Health and medicine

  • Home
  • Health and medicine

Health and medicine this page is to provide general knowledge about health,diseases,and treatment especially drug related

16/07/2023

የኮሌራ በሽታ!!!
የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች፣ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች እና የበሽታው መከላከያ መንገዶች
ኮሌራ ከሰዉነት ዉስጥ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችንና ፈሳሽን በብዛት እና በአጣዳፊ ሁኔታ በተደጋጋሚ ተቅማጥና ትውከት በማስከተል ሰዉነትን አድርቆ የሚገል በሽታ ነዉ፡፡
በሽታዉ የሚያሳያቸዉ ምልክቶች፡-
የሰውነት ድርቀት፣
የአፍ መድረቅ፣
የአይን መሰርጎድ፣
የእንባ መድረቅ፣
የሽንት መቀነስ፣
የቆዳ መሸብሸብና አጠቃላይ የሆነ የድካም ስሜት ያስከትላል፡፡
መተላለፊያ መንገዶች:- በአካባቢና የግል ንጽህና መጓደል አማካኝነት ነው። ማለትም:-
• በሽታው በተበከለ ምግብና ውሃ አማካኝነት ከሰው ወደ ሰው በከፍተኛ ፍጥነት ይተላለፋል፡፡
• ንጹህ ባልሆኑ እጆች ምግብን በማዘጋጀት፣ በማቅረብና በመመገብ፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የምንጭ፣ የጉድጓድ፣ የወንዝ፣ የዝናብ፣ የቧንቧና ወዘተ ውሃን መጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከለ የውሃ ማጠራቀሚያና መገልገያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• ክዳን የሌላቸውና ለዝንቦች የተጋለጡ የምግብ ማስቀመጫና መመገቢያ እቃዎችን በመጠቀም፣
• በበሽታ አምጪ ተህዋስያን የተበከሉ ምግቦችን፣ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን በመመገብ፤ወዘተ ይተላለፋል፡

የኮሌራ በሽታ መከላከያ መንገዶች:-
• ሁልጊዜ ውሃን አፍልቶ እና አቀዝቅዞ መጠጣት ወይም በውሃ ማከሚያ ኬሚካል የታከመ ውሃ መጠቀም፤
• ምግብን በሚገባ አብስሎ በትኩስነቱ መመገብ፤
• የምግብ እቃዎችን በንጹህ ወይም በኬሚካል በታከመ ውሃ ማጠብ እና መጠቀም፣
• መጸዳጃ ቤትን አዘጋጅቶ በአግባቡ መጠቀም፤
• እጅን በሚከተሉት ወሳኝ ጊዜያት በንጹህ ውሃና በሳሙና ሳሙና ከሌለ በአመድ በሚገባ መታጠብ፣
• ከመጸዳጃ ቤት መልስ፣
• ምግብ ከማዘጋጀት በፊት
• ምግብ ከማቅረብ በፊት፣
• ምግብ ከመመገብ በፊት፣
• ሕጻናትን ካጸዳዱ በኃላ፣
• ሕጻናትን ጡት ከማጥባት በፊት ፣
• በበሽታው ለተያዙ ሰዎች እንክብካቤ ካደረጉ በኃላ፣
• በበሽታው የሞቱ ሰዎችን አስክሬን በድንገት ከነኩ፣
• ማንኛውንም ከቤት የሚወጣ ደረቅ ወይም ፈሳሽ ቆሻሻን ውሃንና አካባቢን እንዳይበክል በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ማስወገድ፣
• በኮሌራ በሽታ የታመመን ሰው ልብስ በፈላ ውሃ መቀቀል ወይም በበረኪናና በልብስ ማጽጃ ሳሙና ዘፍዝፎ ማጠብ፣
• በበሽታው የተያዘን ሰው በፍጥነት ወደ ሕክምና ተቋም በመዉሰ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ማድረግ ናቸው።
• የግልና የአካባቢን ንጽህና በመጠበቅ ዝንቦች እንዳይራቡ ያድርጉ፣
• ፈሳሽና ደረቅ ቆሻሻን በአግባቡ በተመደበለት ስፍራ ያስወግዱ
• ሽንት ቤት በመገንባት በአግባቡ ይጠቀሙ እንዲሁም በንጽህና ይያዙ፣
• በተቅማጥና ተውከት የተነካካ እቃን፣ ወለልና መሬትን ከማጽዳትዎ በፊት በረኪና በማፍሰስ ብክለትን ይከላከሉ።
የበሽታ ምልክት ሲታይ መከናወን ያለባቸው ተግባራት:-
- በሽታው የሰውነትን ፈሣሽና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን በብዛት ከሰውነት የሚያስወጣ ስለሆነ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት በመውሰድ እንዲተኩ ያድርጉ።
-በመጀመሪያ ቤት ውስጥ የሚገኘውን ማንኛውም ንጽህናው የተጠበቀ ፈሣሽ የሚችሉትን ያህል ይጠጡ።
-ህይወት አድን ንጥረ ነገር ወይም ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ካለ አንድ ፓኬት ተፈልቶ በቀዘቀዘ አንድ ሊትር ውሃ በመበጥበጥ ይጠጡ፤ የተበጠበጠ ኦ.አር.ኤስን መጠቀም የሚቻለው በተበጠበጠ በ24 ሰዓት ውስጥ ነው።
- ኦ.አር.ኤስ በቤት ውስጥ ከሌለ 8 የሻይ ማንኪያ ስኳር እና ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጨው በአንድ ሊትር ንጹህ ውሃ በመበጥበጥ ባስቀመጥዎ ቁጥር ይጠጡ።

