ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ Joy obstetrics and gynecology specialty clinic

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ Joy obstetrics and gynecology specialty clinic

ጆይ የጽንስና የማህጸን  ልዩ ክሊኒክ Joy obstetrics and gynecology specialty clinic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ Joy obstetrics and gynecology specialty clinic, Women's Health Clinic, Fikre Mariam Aba Techan Street, Addis Ababa.
(1)

ለጤናማ እርግዝና መዘጋጀትና ማቀድ   እርግዝናዎ በተቻለ መጠን ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ  እርስዎ እና ሐኪምዎ ልታደርጓቸው የምትችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እነዚህ ከስር የተዘረዘሩት ነገሮች ...
15/03/2025

ለጤናማ እርግዝና መዘጋጀትና ማቀድ

እርግዝናዎ በተቻለ መጠን ጤናማ እንዲሆን ለማድረግ እርስዎ እና ሐኪምዎ ልታደርጓቸው የምትችሏቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እነዚህ ከስር የተዘረዘሩት ነገሮች ለማርገዝ ከመሞከርዎ በፊት ቀደም ብለው ሊደረጉ ይገባል

● የሚወስዷቸውን መድሃኒቶች ካሉ እና ምን አይነት ለውጦች ማድረግ እንዳለብዎት ይወቁ

● ክትባቶችዎ ወቅታዊ መሆን አለመሆንዎን ይወያዩ

● ፎሊክ አሲድ ያለው መልቲቫይታሚን መውሰድ ይጀምሩ

● የትኞቹ ምግቦች ማቆም እንዳለብዎ እና የትኞቹ ምግቦች ማዘውተር እንዳለብዎ ይወቁ

● ሲጋራ ማጨስን፣ አልኮል መጠጣትን፣ ወይም በሃኪም ያልታዘዘልዎት መድሃኒቶችን ከመውሰድ ይታቀቡ

● ማንኛውም የሕክምና ሁኔታ ካለዎት ፣ በቤተሰብዎ ወይም በትዳር ጓደኛዎ ቤተሰብ ውስጥ የሚከሰቱ በሽታዎች ካሉ በጽንሱ እና በእርስዎ ላይ ሊያስከትል የሚችል ችግር ካለ ይረዱ።

● በመኖሪያ ቤትዎ ወይም በስራ ቦታዎ ውስጥ ማንኛውም ጎጂ ነገር እንዳለ አውቀው ምን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለብዎ ይወቁ

● ጤናማ የክብደት መጠን ለመድረስ ይሞክሩ

በስነተዋልዶ ጤና ዙሪያ ጠቃሚ ጽሁፎች ለማንበብ ገፃችን "ላይክ" ያድርጉ::
ስልምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች መረጃ ለማግኘት በ 0912017767 ይደውሉ::

ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ

አድራሻ

ኮተቤ-መሳለሚያ ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ ወደ ሲኤምሲ አደባባይ እና ጸሓይ ሪልስቴት የሚውስደው መንገድ የመጀመሪያው ቅያስ 50 ሜትር ገባ ብሎ አስቴር ኃይሉ ህንፃ ፊትለፊት።
ስልክ ቁጥር፣ 0912017767
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

05/03/2025

ረመዳን እና እርግዝና

ረመዳን በአመት አንድ ጊዜ የሚመጣ ልዩ የሆነ ጊዜ ነው። በዚህም ጊዜ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች መጾም አይጠበቅባቸውም ፣ይሁን እንጂ ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አብዛኛው ሴቶች አሁንም በእርግዝና ወቅት መጾምን እንደሚመርጡ እና ከሀኪምቻቸው ጋር ስለ ጾም ከመወያየት ይቆጠባሉ።

ከሀይማኖት አንፃር

ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች ሙስሊም ሴቶች በእስልምና የረመዷን ወር አለመፆም ይችላሉ፣ በተለይም የእናትየው ወይም የፅንስ ጤና ላይ ጉዳት የሚያጋጥም መስሎ ከተሰማቸው ( ካጋጠማቸው) ማለት ነው ። ላለመጾም ከወሰነች፣ ያመለጡትን የፆም ቀኖች በኋላ ላይ ማካካስ ወይም በምትኩ ፊድያ (የተወሰነ የበጎ አድራጎት ልገሳ) ማድረግ ትችላለች ።

ከሳይንስ አንፃር

የረመዳንን ወር የሚጾሙ እርጉዝ ሴቶች በአለም ዙሪያ ባሉ ሙስሊም ማህበረሰቦች ዘንድ የተለመደ ነው። ነገር ግን የተለያዩ የህክምና መመሪያዎች የመፆም ውሳኔ የእናትየው ላይ እንዲሁም በማህፀና ውሰጥ ባለው ህፃን ጤና ላይ ተጽእኖ ስለሚያሳድር በጥንቃቄ ሊታሰብበት እንደሚገባ ያስረዳሉ። አንደምክንያቱም እንደሚከተለው ተገልፆዋል ።
ነፍሰ ጡር እናቶች በማህፃናቸው ውስጥ የሚገኘው ህጻን እድገት እና ብልፅግና እንዲረዳው በቂ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ስለሚያስፈልጋቸው እና ፆም አስፈላጊ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች ለማግኘት ስለሚገድብ ነው። ነገር ግን በእውነቱ የረመዷን ወር መፆም በቀን ውስጥ የነበረውን የአመጋገብ ስርዓት ብቻ ወደ ለሌሊት ይለውጣል እንጂ ህፃኑ የሚያሳፈልገውን ንጥረ ነገር ከማግኘት አይገድበውም ።

