Hagere Community Development Association

Hagere Community Development Association Hagere Community Development Association (HCDA) is an indigenous non-governmental, non-profit, secular, legally registered association.

Hagere Community Development Association (HCDA) is an indigenous non-governmental, non-profit, secular, legally registered association established in May 2012 with a group of volunteers who are committed for improving the livelihood of poor and vulnerable community groups. The founders have a wide experience in the area of community care services, social counseling and integrated community development programs. The rationale behind establishing the organization is the gap in the various areas of community care services, social counseling and integrated community development programs especially education, health and water projects. At the outset, the association is established with a set of vision, mission and goal that caters to the needs of the various community members including children, youth, women and others that require increased attention and support.

ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን አፋር ላይ እየሰራ ያለውን ፕሮጀከት ለማስቀጠል  እና በክልሉ  በኢሊኖ ምክንያት ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት  ህዝባዊ መዋጮ  በአዲስ አበባ ኢሊሊ ...
14/03/2016

ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን አፋር ላይ እየሰራ ያለውን ፕሮጀከት ለማስቀጠል እና በክልሉ በኢሊኖ ምክንያት ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ ለመስጠት ህዝባዊ መዋጮ በአዲስ አበባ ኢሊሊ ሆቴል ላይ ቴሌቶን ማካሄዱን ተከትሎ የተለያዩ ባለ ሀብቶች እና ድርጅቶችን ባናገረበት ጥሩ ምላሽ እያገኘ ነው ፡፡ ለዚህም አብይ ምሳሌ የሚሆነው የኢትዮጵያ ሚለርስ አሶሴሽን በስሩ የሚገኙትን ዱቄት እና የዱቄት ውጤት አምራቾችን በማስተባበር ከ 2000(ሁለት ሺ ) ኩንታል ዱቄት በላይ በማሰባሰብ ለመለገስ ቃል ገብቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ፡፡ለማሰባሰብ ሂደቱም አመቺ እና ቀልጣፋ ይሆን ዘንድ ስልት ወጠኖ እየሰራ ነው ፡፡ ያሰባሰብ ሂደቱም በአሁኑ ጊዜ በ6(ስድስት ) ክላስተር በመከፋፈል ፡
ምድቡም
1. በቃልቲ አከባቢ ዙሪያ ላሉት የዱቄት ፋብሪካዎች Echa food complex
2. በቡራዮ እና አዲስ አበባ አከባቢ ላሉት የዱቄት ፋብሪካ Afia food complex
3. በአለምገና ዙሪያ ላሉት ዱቄት ፋብሪካዎች Haymen flour factory
4. በደቡብ ካልል ከባቢ ላሉት የዱቄት ፋብሪካዎች አዋሳ ከተማ Metafray flour factory
5. ናዝሪት አከባቢ ላሉ የዱቄት ፋብሪካዎች Mohmed abubekr flour factory
6. በአሳላ ከተማ ከባቢ ላሉ የዱቄት ፋብሪካዎች አሰላ chilalo flour factory የተመደቡ ሲሆን አባላቶች በተመደቡበት ክላስተር ማበርከት የሚፈልጉትን በተመደቡበት ክላስተር እንዲያስረክቡ በኢትዮጵያ ሚለርስ አሶሴሽን በኩል ለሁሉም አባላት መልእክቱን በማድረስ ወደስራ ተገብቷ ፡፡ ለአሰራርም ይመች ዘንድ ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፐምንት አሶሴሽን በአይነት ለሚለግሱ የዕቃ መረከቢያ ሰነድ አዘጋጅቶ ከላይ በተዘረዘሩት የዱቄት ፋብሪካዎች አስቀምጧል ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ላስረከቡት እቃ ህጋዊ የድርጅቱን ደረሰኝ መውሰዶን እንዳይዘነጉ ሀገሬ ያስገነዝባል ፡፡

Helping HCDA is assisting the needy!!!

28/02/2016
በአሁኑ ወቅት የአፋር ክልል ሁኔታክልሉ በ5 ዞኖች፣ በ32 ወረዳና፣ 407 ቀበሌዎች የተዋቀረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በደረሰው ድርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እየ...
28/02/2016

በአሁኑ ወቅት የአፋር ክልል ሁኔታ
ክልሉ በ5 ዞኖች፣ በ32 ወረዳና፣ 407 ቀበሌዎች የተዋቀረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኢልኒኖ የአየር መዛባት ምክንያት በደረሰው ድርቅ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እየደረሰባቸው ካሉ ክልሎች ውስጥ ዋነኛው ነው፡፡
የዓለም ምግብ ድርጅት ባወጣው መረጃ አንድ ሶስተኛው የአፋር ህዝብ በረሀብ እየተሰቃየ ይገኛል፡፡ እንደ ምግብና የገቢ ምንጭነት የሚጠቀሙባቸው ከብቶቻቸውም በዚሁ ምክንያት እያለቁ ይገኛሉ፡፡
-------------- --------------- ----------------
የአፋር ክልል ህዝብ አብዛኛው አርብቶ አደርና ዘላን የሆነ ህዝብ ነው፡፡ የክልሉ ማህበረሰብም በዋናነት ምግብም ሆነ የገቢ ምንጭ የሚያደርገው የሚያረባቸውን ከብቶች ሲሆን ከቦታ ቦታ በሚዘዋወር ጊዜም እነዚሁኑ ከብቶች በመያዝ ይንቀሳቀሳል፡፡ የክልሉ የአየር ሁኔታ በአብዘሀኛው በረሀማ ከመሆኑም የተነሳ ለእርሻ ስራነት የሚያውለው መሬት ጥቂትና ብዙ ልፋት የሚጠይቅ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ጊዜያት በአየር መዛባት ምክንያት በሚደርሱ ድርቆች የመመታት እድሉ ሰፊ ነው፡፡ ይህ ተጋላጭነቱም ህዝቡ እንዳያገግም አድርጎታል፡፡ በሌላ በኩልም ክልሉ እጅግ ኋላ ቀር ከመሆኑም የተነሳ ህብረተሰቡ ለተለያዩ ዘርፈ ብዙ ችግሮች የተጋረጠ ነው፡፡
------------ ------------- ----------------------
ይህ በእንዲህ እያለ ነው እንግዲህ ይህ ድርቅ የተከሰተው፡፡ ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን በቦታው በመዘዋወር ያለውን ሁኔታ ለመመልከት ችሏል፡፡ በስፍራው በተደረጉ ምልከታዎች ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለመከታተል በተገኙባቸው ክፍሎች መምህራቸውን ከመከታተል ይልቅ ረሀባቸውን እያሰቡ በተጎሳቆሉ ፊቶቻቸው ደርቀው በጉንጮቻቸው የሚወርዱትን የእንባ ዘለላዎችና መላ አካላቸውን ለተመለከተ የሚፈጥረው ስሜት ከባድ ነው፡፡
እናት ልጆቿን ለማባበል በሚል ከለቅሷቸው እንዲታቀቡ ለማድረግ በተጣጠፈ አንጀቷ ስትጥር መመልከት አንጀት ያላውሳል፡፡ አዛውንት በዚያ የጸሀይ ሀሩር ግለት መናገር አቅቷቸው ሀሳባቸውን በእንባቸው ሲገልጹ በቦታው ተገኝቶ ላየ ከአካባቢው ጥፋ፣ ሩጥ፣ ሂድ፣ ጩኽ ያሰኛል፡፡ እዚህም እዚያም የረሀብ ዋይታ ከሚያሰሙ ህጻናት ባልተናነሰ የህይወታቸውን የመጨረሻ እስትንፋስ የሚያጣጥሩ እንስሳትን ድምጽ መስማት ያሳቅቃል፡፡ በየመንደሩ ተዘርረው የሞቱ ሳይሆን ሆን ብለው የተሰደሩ የሚመስሉ አያሌ እንስሳት አስከሬንን መመልከት ብቻ ሳይሆን በዚያ የሚያልፍ የመኪና ተጓዥ እንኳ መስኮቱን የሚያዘጋው ክርፋት የአካባቢውን ችግር በስፋት ያመለከታል፡፡ በቦታው ለተገኘ ከዚህም የከፋ ሁኔታ መኖሩን ሊታዘብ ይችላል፡፡
-------------------- --------------------- ----------------------
የክልሉ ህዝብ በዚህ ሁኔታ እየተራበ እኛ የነዚህ ወገኖች ችግርን መረዳት ካልቻልን ማን ደራሽ ሊኖር ይችላል ብለን ተነስተናል፡፡ ዛሬ በየከተማው ካሉ ምግብ ቤቶች የሚወጡ ትርፈ ምግቦች እንኳን ምን ያክል ረሀብተኞችን መታደግ እንደሚቻል ማሰብ አያዳግትም፡፡ በየከተሞቻችን ከየትም ተብለው በመጡ የምግብ ዓይነቶች መንበሽበሻችን የጠገበ ሰው የተራበ ያለ መሆኑን ይረሳል የሚለውን ብሂል ሊያስታውስ የሚችል ነው፡፡ ከአፋችን ጫፍ ደርሳ የወደቀችዋን ሩዝ ያጡ ወገኖቻችን እንደ ቅጠል ሊረግፉ ጫፍ ደርሰዋል፡፡ ለእጃችን መታጠቢያነት በሳሙና ብዛት የምናባክነውን ውሃ ለጉሮሯቸው ናፍቀዋል፡፡ ተርበዋል፣ ተጠምተዋል፣ ታርዘዋል፡፡ ይህ ነው እንግዲህ በአፋር ያለው እውነታ፡፡ እናም ለወገን ወገኑ ካልደረሰለት ማን ይደርሳል!!
እናም ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን ይህንን ከግምት በማስገባት ለወገን ደራሹ ወገን ነውና የእርዳታ ድጋፍ ጥሪ ከማድረግም አልፎ በማስተባበር ላይ ይገኛል፡፡

ከፕሮጀክቶቹ ውስጥም ዋና ዋናዎቹ  - በአፋር ክልል ዞን ሦስት ስር በሚገኙት ግዋኔ እና ቦርሞዳዪቱ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ 300 ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት በተለያየ ሁኔታ ድጋፍ በማድረግ ትምህርታ...
28/02/2016

ከፕሮጀክቶቹ ውስጥም ዋና ዋናዎቹ
- በአፋር ክልል ዞን ሦስት ስር በሚገኙት ግዋኔ እና ቦርሞዳዪቱ ወረዳ ውስጥ ለሚገኙ 300 ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት በተለያየ ሁኔታ ድጋፍ በማድረግ ትምህርታቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ አስተዋጽኦ ያበረከተ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ለወላጆቻቸው(አሳዳጊዎቻቸው) አቅማቸውን ለማጎልበት በተለይ በኢኮኖሚ ራሳቸውን ችለው ልጆቻቸውን የሚያሳድጉበት መንገድ ለመፍጠር ዕቅድ ወጥኖ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
- በተመሳሳይ ሁኔታም ደቡብ ላይ በስልጤ ዞን ስር ከሚገኙ ወረዳዎች ሁለት ወረዳዎችን በመምረጥ ማለትም ከሁልባረግ እና ስልጤ ወረዳ ጋር በፕሮጀክት ርዕስ Educational material and clothing support for OVC students በተሰኘ ተፈራርሞ በአጠቃላይ ለ400 (አራት መቶ ) ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት ድጋፍ እያደረገ ሲሆን በድምሩ በአሁን ሰዓት ደርጅቱ 700(ሰባት መቶ) ወላጃቸውን ላጡ ህጻናት እና ለአሳዳጊያቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ፡፡
- ከዚህም በተጨማሪ በደቡብ ክልል በተወሰኑ ወረዳዎች የምግብ ዋሰትናቸውን ላላረጋገጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች የምግብ አቅርቦት ስራ በሰፊው ሰርቷል፡፡

ስለ ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽንሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ልማታዊ ድርጅት ነው፡፡ በዋነኛነት  በሃገራችን ኢትዮጵያ ድህ...
28/02/2016

ስለ ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን
ሀገሬ ኮሚዩኒቲ ደቨሎፕመንት አሶሴሽን ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል ልማታዊ ድርጅት ነው፡፡ በዋነኛነት በሃገራችን ኢትዮጵያ ድህነትን በመቀነስ ረገድና በጎ አድራጎት መስኮች የአገሪቱን እቅዶች ግንዘቤ ውስጥ አስገብቶ በሁሉም መስክ የራሱን አሻራ ለማሳረፍ እየሰራ ይገኛል፡፡
ራዕይ /Vision/
ግንባር-ቀደም የልማት ድርጅት በመሆን በሀገሪቱ ዉስጥ የበለጸገ ፣ ንቁና የተማረ እንደዚሁም ከበሽታና ከድህነት የጸዳ ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት፡፡
ተልዕኮ /Mission/
በሀገራችን ዉስጥ የድሆችንና ከከተማ የራቁ ማህበረሰቦችን አቅም በማሳደግ፣ መሰረታዊ የትምህርት፣ የጤና፣ እንደዚሁም የንጹህ ውሀ አቅርቦትን በማሳደግ ፣ በኤች ኤይ ቪ/ ኤድስና በቤተሰብ ምጣኔ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በማቅረብ፣ እንደዚሁም ተነሳሽነትን በመውሰድ የኢትዮጵያ የአየር ለውጥን በመንከባከብና በመጠበቅ በሁሉም መስክ የተሻለች ሀገር ሆና ማየት ነው፡፡

Address

Addis Ababa
325

Telephone

0911428607

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hagere Community Development Association posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to Hagere Community Development Association:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram