psychologists, and live music from Kine-Fews Acoustic Band.

Don’t miss this opportunity to connect and reflect for free.
See you there!

N.B. The exhibition was visited by 423 people in total in 21 days.






ጥቅምት 11 2018 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በቦናንዛ ሆቴል ትውስታዎች
21/10/2025

ጥቅምት 11 2018 የዓለም የአእምሮ ጤና ቀን በቦናንዛ ሆቴል ትውስታዎች



ይህን መሰል አሳዛኝ ታሪኮች ቤት ይቁጠራቸው።እባካችሁ አግዙን የሰማ ላልሰማ ያሰማ፤የአእምሮ ህመም ውጤታማ ህክምና አለው!
21/10/2025

ይህን መሰል አሳዛኝ ታሪኮች ቤት ይቁጠራቸው።
እባካችሁ አግዙን የሰማ ላልሰማ ያሰማ፤
የአእምሮ ህመም ውጤታማ ህክምና አለው!

አሳዛኝ ታሪክ ከአማኑኤል ሆስፒታል (በድጋሚ የተለጠፈ)
===================================
'ራውንድ' እያደረግን ነው። አዲስ የገቡ ሶስት ታካሚዎች አሉ። ሁለቱን ካናገርኩ በኃላ የሶስተኛው ተራ ሲደርስ ሲስተር 'መምጣት አይችልም' አለችኝ። ያለበት ላየው ሄድኩኝ። ጉልበቶቹ ታጥፈው ይንፏቀቃል፤ መራመድ አይችልም። እግሮቹ ሰልለዋል። ስለህመሙና ስለህክምናው ተነጋገርን። ለምን መራመድ እንደማይችል ግን ሊነግረኝ አልፈለገም። ለተጨማሪ መረጃ እናቱን ማናገር ጀመርኩኝ።

ሁለት ወንድ ልጆች እንደነበሯቸውና አንደኛው ልጃቸውና ባለቤታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት እንዳረፉ ነገሩኝ። ብቸኛ ልጃቸው ህመም የጀመረው ከአምት አመት በፊት እንደነበረና የተለያዩ የባህል ህክምና እንደሞከሩለት ነገሩኝ። ነገር ግን ብዙ ለውጥ እንዳልነበረውና ህመም መሆኑን ባለማወቃቸው ወደ ህክምና እንዳልወሰዱት ነገሩኝ። ይጠፋብኛል ብለው ሰግተው ቤት ውስጥ ለአራት አመታት አስረው እንዳስቀመጡትና በዚያ ምክኒያት መራመድ እንደማይችል ሲናገሩ አይናቸው እንባ አቀረረ። ከአንድ አመት በፊት ሰዎች 'ለምን ህክምና አትወስጂውም?' ብለውኝ ነበር። እኔም ለመውሰድ አስቤ ነበር። ነገር ግን በአቅራቢያችን የአእምሮ ህክምና የለም። እዚህ ለመምጣት ደግሞ አቅም የለኝም። አሁን ራሱ የመጣነው ጎረቤት ገንዘብ ሰብስቦልን ነው። አሉ።

'የሚታከም መሆኑን ባውቅ ኖሮ ልጄን እንዲህ አላደርግውም ነበር።' አሉ። እንባቸው መውረድ ጀመረ። በእናት አንጀት የሚሰማቸውን ሀዘንና ፀፀት ሳስበው ውስጤ ተረበሸ። ሶፍት ከኪሴ አውጥቼ አቀበልኳቸው።

ያን ቀን ከስራ ሰወጣ የአእምሮ ህመም ግንዛቤ የተስፋፋ ቢሆን፣ ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ቢኖር የልጃቸው ሁኔታ እንዴት የተለየ ሊሆን እንደሚችል እያሰብኩ ነበር።

የአእምሮ ህክምና ግንዛቤን መፍጠር የሁላችንም ሀላፊነት ነው። መንግስት ደግሞ የአእምሮ ህክምና ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ ሀላፊነት አለበት።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም
ዶ/ር ዮናስ ላቀው።

29/05/2025

የአእምሮ ሕመም ሕክምና ምንነትና መለያ ባሕሪያት

ማጠቃለያ ክፍል ሶስት

ስለአእምሮ ሕመም ትኩረት በማድረግ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ክፍሎች ያስነበብናችሁን የምንቋጭበት የዛሬው ተከታይ ክፍል ትኩረቱን ያደረገው በሕክምና አሰጣጥ ክፍሉ ያሉ ተግዳሮቶችን፣ እንደ ጥንካሬ ምንጭነት የሚታየውን በራስ ተነሳሽነት ለምርመራ መቅረብ እና ዓለማቀፋዊና ሀገራዊ ገጽታውን ይመለከታል።

እንደማጠቃለያም ከሳይንሳዊ መፍትሄው ባሻገር ማኅበረሰባዊና ባሕላዊ ተሳትፎው ላይ ትኩረት በማድረግ ለመሰዳሰስ ይሞክራል፡፡
እንደቀድሞዎቹ ክፍሎች ሁሉ መረጃውን በማጋራት የተባበሩን በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ትምህርት ከፍል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ባርኮት ሚልኪያስ ናቸው::

የአእምሮ ሕመም ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ

የአእምሮ ሕመም ሕክምናውም ሆነ ጥናቶቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ይገኛል። የአእምሮ ሕመም መንስኤዎች በተለይ ተፈጥሯዊ ወይም አካላዊው ምክንያቶች ለምሳሌ አንጎል ውስጥ የሚገኙ ለአእምሮ ሕመም የሚያጋልጡ ግኝቶች አሉ።

በይበልጥ የዘረመል ተጋላጭነት፣ መድሃኒቶች ወይም ደግሞ ከኤሌክትሪክ ንዝረት ጋር የተገናኙ ሕክምናዎችን በሚመለከት የዘረመል ሕክምና ለማድረግ ተጋላጭነት ያለባቸውን ሰዎች ተጋላጭነቱን ለመከላከል ሳይንሱ በከፍተኛ ደረጃ አድጓል።

ስለዚህ የአእምሮ ሕመም ስሜት ብቻ ሳይሆን ትክክለኛ ሕመም መሆኑ ስነ ሕይወታዊ የሆኑ ማስረጃዎች በብዛት አሉ። ከቀደመው በላይ ሳይንሱ ብዙ የምርምር እና የጥናት ትኩረት እያገኘ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። አንጎል ውስጥ ያሉ ነገሮች አሉ። የማናየው፣ የማንዳስሰው፣ በላቦራቶሪ ምርመራ ወይም በዐይናችን የማናረጋግጠው ስለሆነ አወዛጋቢ ነው ልንለው እንችላለን። ምክንያቱም የአእምሮ ሕመም ከሁሉም የሕመም አይነቶች የተለየ ነው። ስለሕመሙ የተለያዩ ሰዎች ወይም የሕብረተሰብ ክፍሎች ብዙ አስተያየት አላቸው።

ስለሌላ ሕመም ብዙ ሰው ብዙ ነገር ሊል አይችልም፤ ሳይንስ የሚለውን ሕክምናው የሚለውን ነው የሚለው። ስለአእምሮ ሕመም ግን ሁሉም ሰው የራሱ አመለካከት አለው። ዘርፉ ለተለያዩ አስተያየቶች ክፍት ነው።

ዋናውና አስፈላጊ የሆነው ደግሞ የአእምሮ ሕመም በባሕል ጉዳይ ስሜታዊ ነገር መሆኑ ነው። የአእምሮ ሕመም አሜሪካንና አውሮፓ የሚታይበት መንገድና ኢትዮጵያ የሚታይበት መንገድ ይለያያል።
በምዕራብ ሀገራት አንድ የአእምሮ ሕመም የሚገለጥባቸው ምልክቶች እና በኢትዮጵያ የሚገለጥባቸው ምልክቶቹ ይለያያሉ። ከባሕል እና ከእምነት ጋር በጣም የተሳሰረ፣ የተቆራኘ ነው። ሕመሙ በተለይ ከባሕል ጋር የሚገናኝ ነገር ስላለው፣ የማይታይና አስቸጋሪም ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።

የዘርፉ ተግዳሮቶች

የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአዕምሮ ትምህርት ከፍል 26 ሠራተኞች ያሉት ሰፊ ክፍል ነው። ክፍሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአእምሮ ሕክምና አገልግሎት የሰጠ ነው። የመጀመሪያው የስፔሻላይዜሽን መርሃ ግብር ያለው ክፍል ነው። በትምህርት ክፍሉ የተማሩ የአእምሮ ሃኪሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የአእምሮ ሕክምና እየሰጡ እና የራሳቸውን ማእከል እየከፈቱ ናቸው። ከአእምሮ ሕክምናው ስር ብዙ ሰብስፔሻሊቲዎችን አዋቅሮ የያዘ ክፍል ነው። ለምሳሌ የሱስ ሰብእስፔሻሊቲ፣ ከሕግ ጉዳዮች ጋር የተያያዘ ፎረንሲክ የሚባለው የአእምሮ የጤና ሕክምና፣ የልጆችና የታዳጊዎች፣ ከባድ የሆነ የአእምሮ ቁስልን ጨምሮ ብዙ ሰብስፔሻሊቲዎች አሉት። እንዲህም ሆኖ ክፍሉ የራሱ የሆነ አገልግሎት የሚሰጥበት ቦታ የለውም። ትልቁ ችግር ቦታ አለመኖር ነው። አንድ ክፍል ብቻ ነው ያለው።

ስለዚህ ባለሙያዎች አገልግሎት የሚሰጡት በየሆስፒታሉ እየሄዱ ነው። አንዱና ዋናው ተግዳሮት ሕመሙ እንደማንኛውም ሕመም ቢሆንም በየሆስፒታሉ የአእምሮ ሕክምና የአእምሮ ሕመም ሕክምና ምንነትና መለያ ባሕሪያት እንደማንኛውም ሕመም ቦታ ተሰጥቶት መታከም አለመቻሉ ነው። እንደ አማኑኤል ሆስፒታል ለብቻ ሲወጣ አሉታዊ አመለካከት (stigma) ጋሬጣ ይሆናል።

የአማኑኤል ታካሚ፣ የአማኑኤል መድሃኒት የሚሉ ቅፅሎች ይወጡለታል። ስለዚህ ለብቻው ስም ያልተሰጠው እንዳይሆን ባሉ የጤና ተቋማት ጋር እንደ አንድ አገልግሎት ሲሰጥ አሉታዊ አመለካከቱንም ይቀንሰዋል።

የከፍል ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ባርኮት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ እንደማንኛውም ሕመም አንድ ላይ አገልግሎት ለመስጠት ቦታ እንዲኖረን በጣም እንፈልጋለን ብለዋል። ነገር ግን ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሌሎች ሕመሞች መሆናቸውን ያስረዳሉ።

‹‹የአእምሮ ሕመም እናክም ቦታ ይሰጠን›› ስንል ‹‹ከእኛ ታካሚዎች ጋር መስታወት የሚሰብርና የሚጮህ ታካሚ ልታመጡብን›› የሚሉ መኖራቸውን ረዳት ፕሮፌሰር ባርኮት ያብራራሉ። ይህ አይነቱ አመለካከት አሉታዊና የተሳሳተ ነው። የአእምሮ ሕመም እንደማንኛውም ሕመም ማንኛውንም ሰው የሚያም ሕመም መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።

ነገር ግን ስለሕመሙ ከማኅበረሰቡ ጀምሮ ያለው አመለካከት፣ ለሕመሙ ተገቢው ትኩረት አለመሰጠቱ፣ ተገቢው ቦታ እና አስፈላጊው ሃብት እያገኘ አለመሆኑ ትልቅ ጫና እየፈጠረ ነው። ረዳት ፕሮፌሰር ባርኮት ‹‹እኛ ያስተማርናቸው ልጆች ወደ ሌሎች ክልሎች ሄደው ትልቅ ማዕከል ይከፍታሉ። እኛ ግን እዚሁ አንድ ክፍል ይዘን የተመላላሽ ሕክምና ነው የምንሰጠው። አገልግሎቱን የምንሰጠው አማኑኤል ሆስፒታል ነው። እኛ የምንቆጣጠራቸው የተወሰኑ ክፍሎች አሉ።

ይሄ መለወጥ አለበት። ቦታውን እንዳናገኝ አንድ ምክንያት የሆነን አሉታዊ አመለካከቱ ነው። ይሄ ለዘርፉ ከተሰጠ የተዛባ አመለካከት የሚመነጭ ነው። በመሆኑም ለዘርፉ በቂ ቦታ፣ በቂ ሃብት እና ትኩረት እንዲሰጠው እንፈልጋለን›› ይላሉ።