የረመዳንን መፆም እርጉዝ ሴቶች ላይ የሰውነት ድርቀት (Dehaydration) የመጋለጥ እድልን ይጨምራል።
በእርግዝና ወቅት የነፍሰ ጡር ሴቶች አካል የሕፃኑን እድገት ለመደገፍ እና ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጤንነት ለመጠበቅ ተጨማሪ ውሃ ይፈልጋል፤ ስለዚህ በጾም ወቅት ውሃ አለመጠጣት ሰውነት የሚፈልገውን የውሃ መጠን ይቀንሳል ፤ ነገር ግን በስሁር እና በፆም በሚፈቱበት ሰዓት ለነብሰ ጡር የሚያስፈልጓቸውን ንጥረ ነገሮች ከሞላች መፆም አስተማማኝ ነው።

ከተለያዩ ጥናቶች ለማየት እንደቻልነው የረመዳንን ፆም በዋናነት ከእናቶች ድካም እና የሰውነት ድርቀት (Dehydration) ምልክቶች ውጭ ተፅኖው በተለየም በሚወለደው የልጅ ክብደት ወይም ያለጊዜው መውለድ ላይ ያለው ክሊኒካዊ ጉልህ የሆነ አሉታዊ ውጤት አልተገኘም ። ጾም በልጁ ላይ የሚኖረውን የረዥም ጊዜ ተጽእኖ የሚገልጹ ወቅታዊ ጽሑፎች የጎንዮሽ ጉዳቶችን ይጠቁማሉ፤ ነገር ግን ተጨማሪ መረጃ ያስፈልጋል።

የማህፀን ህክምና እና ሌሎች የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ ሰጪዎች ባለሙያዎች ለታካሚዎችን በጋራ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ማሳተፍ እና የህክምና ልምዳቸው እና በታካሚ ታሪክ ላይ ተመስርተው ስለ ማስረጃዎቹ (ውሱንነቶችን ጨምሮ) እና ልዩ የሆነ የህክምና ምክሮች መስጠት አለባቸው።
በመቀጠልም በእርግዝና ክትትል ወቅት በጾም ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳትና ችግር ለመቀነስ የሕክምና ምክሮችን፣ የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ መስጠት አለባቸው።

ነፍሰ ጡር እናቶች በረመዷን ለመጾም ከወሰኑ ጤንነታቸውን እና ምቾታቸውን ለመጠበቅ ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል።
• በመጀመሪያ ነፍሰ ጡር እናቶች ሰሁርን ሲመገቡ እና ፆማቸውን በሚፈቱበት ወቅት የተመጣጠነ ምግብ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። እንደ አትክልትና ፍራፍሬ ባሉ ንጥረ ነገሮች የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ፣ እንደ አሳ፣ ስጋ ወይም ባቄላ ያሉ የፕሮቲን ምንጮች እና እንደ ሩዝ ወይም ዳቦ ያሉ ውስብስብ ካርቦሃይድሬትስ ያሉ ምግቦችን መመገብ የነፍሰ ጡር እናቶችን እና የህፃኑን ጤና ለመጠበቅ ይረዳል።
• ሁለተኛ ነፍሰ ጡር እናቶች በፆም ወቅት ለመጠጣት በሚፈቀድላቸው ጊዜ በቂ መጠን ያለው ውሃ መጠጣታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው። በቀን ቢያንስ ከ10 ብርጭቆ በላይ ውሃ መጠጣት የሰውነትን እርጥበት ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ እና ከሰውነት ውስጥ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ለማስወገድ ይረዳል።
• በሶስተኛ ደረጃ ነፍሰጡር እናቶች በረመዷን በተለይም በሞቃት ወቅት ከጠንካራ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መቆጠብ አለባቸው። ከመጠን በላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሰውነት ድርቀት እና ድካም የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ፤ ይህም በነፍሰ ጡር ሴቶች እና በልጆቻቸው ጤና ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።
• አራተኛ ነፍሰጡር እናቶች ሁል ጊዜ የዶክተሩን ምክር በመከተል በረመዳን ወር ጤንነታቸውን መከታተል አለባቸው።
• ስለዚህ በአጠቃላይ ነፍሰ ጡር እናቶች የራሳን እንዲሁም የህፃን ሁኔታ ጤናማ ከሆነ እና የዶክተሩን መመሪያ ከተከተሉ የረመዳን ወር መፆም ደህንነቱ የተጠበቀ ይሆናል። በማህፀን ውስጥ ሆኖ ያልተለመዱ ምልክቶች ከታዩ ወዲያውኑ ከህክምና ባለሙያ እርዳታ መጠየቅ አለብሽ።

ዶ/ር መሁዲን አሩሲ
የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

Address

Fikre Mariam Aba Techan Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጆይ የጽንስና የማህጸን ልዩ ክሊኒክ Joy obstetrics and gynecology specialty clinic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram