11/08/2025
ስለ ዓመታዊ የጤና ምርመራ
Annual Health Check-Up
አመታዊ የጤና ምርመራ በተለያየ የዕድሜ ክልል ላይ ላሉ ሰዎች የሚደረግ እና ለአንድ በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ቀድሞ ለማወቅ የሚያስችል የምርመራ ዘዴ ነው።
እድሜ እና ፃታን መሠረት አድርገው በየአመቱ እና ከዛም በላይ ሊደረጉ የሚገቡ የምርመራ አይነቶች አሉ። እነዚህን ምርመራዎች መረዳት እና መቼ መጠየቅ እንዳለቦት ማወቅ ጤናማ ሆነው እንዲቆዩ ያግዝዎታል። እንደ ካንሰር ፤የልብ ህመም፤ስትሮክ ፤የኩላሊት ህመም፤የስኳር ህመም፤የደም ግፊት መጨመር እና አንዳንድ በቅድመ ጥንቃቄ ልንከላከላቸው የምንችላቸውን ህመሞች ለመቆጣጠር ቀደም ብሎ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
ምን ዓይነት ምርመራዎችን ማድረግ አለብዎት?
ከ 18- 39 አመት የሞላቸዉ ሰዎች እነዝህን ምርመራዎች እንድያደርጉ ይመከራል፡-
ክብደት እና ቁመት
የደም ግፊት ልኬት
የዓይን ምርመራ
የጆሮ ምርመራ
አጠቃላይ የደም ህዋሶች ምርመራ
የኩላሊት አሰራር፣ የጉበት አሰራር ምርመራዎች፣የተለያዩ የደም ውስጥ ንጥረ ነገሮች ምርመራ
በሰውነት ውስጥ ያለ የስብ መጠን ምርመራ
የታይሮይድ ሆርሞን ምርመራ
የስኳር በሽታ ምርመራ
በደም ንክኪና በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች፡- ኤችአይቪ ፤ጨብጥ፣ቂጥኝ ወይም ሌሎች ኢንፌክሽኖችን ሊያካትት ይችላል።
የሽንት ምርመራ
የልብ ምርመራ
ለሴቶች ከ21 ዓመት ዕድሜ ወይም ግንኙነት ማድረግ ከተጀመረበት ከ3 ዓመታት ጀምሮ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ፡ በየ 3 አመቱ የፓፕ ስሚር ምርመራ ያደርጋል፡፡
ከ 40 አመት በላይ የሆኑ ሰዎች ለተለያዩ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸዉ በጣም ስለ ምጨምር ከላይ ከተዘረዘሩት ምርመራዎች በተጨማሪ እነዝህን መመርመር አለባቸዉ፡-ኮሎኖስኮፒ፤ለሴቶች ደግሞ የማህፀን በር ካንሰር ምርመራ፤ማሞግራም(የጡት ካንሰር) እና በሰውነት ውስጥ ያለ የካልሲየም መጠን መቀነስ ወደ አጥንት መሳሳት ችግር ሊያመራ ስለ ምችል የአጥንት ምርመራ እድሜያቸው 65 እና ከዛ በላይ ለሆኑ ሴቶች ይመከራል፡፡
ዕድሜያቸዉ ከ50 ዓመት በላይ የሆኑ ወንዶች የፕሮስቴት ዕጥ እና የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ በአልትራሳወንድና በደም ምርመራ ማድረግ አለባቸዉ፡፡
ማስታወሻ
ሁሉም ሰው ዓመታዊ የጤና ምርመራ የማድረግ ልማድ ሊኖረው ይገባል ምክንያቱም ዕድሜዎ እየገፋ ሲሄድ ጤናዎ ላይ ለውጥ ይኖራል፡፡ በተለያዩ የሕይወትዎ ደረጃዎች ውስጥ ለተለያዩ በሽታዎች የበለጠ ተጋላጭ ይሆናሉ። እነዚህም በርካታ የካንሰር ዓይነቶችን ፣ የደም ግፊት ፣ የስኳር በሽታ እና የደም ቧንቧ መጥበብ ችግሮችን ያጠቃልላል።
እንዲሁም የራስዎን እና የቤተሰብዎን መልካም ጤንነት ለመጠበቅ ይሄን ተግባር በህይወት ዘመንዎት በቁርጠኝነት ከሚያከናውኗቸው ተግባራት ውስጥ ማካተት አለብዎት።
🔬ታዲያ በዚህ ክረምት ለምን የጤና ምርመራ አያደርጉም?🚑
📌የስራ ሰዓት:- ዘወትር በስራ ከሰዓት እንገኛለን
🚨ለህክምና አገልግሎት በ 📞+251936659999 / +251911194824 ይደውሉ።🚨
👉አድራሻ:-ሳሚት ኮንዶሚኒየም, አሳት አደጋ ወረድ ብሎ እንገኛለን።
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ.፡