St. Arsema Opetics Work

St. Arsema Opetics Work Best quality with reasonable price!!!

22/04/2024



በመቐለ የሚገኘው " ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የአእምሮ ህሙማን የህፃናት እንክብካቤ ማእከል " በእሳት ቃጠሎ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ ወድመት አጋጥሞታል።

አደጋው ያጋጠመው ሚያዝያ 7/ 2016 ዓ.ም ሲሆን ለበጎ አድራጊዎች ሁሉ የእርዳታ ጥሪ ተማጽኖ አቅርቧል።

የምግባረ ሰናይ ድርጅቱን የተለያዩ በጎ አድራጊዎች ሲረዱት ቆይተዋል።

የሚያዘያ 7ቱ የእሳት አደጋ ከአጋዦቹ አንዱ የሆነው መስፍን ኢንዳስትሪያል ኢንጅነሪንግ ሚሊዮን ብሮች በመስጠት ባሰራው አዳራሽ ነው የደረሰው።

በተነሳው ቃጠሎም አዳራሹ ሙሉ በሙሉ ሲወድም በተረጂዎች ማደሪያ ፣ መመገብያና ፣ መስሪያ ክፍሎች ወድመት ደርሷል።

በከፍተኛ ውጪ የተሰራው አዳራሽ ሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም. የተመረቀ ሲሆን በነጋታው ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው በእሳት ሙሉ በሙሉ የወደመው።

የአደጋው መንስኤ በኤሌክትሪክ ማስተላለፍያ በተነሳ ቃጠሎ ነው ተብሏል።

ያጋጠመው ቃጠሎ ከፍተኛ የነበረ ቢሆንም በህዝብና በመቐለ የእሳት አደጋ መከላከያ ብርጌድ የተቀናጀ ርብርብ በማእከሉ በሚገኙ አቅመ ደካሞች የህይወት ማጣት አደጋ አልደረሰም።

ምግባረ ሰናይ ድርጅቱ በእሳት አደጋ ቃጠሎ ምክንያት የመኝታ፣ መመግብያ ክፍሎቻቸው የተቃጠለባቸው የሚንከባከባችው አቅሞ ደካሞች ሜዳ ላይ ተጥለው እንደሚገኙ በመጠቆም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰብአውያን ሁሉ እንዲረዱት ጥሪ አቅርበዋል።

መርዳት የሚፈልጉ ወገኖች ፍሬምናጦስ የአረጋውያን የእአምሮ ህሙማንና የህፃናት እንክብካቤ ማእከል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000622132404 ሂሳብ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ።



18/11/2023

በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ነገ መሮጥ አልቻልኩም!!!
ቲሸርቱን ትንሽ ላይክ ላገኘው እድለኛ ኮሜንት!!!

13/10/2016

St. Arsema Optics ቅድስት አርሴማ የመነፅር ስራ

04/08/2016

ቅድስት አርሴማ የመነፅር ስራ, Rwanda St, Addis Ababa, Ethiopia

14/05/2016

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። ‹‹የቅድስት አርሴማ ሥዕል በቤተክርስቲያን ትክክለኛው ሥዕሏ የቱ ነው?›› በሚለው ርዕስ የሚቀርበው ተከታታይ ጽሑፍ የመጨረሻው ክፍል እነሆ፡፡ ይህ ጽሑፍ የሚዳሰሰው የቅድስት አርሴማ ሥዕል ተብለው በስፋት የሚሰራጩትን ቅዱሳት አንስት አጠር ያለ ታሪካቸውን…

21/04/2016

ፀሎተ ምህላ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።

“አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረን፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፋችንን ደምስስ።

ከበደላችንም ፈጽሞ እጠበን፥ ከኃጢአታችንንም አንጻን፤ እኛ መተላለፋችንን አናውቃለንና፥ ኃጢአታችንም ሁልጊዜ በፊታችን ነውና። አንተን ብቻ በደልን፥ በፊትህም ክፋትን አደረግን፥ በነገርህም ትጸድቅ ዘንድ በፍርድህም ንጹሕ ትሆን ዘንድ።” መዝ.50/51፡1-4

†♥†♥♥♥†♥† የይቅርታ አምልክ አቤቱ
ማረን የቸርነት አምላክ አቤቱ ይቅር በለን፤ ልጅህን ልከህ ያዳንከን አቤቱ ተመልከተን ጨለማ ሕይወታችንን ወደ ብርሃን የለወጥክ አቤቱ ታደገን።

†♥†♥♥♥†♥† በዚህ ክፉ ዘመን የገጠመንን መከራና ችግር ታርቅልን ዘንድ በአማኑኤል ስምህ
በድንግል እናትህ እንለምንሃለን።

†♥†♥♥♥†♥† በጨለማ ለነበሩት አህዛብ
እንደ ነጋሪት ጮኸው መወለድህንና መምጣትህን ስላስተማሩ ነብያትህ ብለህ ከመዓት ሰውረን።

†♥†♥♥♥†♥† የአህዛብን ምድር በመስቅልህ እርፍ አርሰው የቃልህን መዝገብ በዓለም ዳርቻ ሁሉ ስለ ዘሩ ስለ ቅዱሳን ሐዋርያት ብለህ ከክፉ መከራ አድነን።

†♥†♥♥♥†♥† ድል ስለነሱ፣ አምነው ንጹህ
ስለሆኑ ስለ ሰማዕታት ተኩላዎች ስለበሏቸው ስለመንጋህ ብለህ ይቅር በለን።

†♥†♥♥♥†♥† የጽድቃቸውን ዋጋ
ትሰጣቸው ዘንድ በንጽህና ሹመታቸውን ስላበረከቱ
ፍጻሜያቸውንም ስለተቀበልከው ስለአባቶቻችን ጳጳሳት፣ ቀሳውስት፣ ስለወንድሞቻችን ዲያቆናት፣ ደናግልና መነኮሳት ብለህ ይቅር በለን።

†♥†♥♥♥†♥† ይህንን አላፊ ዓለም
ጠልተው በሰማይ ያለውን ሰርግና ክቡር የማያልፈውንም ተድላ ስለወደዱና ዓለምን ስለናቁ ልጆችህ ስትል ይቅር በለን።

†♥†♥♥♥†♥† የሁላችን እምቤት
የእምነታችን ምልክት የመዳናችን ምክንያት እውነተኛ መብልን የሰጠችን መሶበ ወርቅ የሕይወት ውሃን ያጣፈጠችልን ንጹህ ማሰሮ በሆነች በድንግል ማርያም ስም ብለህ ይቅር በለን።

†♥†♥♥♥†♥† ጌታ ሆይ ስለማያልቀው
ቸርነትህ ስትል ምህረትህን አድርግልን። በዚህ ቦታ በዚህም የምህላና በዚህም ሥፍራ በሀገራችንና በዓለም ሁሉ ምህረትህንና ቸርነትህን አድርግልን።

†♥†♥♥♥†♥† ቸር አምላክ ሆይ የደከሙት
ይዳኑ፣ ኸጥአን ይጽደቁ፣ ንሰሐ የገቡት ይንጹ፣ ፃስቃንም ይጠበቁ የተቸገሩት ይፈቱ፣ የተጠጨነቁት ይረፉ፣ ተክዘው የነበሩ ሁሉ መጸናናትን ያግኙ፣ ያዘኑትም ባንተ ደስ ይበላቸው፤ ተስፋ የቆረጡት ተስፋቸው ይመለስ። በአስከፊ ሕይወት ውስጥ
ያሉ ሰዎች ሁሉ በምህረት ዓይንህን ይጎብኙ።

†♥†♥♥♥†♥† ጌታ ሆይ እየሰተሰማ እየታየ
እየተፈራና እየተጠበቀ ካለው ክፉ ነገር ሁሉ ጠብቀን፤ ሕዝቦችህን ጎብኝ።

†♥†♥♥♥†♥† በቸነፈር፣ በዋግ፣
በአንበጣ በአረማሞ፣ በተምችና በኩብኩባ፣ በወባ ንዳድ በኤድስና በረሃብ ከመሞት ሰውረን።

†♥†♥♥♥†♥† ቸር አምላክ ሆይ በእስር
ቤት ያለ ፍርድ የሚማቅቁትን ፍትህ በማጣት በገዥዎች ቀንበር ሥር ወድቀው የሚሰቃዩትን ሁሉ ተመልክተህ ነፃ አውጣ።

†♥†♥♥♥†♥† ምድራችንን እያናወጠ
ካለው የዲያብሎስ አሰራር፤ እርሱም ዘረኝነት፣ ደም እፍሳሽነት፣ ሽብርተኝነት፣ መናፍቅነት ታደገን።

በመከራችን ጊዜ ካንተ በቀር የሚረዳን፤ በሀዘናችንና በችግራችን ጊዜ የሚታደገን የለምና ይቅር በለን።

በአንድ ልጅህ በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ
ክርስቶስ ስም ከነርሱም ጋር ትክክል በሆነ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል- ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡

አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን
አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

04/02/2014

Best quality with reasonable price!!!

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 09:00 - 19:00
Tuesday 09:00 - 19:00
Wednesday 09:00 - 19:00
Thursday 09:00 - 19:00
Friday 09:00 - 19:00
Saturday 09:00 - 19:00
Sunday 10:30 - 18:00

Telephone

+251-912-61-05-31

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when St. Arsema Opetics Work posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Practice

Send a message to St. Arsema Opetics Work:

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram

Category