አስም ምንድን ነው? አስም በመተንፈሻ አካላት (የአየር መተላለፊ ቱቦዎች) ጊዜያዊ እብጠት  ወይም መጥበብ የሚመጣ ህመም ነው።  በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ የተለመደ በ...
06/07/2023

አስም ምንድን ነው?
አስም በመተንፈሻ አካላት (የአየር መተላለፊ ቱቦዎች) ጊዜያዊ እብጠት ወይም መጥበብ የሚመጣ ህመም ነው።
በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ሰዎችን የሚያጠቃ የተለመደ በሽታ ነው ÷ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ በልጅነት ይጀምራል::
የአስም በሽታ ተጋላጭነቶች እና የአደጋ ምክንያቶች
• ለአለርጂ የመጋለጥ ዝንባሌ (የአበባ ብናኝ ÷ አቧራ ÷ የቤት እንስሳት ፀጉር)÷
• የመተንፈሻ ቱቦ መቆጣት (በጭስ ÷ በጠንካራ ሽታ)÷
• የአየር ብክለት÷
• የመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን÷
• ከፍተኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ÷
• ትምባሆ÷
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት÷
• አመጋገብ÷
• ቀዝቃዛ አየር ÷
• ጭንቀት÷
• መድሃኒቶች÷
• የሙያ መጋለጥ÷
• የሆርሞን ለውጦች::
የአስም በሽታ ዋና ዋና ምልክቶች:- በሚተነፍስበት ጊዜ የሚያፏጭ ድምፅ(Wheeze)፣ የትንፋሽ ማጠር /ለመተንፈስ መቸገር ፣ ማሳል፡- ብዙ ጊዜ በሌሊት ወይም በማለዳ ይባባሳል፣ የደረት መጨናነቅ(Chest thightness)፣ የድካም ስሜት፣ በፍጥነት መተንፈስ፣ በአተነፋፈስ ችግር ምክንያት መጨነቅ ወይም መደናገጥ፣ ማስነጠስ፣ የአፍንጫ ፍሳሽ እና የአይን ማሳከክ
ወዘተ....
• አስም እንዳለብዎ ከተጠራጠሩ ለትክክለኛ ምርመራ እና የሕክምና አማራጮች የጤና ባለሙያ ማማከር ይኖርብዎታል::
የአስም በሽታ ምርመራ:-
• የሕክምና/የህመም ታሪክ ማዎቅ ፣
• የአካል ምርመራ ማድረግ፣
• የሳንባ ተግባር ምርመራዎች (Spirometry) ፣
• አንዳንድ ጊዜ የአለርጂ ምርመራ።
የአስም ሕክምና
አጋላጭ የሆኑትን/አስምን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መቀነስ ወይም ማስወገድ::
1.1 ራስን ከአለርጂ መጠበቅ/መከላከል
- ቀስቃሾችን መለየት እና ማስወገድ የአስም ምልክቶችን ለመከላከል ይረዳል ፡- የተለመዱ ቀስቃሾች የአበባ ብናኝ፣ አቧራ፣ የቤት እንስሳት ብናኝ፣ ሻጋታ እና አንዳንድ ምግቦችን ያካትታል።
1.2 የአኗኗር ዘይቤን ማሻሻል፡-
1.2.1 መደበኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- የአስም በሽታ ያለባቸውን ሰዎች የሳንባ አሰራርና አጠቃላይ የአካል ብቃት ደረጃን ያሻሽላል።
1.2.2 ጤናማ አመጋገብ፡-በፍራፍሬ፣ አትክልት ፕሮቲን... የበለፀገ የተመጣጠነ አመጋገብ አጠቃላይ ጤናን ሊያስተካክል እና የአየር መተላለፊ ቱቦ እብጠትን ሊቀንስ ይችላል።
1.2.3 የበዛ ጭንቀትን ማስወገድ
[ ] አስፈላጊ ሲሆን ደግሞ መድኃኒቶችን መጠቀም።
የአስም መድሐኒቶች:
1. የጠበበ የመተንፈሻ ቱቦን የሚያሰፉ (Reliever) መድሃኒቶች :-የመተንፈሻ ቱቦ ጡንቻን የሚያዝናኑ እና ለድንገተኛ ምልክቶች ፈጣን እፎይታ የሚሰጡ;
1.1. β2-agonists
• Salbutamol(Albuterol) ብዙ ጊዜ የምንጠቀመው::
• Salmeterol÷ formoterol÷Indacaterol...
1.2. Anticholinergics ÷Theophylline
2. ተቆጣጣሪ መድሃኒቶች(Controllers):- እብጠትን ወይም /መቆጣትን የሚያክሙ;
2.1.Corticosteroids
• በአፍ የሚነፉ:-Beclomethasone....
• በደም ስር የሚሰጡ:-Hydrocortisone...
• በአፍ የሚዋጡ:- predinson/lone...
• ጡንቻ ላይ የሚዎጉ:-
2.2.Leukotriene Modifiers:
• Montelukast
• Zafirlukast......
[ ] የአስም ግላዊ የህክምና እቅድ ማዘጋጀት፡-
• የእርስዎን ልዩ ፍላጎቶች የሚያሟላ እና ጥሩ የአስም መቆጣጠርን ለማግኘት የሚረዳ ግላዊ የህክምና እቅድ ማዘጋጀት÷
• ይህም በጤና ባለሙያዎ አጋዥነት ስለ መድሃኒት አጠቃቀም፣ ስለ ምልክቶችን ማወቅ(የቀን÷የማታ÷በሳምንት ውስጥ) እና ስለ የድንገተኛ ህክምና መመሪያዎችን ያካትታል።
የአስም ህክምና ዓላማ:-
• በቀን የሚከሰት የምልክት ድግግሞሽን በሳምንት ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• በወር ውስጥ ሌሊት ላይ የሚከሰት ህመምን ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• የማስታገሻ(Reliever) መድሃኒት አጠቃቀምን በሳምንት ሁለትና ከዚያ በታች ማድረግ÷
• በአመት ከአንድ ጊዜ ያልበለጠ አጣዳፊ ህመም መከሰት÷
• የሳንባ አሰራርን ማሻሻል÷
• የተለመዱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎችን ያለምንም ችግር ማከናወን÷
• በትንሹ ወይም ምንም የጎንዮሽ ጉዳት ሳይኖር በአስም ህክምና መደሰት÷
ስለ አስም ህክምና የተሳሳቱ ግንዛቤዎች
1.አልሜታሚን (Almetamine ) ያክመዋል ብሎ ማሰብ፣
2. ምስር የምታክል ሮዝ/ነጭ ታብሌት መድሃኒት (Predinsolone) ያለ ሃኪም ትዛዝ ለረጅም ጊዜ መውሰድ በዚህም ለጎንዮሽ ጉዳት መጋለጥ፣
3.በአፍ የሚነፉ መድሃኒቶች (puffs) ይለምድብኛል ብሎ አለመውሰድ፣
4.የሚነፋ መድሃኒትን በትክክል ወደ የአየር መተላለፊ ቱቦዎች ከትንፋሽ ጋር ከማስገባት ይልቅ መዋጥ(...የቴክኒክ ችግር)÷
5.የሚነፋ መድሃኒትን ከወሰዱ በሗላ አፍን አለመታጠብ::

• በትክክለኛ አያያዝና የሕክምና ዕቅዶችን በመተግበር ፣አብዛኞቹ አስም ያለባቸው ሰዎች ያለአንዳች ገደብ መደበኛ ህይወት መምራት ይችላሉ።

ሾተላይ (Rh-isoimmunization)💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh inc...
30/06/2023

ሾተላይ (Rh-isoimmunization)

💥 ሾተላይ የሚባለው በሽታ ከሁለተኛ ጀምሮ የሚወለዱ ህፃናትን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን ይህም በእናትና በፅንሱ መሀከል የደም አይነት አለመጣጣም(Rh incompatability) ምክንያት የሚከሰት ነው።

💥 ሾተላይ የሚከሰተዉ የሴቲቱ የደም አይነት Rh negative ፣ የባል የደም አይነት Rh positive እና የፅንሱ ደግሞ Rh positive ከሆነ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች Rh positive ደም ወደ ሴቲቱ ደም ከገባ ወይም ከወሰደች ነው።

ነጥብ

💥 ሚስት Rh negative መሆን ይኖርባታል እና ፅንሱ Rh positive መሆን ይኖርበታል
💥 ባል Rh negative ከሆነ ሾተላይ አይከሰትም

🌟 ሾተላይ ለምን ይከሰታል?

👉 የሰው ልጅ ከወላጆቹ ዘረመል ተነስቶ ከ4 የደም አይነቶች ውስጥ አንዱን ሊይዝ ይችላል። እነኝህም
1. “A”
2. “B”
3. “AB”
4. “O” ተብለው ይጠራሉ።

👉 በሰውነት ውስጥ የሚገኙ ቀይ የደም ህዋሶች(RBCs) የላይኛው ሽፋናቸው ላይ Rh የተባለ ፕሮቲን (protein) ካላቸው ሴቲቱ Rh positive ናት ማለት ሲሆን እነኚህ ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ Rh negative ናት ማለት ነው።

ለምሳሌ:- ሴቲቱ የደም አይነቷ B ቢሆንና ቀይ የደም ሴሎቿ ላይ Rh ፕሮቲን ካለ B Positive ናት ማለት ነው፤ እነኚህ Rh ፕሮቲኖች ከሌሉ ደግሞ B Negative ናት ይባላል።

👉 አንዲት ሴት ሾተላይ የሚባለው ችግር ሊከሰትባት የሚችለው እሷ Rh negative ሆና በተለያዩ አጋጣሚዎች Rh positive የሆነ ደም ወደሰውነቷ ሲገባ ሰውነቷ እነኚህን Rh positive የደም አይነቶች የሚያጠፉ(የሚገሉ) ንጥረ ነገሮች (Antibodies) ሲያመነጭ (ሲያመርት) ነው። እነኚህም እስከ እድሜልክ በሰውነቷ ይቆያሉ።

👉 እነኚህ የተመረቱት ተከላካይ ንጥረ ነገሮች(Antibodies) የመጀመሪያው ልጅ ላይ ምንም ተፅዓኖ ሳይኖራቸው ልጁ በሰላም ሊወለድ ይችላል ነገር ግን የሁለተኛው ፅንስ የደም አይነቱ Rh positive ከሆነ ወደ ፅንሱ በማለፍ የፅንሱን Rh positive የቀይ የደም ህዋሶች ያጠቃሉ ማለት ነው፤ ይህም ፅንሱን ለተለያየ አደጋዎች ሊያጋልጠው ይችላል።

👉 ይህም ችግር ፅንሱ ላይ የተለያዩ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል ፤ እነኚህም

☘️ በፅንሱ የተለያዩ የአካል ክፍሎች ውሀ መቋጠር - Fetal hydrops
☘️ በተደጋጋሚ የፅንስ መውረድ - Miscarriage
☘️ የፅንሱ የደም ማነስ - Fetal anemia
☘️ ፅንሱ በማህፀን ውስጥ እንዳለ ጊዜው ሳይደርስ ህይወቱ ማለፍ
☘️ ህፃኑ ከተወለደ በውሃላ ቆዳው ቢጫ መሆን እና የጨረር ህክምና ማስፈለግ(phototherapy)
☘️ በከፍተኛ ደም ማነስ ምክንያት ደም ለመውሰድ መጋለጥ

🌟 ሾተላይ እንዴት ይታከማል?

👉 Rh negative የሆነችው እናት ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ነገሮች ከገጠሟት
☘️ ባለቤቷ Rh positive ከሆነ
☘️ ውርጃ ካጋጠማት
☘️ ከማህፀን ውጭ እርግዝና ካጋጠማት
☘️ ከእንግዴ ልጅ ላይ የሚነሳ እጢ(Gestation trophoblastic disease) ካጋጠማት
☘️ በእርግዝና ወቅት አደጋ ከደረሰባት፤
☘️ በክትትል ወቅት ከእንግዴ ልጅ ወይም ከሽርት ዉሃ በመሳሪያ ናሙና ከተወሰደ

👉👉 Anti D የተባለ ኢሚውኖግሎቡሊን (immunoglobulin) መድሀኒት በመውሰድ ሾተላይን መከላከል ይቻላል።

💥☘️ በእርግዝና ጊዜ Anti D የተባለውን መድሃኒትን በ 7 ወር(28 ሳምንት) ላይ እና ህፃኑ በተወለደ ቢቻል እስከ 72 ሰዓት ውስጥ በመስጠት የሾተላይ በሽታን መከላከል ይቻላል።

👉 Rh negative የሆነች እናት(ባል Rh positive) የእርግዝና ክትትሏ ከሌሎች እናቶች ለየት ያለ እና የሚሰጣትም ቀጠሮ በዛ ያለ ይሆናል።

👉 ይህም በልጇ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉትን የሰውነት ውሀ መቋጠር(መጠራቀም) እና የፅንሱ ደም ማነስ ካለ ቀድሞ በማወቅ ህክምናውን በቶሎ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ እዛው ማህፀን ውስጥ እንዳለ ደም በመለገስ እና ወቶ ለመኖር ብቁ በሆነበት ጊዜ ቀድሞ እንዲወለድ በማድረግ ተጨማሪ የሆኑ የህክምና እርዳታዎች እንዲደረግለት ማድረግ ይቻላል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Health and medicine posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your practice to be the top-listed Clinic?

Share

Share on Facebook Share on Twitter Share on LinkedIn
Share on Pinterest Share on Reddit Share via Email
Share on WhatsApp Share on Instagram Share on Telegram