Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS

Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS, 9. 046572, 38. 728670, Addis Ababa.

Ethiopian Pharmaceutical Supply service , EPSS
, procure ,manage and distribute RDF & Heath Programme Products for governmental health facilities to supply quality assured essential pharmaceutical with affordable prices & a sustainable manner in Eth

24/04/2026
መድሃኒትን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚደረጉ ጥረቶች ተገቢው እገዛ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ*******************የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ የ...
24/04/2026

መድሃኒትን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚደረጉ ጥረቶች ተገቢው እገዛ ሊደረግላቸው እንደሚገባ አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ
*******************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ የመድሃኒት እና ሕክምና ቁሳቁሶችን በአገር ውስጥ ለማምረት የሚያስችሉ አቅሞችን ለመደገፍ ባንካችን ቁርጠኛ ነው ሲሉ አስታወቁ፡፡ የአገር ውስጥ መድሃኒት ፍላጎትን ምላሽ የሚሠጡ ፕሮጀክቶች ተገቢው እገዛ ሊደረግላቸው እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት፤ በፕሬዚደንታችን የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ በቅሊንጦ ኢንደስትሪ ዞን የሚገኘውን የአፍሪኪዩር የፋርማሲዩቲካልስ ማኑፋክቸሪንግ ኢትዮጵያን ጎብኝቷል፡፡

የልኡካን ቡድኑ አባላት የፋብሪካውን የምርት፣ የላብሯቷሪ፣ የጥራት ቁጥጥር፣ የክምችት፣ የአስተዳደር እና መሰል ክፍሎችን የጎበኙ ሲሆን፤ በድርጅቱ ባለቤቶች እና ባለሙያዎች በፋብሪካው አመራረት፣ አሰራር እና ወደ ገበያ ለመግባት ባለው ዝግጁነት ዙሪያ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡

በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ የባንካችን ፕሬዚደንት አቶ አቤ ሳኖ፤ ፋብሪካው የአገር ውስጥ መድሃኒት ፍላጎትን ለማሟላት ያለው ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በየዓመቱ ለመሰረታዊ መድሃኒቶች ግዥ የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት፤ ከአገር ውስጥ ፍጆታ የሚተርፈውን ለውጭ ገበያ በማቅረብ፤ ለውጭ ምንዛሬ ግኝትም አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም አለው ሲሉ ፕሬዚደንቱ አስገንዝበዋል፡፡

ፋብሪካው፤ ለምርት ጥራት በየደረጃው ለሰጠው ትኩረት ያላቸውን አድናቆት የገለጹት አቶ አቤ፤ የፋብሪካው ግንባታና የማምረቻ መሳሪያዎች ተከላ ተጠናቆ ወደ ማምረት አለመሸጋገሩ የሚያስቆጭ ነው ሲሉ አሳስበዋል፡፡

ባንካችን ፋብሪካው ወደማምረት እንዲሸጋገር አስፈላጊውን ድጋፍ እና እገዛ እንደሚያቀርብም በጉብኝቱ ወቅት ጠቁመዋል፡፡

የፋብሪካው መስራች፣ ባለድርሻና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ታደሠ ተፈሪ፤ አፍሪኪዩር ፋርማሲዩቲካልስ፤ በአገር ውስጥ ያለውን የመድሃኒት ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ታስቦ መገንባቱን ገልጸዋል፡፡

ፋብሪካው ወደ ማምረት እንዲሸጋገር ባንካችን ያሳየውን በጎ ምላሽ አድንቀዋል፡፡ ፋብሪካው ምርት ሲጀምር ለአገራችን የጤና ዘርፍ ታላቅ የምስራች ከመሆኑም ባሻገር፤ ወደ ሶስት የአፍሪካ አገራት ምርቶቹን ይልካል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ የፋብሪካው አዲስ ባለድርሻ በመሆን የሚገቡት ዶ/ር መሐመድ ኑሪ በበኩላቸው፤ ፕሬዚደንታችን በፋብሪካው በመገኘት ላደረጉት ጉብኝት አመስግነዋል፡፡

ከፋብሪካው ትልቅነት እና አገራዊ ፋይዳ ጋር ተያይዞ ወደ ማምረት በፍጥነት ለመሸጋገር የፋይናንስ አቅርቦት ተግዳሮት እንደገጠማቸው እና ይህንኑም ለመቅረፍ ከባንካችን ጋር የተጀመሩ አጋርነቶች እና ትብብሮችን አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በስነ ምግባርዊ ዉሳኔ አሰጣት እና የጥቅም ግጭት ማስተዳደር ላይ የግንዛቤ መድረክ በአገልግሎቱ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ ------------...
23/04/2026

የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በስነ ምግባርዊ ዉሳኔ አሰጣት እና የጥቅም ግጭት ማስተዳደር ላይ የግንዛቤ መድረክ በአገልግሎቱ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
-------------------

የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ሚያዝያ 15 ቀን 2018ዓ.ም በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዘመናዊ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በስነ ምግባርዊ ዉሳኔ አሰጣት እና የጥቅም ግጭት ማስተዳደር ዙሪያ ለጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ የጤና ሚኒስቴር ዲኤታዎች ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እና ወ/ሮ ፍሬህይዎት አበበ ፤ የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ ፤ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንዲሁም የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረኩ ለተቋም ግንባታው አዎንታዊ ሚናው የላቀ እንደሆነ የገለፁት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ክፍተቶች ላይ በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ሃላፊዎች ዉሳኔ ሲወስኑ የትክክለኛነት፣ የፍትህ፣ የተግባር ኃላፊነት እና የሌሎች መብት መከበርን መመርመር እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

ስለ ስነ ምግባራዊ ዉሳኔ አሰጣጥ እና የጥቅም ግጭት ፤ የጤናው ዘርፍ የጥቅም ግጭት ስጋትና ተጋላጭነት፤ ገንዘብ፣ ቤተሰብ፣ ጓደኞች ከሙያዊ ወይም ድርጅታዊ ኃላፊነት ጋር እንዴት ይጋጫል ፤ ቀጥታ (Actual) ግጭቱ እውነተኛ ሲሆን ምን አይነት ጥንቃቄ ይደረግ ፤ የሚታይ (Perceived) ወይንም ሊኖር የሚችል (Potential) ሲሆንስ ምን ይወሰን በሚሉት ሃሳቦች ዙሪያ ግንዛቤ ተሰቷል፡፡

የደንበኞችን ፍላጎት በበቂ ደረጃ ምላሽ ለመስጠት የአገልግሎቱ አመራሮች ከመቼዉም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ እንደሆኑ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ጠቁመው በስነ ምግባርዊ ዉሳኔ አሰጣት ብቃት ያለው አመራር እየተገነባ እንደሆነና ሁሉም የጤናው ዘርፍ ሃላፊዎች በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

#ማገልገል ክብር ነዉ
አማኑኤል ወርቃየሁ

23/04/2026

የሶስተኛው የ100 ቀናት አፈጻጸም ሪፖርት በተመለከተ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ያስተላለፉት መልዕክት

54 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የመድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል - ዶ/ር መቅደስ ዳባ አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 54 ቢሊየን...
23/04/2026

54 ቢሊየን ብር የሚገመቱ የመድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል - ዶ/ር መቅደስ ዳባ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 54 ቢሊየን ብር ግምት ያላቸው የመድሀኒትና የህክምና ቁሳቁሶችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል አሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2018 በጀት ዓመት ሦስተኛው የ100 ቀናት እና የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
ሚኒስትሯ በጤናው ዘርፍ የተመዘገበውን አፈጻጸም አስመልክተው በሰጡት ማብራሪያ፥ ተደራሽነትን፣ ጥራትንና ፍትሃዊነትን መሰረት በማድረግ በርካታ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል፡፡
ከውጭ የሚገቡ መድሀኒቶችን በሀገር ውስጥ ለመተካት በተደረገው ጥረት ከሀገር ውስጥ የመድሀኒትና የህክምና ቁሳቁስ አምራቾች ጋር በርካታ ግዥዎች ተፈጽመዋል ነው ያሉት፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ 54 ቢሊየን ብር ወጭ በማድረግ መድሀኒቶችንና የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን ለተለያዩ ክልሎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
በጤና ዘርፉ ዲጂታላይዜሽንን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በተሰራው ስራ የጤና ተቋማት ያሉበትን ደረጃና የመድሃኒት አቅርቦት እንቅስቃሴዎችን መከታተል የሚያስችል ዲጂታል አሰራር ወደ ሥራ እንዲገባ መደረጉን አንስተዋል፡፡
የጤና ዘርፉ በተለይም ህክምና ቁሳቁሶችንና መድሃኒቶችን በማምረት ኢንዱስትሪውን እየደገፈ ይገኛል ያሉት ሚኒስትሯ፥ ዘርፉን በዲጂታል አሰራር የማዘመን የተቀመጡ ስትራቴጂዎችን ውጤታማ የማድረግ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ

የሴቶች ቀን አንድ ቀን ተከብሮ የሚረሳ ሳይሆን በየዕለቱ ጉድለታችንን ለመሙላት የምንሰራበት መሆን እንደሚገባ ተገለፀ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2018 ዓ...
20/04/2026

የሴቶች ቀን አንድ ቀን ተከብሮ የሚረሳ ሳይሆን በየዕለቱ ጉድለታችንን ለመሙላት የምንሰራበት መሆን እንደሚገባ ተገለፀ

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም አለም የሴቶች ቀን ( Mach 8 ) በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ115ኛ ጊዜ " Give to Gain) በሚል ቃል እንዲሁም በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ " የሴቶች ድምፅ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል አከበረ ።

የሴቶች ቀን አንድ ቀን ተከብሮ የሚረሳ ሳይሆን በየዕለቱ ጉድለታችንን ለመሙላት የምንሰራበት መሆን እንደሚገባ ያሳሰቡት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ ሲሆኑ ፤ የአገልግሎቱ የህክምና ግብዓት አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን አስታውሰው ይህንን ያለ ሴቶች አስተዋፅኦ ማስመዝገብ እንደማይቻል ተናግረዋል ።

የሴቶች ድምፅ ለዕኩልነት እና ለበለጸገች ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የሴቶች ቀን መሪ ቃሉ ወደ ተቋማችን በመውሰድ ልንተገብረው የሚገባ መሆኑን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ አሳስበው ፤ በተቋሙ ሴቶች ወደ ውሳኔ ሰጪነት እንዲመጡ አስፈላጊውን እገዛ ከዚህ ቀደም ከነበረው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ቃል ገብተዋል ።

ይህንን ቀን ለሴቶች ተጨባጭ ለውጥ በሚያመጣ መልኩ ለማክበር አመቱን ሙሉ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን የአገልግሎቱ የሴቶች ፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አለም ፀሀይ ዳታ ተናግረው ፤ ይህ ፕሮግራም እንዲሳካ ላደረጉ ለጤና ሚኒስቴር እና ለአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

የትምህርት ዕድሎች መስጠት ፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር ፣ ምቹ የስራ አካባቢን ከመፍጠር አንፃር ፣ 7 የህፃናት ማቆያ ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ስራ የገቡና በግንባታ ላይ 6 ማቆያ ይገኛል ፣ በክፍሉ የተዘጋጁ የተለያዩ ዶክመንቶች እነዚህንና ሌሎች አንኳር ስራዎችን የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ባለሙያ ወ/ሮ ሂሩት ሀይሉ በዝርዝር አቅርበዋል ።

የፓናል ውይይት የተከናወነ ሲሆን ፓናሊስቶቹ የትምህርት ፣ የስራና የግል ህይወት ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች ያጋሩ ሲሆን ።፤ በመጨረሻም የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሂዷል ።

ማገልገል ክብር ነው !
ማኅሌት አበራ

የክትባት አገልግሎትን በፋርማሲዎች ለመስጠት የሙከራ ፕሮጀክት ተጀመረ፨፨፨፨፨፨የሙከራ ፕሮጀክቱ የክትባት አገልግሎትን ወደ ህዝብ በቀላሉ ለማድረስ እና የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ...
19/04/2026

የክትባት አገልግሎትን በፋርማሲዎች ለመስጠት የሙከራ ፕሮጀክት ተጀመረ
፨፨፨፨፨፨

የሙከራ ፕሮጀክቱ የክትባት አገልግሎትን ወደ ህዝብ በቀላሉ ለማድረስ እና የጤና ስርዓቱን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ያለዉ ሲሆን በኢትዮጵያ የክትባት ተደራሽነትን ለማሳለጥ ፋርማሲዎች እንደ ተመራጭ የአገልግሎት መስጫ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህም መሰረት በሙከራ ደረጃ በ20 ፋርማሲዎች የክትባት አገልግሎት መጀመሩን የኢትዮጵያ ፋርማሲ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ገልፀዋል።

ፕሬዝዳንቱ እንደገለፁት የፋርማሲ ባለሞያዎችን በተገቢው ስልጠና በማብቃት እና የሀገሪቱን የጤና ፖሊሲ መመሪያዎች በመከተል የሙከራ ፕሮጀክቱ ውጤት ከታየ በኋላ በመላው አገሪቱ እንዲስፋፋ እቅድ መኖሩን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የPopulation Services International Ethiopia (PSI) ፕሮጀክት ዳይሬክተር ወ/ሮ ቤተልሔም አበራ እንደገለፁት ክትባትን በጥራት እና በስፋት ለማቅረብ ተገቢ የሆኑ ስልጡን ባለሞያዎችን ማቀናጀት እንደሚገባ ገልፀዉ ፤ ፕሮጀክቱ በመነሻነት በአማራ እና ኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ እንዳለ አስታዉቀዋል።

በፕሮጀክቱ ከ300 ሺህ በላይ ሰዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ፕሮጀክት ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

የጤና ሚኒስቴር እና ሌሎች ተጠሪ ተቋማት ከክልል የጤና ቢሮዎች ጋር በመቀናጀት ፕሮጀክቱ እየተጠናከረ እንዲመጣም በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ የጋራ ኮንዶሚኒየም ከታ ቦሪሼ የማህበረሰብ ፋርማሲ ይፋዊ የሙከራ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መድረክ ተገልጿል።

#ማገልገል ክብር ነዉ
አማኑኤል ወርቃየሁ

16/04/2026

ክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ልዩ ቆይታ ከባሕር በር እስከ ኢንዱስትሪ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ማብራሪያ በተለይም የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት አፈፃፀም አሁን ላይ 44% መድረሱ በዚህ ዓመት ከ50% ለመድረስ፣በሀገር ውስጥ የማምረት ተስፋ፣ በሀገር ውስጥ መድኃኒት እንዳይመረት የሚተናነቁ ፣ገበያውን የተቆጣጠሩ ተግዳሮችን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ #ኢትዮጵያ​ #የባሕርበር​ #ኢንዱስትሪ​ #ወቅታዊመረጃ​ #ብልጽግና​ #ዐቢይአሕመድ​ ​ ​ ​




16/04/2026

ክቡር የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ልዩ ቆይታ ከባሕር በር እስከ ኢንዱስትሪ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ማብራሪያ በተለይም የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦት አፈፃፀም አሁን ላይ 44% መድረሱ እና የሀገር ውስጥ አምራቾች የመስሪያ ካፒታል ከባንኮች በብድር አለመስጠታቸውን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያ

​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ ​ #ኢትዮጵያ​ #የባሕርበር​ #ኢንዱስትሪ​ #ወቅታዊመረጃ​ #ብልጽግና​ #ዐቢይአሕመድ​ ​ ​ ​




Address

9. 046572, 38. 728670
Addis Ababa

Telephone

+251112763276

Website

https://t.me/epsaethiopia2012

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Ethiopian Pharmaceuticals Supply Service - EPSS:

Share