የጥንካሬ ምልክት

የአእምሮ ሕክምና ለማግኘት ፈልጎ መምጣት እና ሕክምናውን ማግኘት ቀላል አይደለም። ይህ ማለት ወደ ሕክምና የሚመጣው ብዙ ነገር በማለፍ ነው። ሕክምናው ጋር የሚደረሰው ብዙ ውስጣዊ ሂደት ታልፎ ነው። ከራስ ጋር የሚታለፍ ነገር፣ ከማኅበረሰቡ ድጋፍ ፈልጎ ሳይሆን ወይ ደግሞ በእምነት መፍትሄ የሚፈለግበት፣ በሰዎች ግፊትም ይሁን በራስ እምነት የአእምሮ ሕክምና ፈልጎ መምጣት በጣም የሚደነቅ ነው። እንደ ባለሙያ የጥንካሬ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።

ምክንያቱም ሕክምናው እስኪ ጥርሴን ልታይ፣ አይኔን ልታከም ተብሎ እንደሚነገረው አይደለም። ሕመም ኖሮበትም ሆነ ሳይኖርበት ለማማከር መቅረብ የስንፍና፣ እምነት የማጣት እና መሰል ምክንያቶች ሳይሆን የጥንካሬ ምልክት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ይሄ ሕመም ነው አይደለም በሚል ጥርጣሬ ላይ ያሉ ካሉ ወደ ሕክምና መቅረቡ የጥንካሬ ምልክት እንጂ፤ ያለመቻል፣ የስንፍና ወይም የደካማነት ምልክት አለመሆኑን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ረዳት ፕሮፌሰር ባርኮት ይመክራሉ።

ሁሉም የአእምሮ ሀኪም እንዲሆን

ስለውስጡ ወይም ስለስሜቱ ሊያወራ የፈለገ ሰው ካለ ማድመጥ አንዱ በአእምሮ ሕክምና ያለን መገፋት ይቀንሳል። እኛም ማውራት ከፈለግን የራሳችን የሆነ ሰው ጋር ሄደን ማውራት ትልቅ ቦታ ያላቸው ነገሮች ናቸው። ማኅበረሰቡ የኖረው እርስ በርስ እየተደጋገፈ እና አንዱ ሌላውን እያከመ ነው። እርስ በእርስ በባኅላዊ እና ሃይማኖታዊ የሚደረጉ ድጋፎች በራሳቸው ለዘመናት እያከሙ ኖረዋል።

ዘመናዊው ነገር አሁን ገና እየመጣ ነው። ዘመናዊው ነገርም የነበረው ላይ ሊጨመር እንጂ ያንን ሊያጠፋ አይደለም። በመሆኑም በሕብረተሰቡ ውስጥ የነበረውን ድጋፍ እያደረግን መቀጠሉ ጠቃሚ ነው። ትንሽ ሰበር ያለ፣ ከባድ ነገር ውስጥ እያለፈ የሚመስለን ሰው እንዲያወራ ቀላል ሆኖ መቅረብ ይገባል። ይህ ማለት ግን አይዞህ፣ ጠንከር በል፣ ስንት የምታመሰግንበት ነገር አለ አይደል እንዴ? በሚሉ እና መሰል ነገሮችን በማለት አይደለም። ለሕክምናው የሚጠበቀው ማዳመጥ ነው።

ለመምከር መዘግየት፣ ለመስማት ደግሞ ቀድሞ መገኘት እና ቀላል መሆን ይገባል። ለውስጣዊ ነገሮች ክፍት መሆን፤ እያንዳንዳችንም ለውስጣችን ጊዜ የሚሰጠን ሰው ካለ ይህንን ማድረግ ተገቢ ነው። አልፎ ደግሞ እኛ ጋር ሊያወራ የሚፈልግ ሰው ካለ የጥንካሬ ምልክት ነው። መደገፍ ይቻላል። ሰው ፈርቶ ወደኋላ መቅረት የለበትም።

ብዙዎቹን ሰምተን እንልካለን። ይሄ ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል። አንዳንዶች የአእምሮ ሕክምና ብለው እንደሚያስቡት የሚያደነዝዝና በተለምዶ የሚያጀዝብ የሚባለው መድሃኒት አይደለም። ወደ ሕክምና ተቋም ሄደው አውርተው ተንፈስ ብለው ቢሄዱ ራሱ ሕክምና ነው። ይህ በሳይንስ ጭምር የተረጋገጠ፣ ምን ያህል እንደሚረዳ የታወቀ ነው። ለመምከር ሳይሆን ለመስማት ራሳችንን እንስጥ። ነገር ግን አዳምጦ የማይፈርድባቸው፣ ሚስጥራቸውን የማያወጣባቸው መሆን ይኖርበታል።

ጥናት የሚያሳየው የአእምሮ ሕመም ያለባቸው ሰዎች 85 በመቶ ያህሉ ምንም አይነት ሕክምና እያገኙ አለመሆኑን ነው። ሕክምና የሚያገኙት 15 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። መልካም መሆን ጥሩ ነው ብለን ያነሳነው በራሱ ቢያንስ 85 በመቶውን ያክማል ማለት ነው። የተደራሽነት ችግር፣ ግንዛቤው በስፋት አለመኖር፣ ሕመም ነው ብሎ አለማሰብ፣ እያወቀም አሉታዊ አመለካከቱን መስጋት፣ አንዳንዱ ደግሞ አውቆም ሕክምናው በአካባቢው አለመኖር ችግር ወይም መድሃኒቱን ለመግዛት የአቅም ውስንነት፣ ሆስፒታል በአጠገቡ እያለም የአእምሮ ጤና ባለሙያ አለመኖር ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ።

ሆስፒታልም ሄዶ የአእምሮ ጤና ባለሙያ ባለመኖር ወይም ባሉ ጤና ተቋማት የአእምሮ ሕክምና ክፍል አለመካተቱ ወይም ሌሎቹ ሃኪሞች ጠቅላላ ሃኪም ሳልና ትኩሳት እንደሚያክመው ለምሳሌ የሚጨነቅንም ሰው ማከም አለበት። ይሄ ባለመሆኑ ሕመሙ ራሱ አይታከምም። ሰውየው ታሞ በእንቅልፍ ማጣት ወይም ክብደት በመቀነስ ላቦራቶሪ እየተመላለሰ የሚያሠራ ይሆናል። ሆኖም ግን ሕመሙ ላይታወቅለት ይችላል። 85 በመቶዎቹ ያሉት በማኅበረሰቡ ውስጥ ናቸው። ሁሉም ለማከም ኃላፊነት አለበት። ሕክምናው ደግሞ ቀላል ነገሮች ናቸው። አብሮ ተቀምጦ ቡና መጠጣት ሊሆን ይችላል። አብዛኛው ደግሞ ከባድ የአእምሮ ሕመም አይደለም። የተለመዱ የአእምሮ ሕመም አይነቶች ናቸው። ስለዚህ ጊዜና ትኩረት መስጠት ግድ ይላል።

እንደማጠቃለያ

ስለሕመሙ ግንዛቤ አለመኖር ችግር በታካሚው፣ በባለሙያው እና በማኅበረሰቡም ዘንድ የሚታይ ነው። ባለሙያው የተወሰነ የአእምሮ ሕመም ማከም እንዲችል የሰለጠነ ቢሆንም የአእምሮ ሕመም አመጣጡ ግን የተለያየ በመሆኑ በቀላሉ ሊታለፍ ይችላል። ሰውየው መጥቶ በፈገግታ ስለሕመሙ ነግሮ ከሄደ ይሄ እማ ጭንቀት አይደለም ብሎ ሊታሰብ ይችላል።

የአእምሮ ሕመም የሆነ ፊትና ገጽታ የለውም። ጠጋ ብሎ በማውራት የሚታወቅ ነገር ነው። የአእምሮ ሕመም አይነቱ እና መገለጫው ሊለያይ ይችል ይሆናል እንጂ፤ በየትኛውም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ነው። በልጆች ላይ፣ በታዳጊዎች፣ በአዋቂዎች እስከ ሽምግልና እድሜ ድረስ ይከሰታል። በእድሜ የተገደበ አይደለም። ለምሳሌ የድባቴ ሕመም ልጆች ላይ ሲከሰት አዋቂዎች ላይ አንድ ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ልጆች ላይ የተለያየ ባሕሪ ወይም ለውጥ ስናይ የአእምሮ ሕመም አይደለም ማለት አንችልም። ሕክምናውም በሁሉም የእድሜ ክልል የሚሰጥ ነው።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር Mental Service Users' Association - Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to የአእምሮ ህክምና አገልግሎት ተጠቃሚዎች ማህበር Mental Service Users' Association - Ethiopia:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram